Wednesday, September 28, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊአፍሪካ ‹‹ሜኒንጃይትስ ኤ››ን ለማጥፋት መቃረቧ ተገለጸ

  አፍሪካ ‹‹ሜኒንጃይትስ ኤ››ን ለማጥፋት መቃረቧ ተገለጸ

  ቀን:

  ለምዕተ ዓመት በአፍሪካ በወረርሽን መልክ እየተከሰተ ብዙዎችን ሲቀጥፍ የቆየው ‹‹ሜኒንጃይትስ ኤ›› ወይም ማጅራት ገትር ፍቱንነቱ በተረጋገጠ ክትባት ምክንያት ወደ መጥፋቱ እየተቃረበ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት በድረ ገጹ አስታወቀ፡፡

  በየዓመቱ ብዙዎችን የሚገድለውና አካል ጉዳተኛ ወይም አልጋ ቁራኛ የሚያደርገው ማጅራት ገትር፣ ከሰሃራ በታች የሚገኙ አገሮች ሕዝቦችን በወረርሽኝ መልክ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ሲያጠቃ ቆይቷል፡፡

  ድርጅቱ እንደሚለው ተመጣጣኝ ዋጋ ያለውና ፍቱንነቱ የተረጋገጠው የማጅራት ገትር ቅድመ መከላከያ ክትባት ከአምስት ዓመት በፊት ከተዋወቀ በኋላ፣ ከሰሃራ በታች የሚከሰተው ማጅራት ገትር ኤ ቀንሷል፡፡ ከሴኔጋል እስከ ኢትዮጵያ ባለው የአኅጉሪቱ ክፍል እ.ኤ.አ. በ2013 በላቦራቶሪ የተረጋገጠው ‹‹ማጅራት ገትር ኤ›› ክስተትም አራት ብቻ ነበር፡፡  

  በዓለም ጤና ድርጅት የኢሚዩናይዜሽን፣ ቫክሲንና ባዮሎጂካልስ ዳይሬክተር ዶ/ር ጄን ማሪ ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ‹‹ሜኒንጃይትስ ኤ››ን ለመከላከል የሚሰጠው የክትባት ዘመቻ በአገሮች የሕፃናት ክትባት ሥርዓት ውስጥ ተካቶ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

  ‹‹ሜኒንጃይትስ ኤ›› በአፍሪካ በከፍተኛ ደረጃ በወረርሽን መልክ እ.ኤ.አ. በ1996 ሲከሰት፣ ከ250 ሺሕ በላይ ሰዎችን ያጠቃ ሲሆን፣ ከ25 ሺሕ በላይም ገድሏል፡፡ ይህንን ተከትሎ የተሠራውና በአፍሪካ ከአምስት ዓመት በፊት ተግባር ላይ የዋለው ክትባት፣ የወረርሽኙ ድግግሞሽ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲቀንስ፣ በአንዳንድ አገሮች ደግሞ እንዳይከሰት እያገዘ መሆኑንም ድርጅቱ ገልጿል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ጦርነቱና ውስጣዊ ችግሮች

  መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም. የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው...

  መኖሪያ ሸጦ መዞሪያ!

  እነሆ ከመካኒሳ ወደ ጀሞ ልንጓዝ ነው። ቀና ሲሉት እየጎበጠ...

  በምግብ ራሳችንን የመቻል ፈተና

  በጋሹ ሃብቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ በምግብ ራሳችንን መቻል እጅግ በጣም የተወሳሰበ...