Saturday, June 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበማታለል ወንጀል የተጠረጠሩት መምህር ግርማ ዋስትና ቢፈቀድላቸውም አልተፈቱም

በማታለል ወንጀል የተጠረጠሩት መምህር ግርማ ዋስትና ቢፈቀድላቸውም አልተፈቱም

ቀን:

በየካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ በተለምዶ ወሰን ግሮሰሪ በመባል በሚታወቀው አካባቢ፣ የሚኖሩ ግለሰብን መኖሪያ ቤት በማሸጥና ገንዘባቸውንም ‹‹ፀሎት ይደረግበት›› በማለት አታለው ወስደዋል ተብለው ተጠርጥረው የታሰሩት [መምህር] ግርማ ወንድሙ፣ ጥቅምት 30 ቀን 2008 ዓ.ም. በ50 ሺሕ ብር እንዲፈቱ የተፈቀደላቸው ቢሆንም፣ በተጠረጠሩበት ሌላ ወንጀል አልተፈቱም፡፡

ግለሰቡን በቁጥጥር ሥር አድርጐ በመመርመር ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መርማሪ ቡድን፣ ጥቅምት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት ባቀረበው የምርመራ ሥራው፣ ተጠርጣሪው ፈቃድ ማግኘት ከሚገባቸው ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን (ቤተ ክህነት) ፈቃድ ሳያገኙ፣ በሐሰተኛ ሰነድ (ፎርጅድ) ሲገለገሉ እንደነበር አስረድቷል፡፡

በመሆኑም ቀሪ ምርመራ እንደሚቀረው ገልጾ፣ ከጠየቀው 14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ሰባት ቀናትን ፈቅዶለታል፡፡ በመሆኑም [መምህር] ግርማ፣ ከቤት ሽያጭና ከሲም ካርድ ጋር በተያያዘ በቀረበባቸው ወንጀል በ50 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቢሰጥም፣ በሐሰተኛ ሰነድ የተጠየቀባቸው የሰባት ቀናት ጊዜ የሚያልቀው ኅዳር 2 ቀን 2008 ዓ.ም. በመሆኑ በማረፊያ ቤት ለመቆየት ተገደዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አያሌ የውኃ “ጠርሙሶች”ን በጫንቃ

መሰንበቻውን በአይቮሪ ኮስት መዲና አቢጃን የምትኖር አንዲት ሴት፣ በሚደንቅ...

ወልቃይትን ማዕከል ያደረገው የምዕራባዊያን ጫና

በትግራይ ክልል የተከሰተው የዕርዳታ እህል ዘረፋ የዓለም አቀፍ ተቋማት...

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...