Friday, April 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሰላምና ልማት ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ ተሻሻለ

የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሰላምና ልማት ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ ተሻሻለ

ቀን:

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በቅርቡ ባወጣው ደንብ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሰላምና ልማት ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያን በማሻሻል፣ ተቋሙ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂ ጥናት ኢንስቲትዩት ተብሎ እንዲጠራና ትኩረቱም በውጭ ግንኙነት ላይ እንዲሆን አደረገ፡፡

የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሰላምና ልማት ኢንስቲትዩት በ1988 ዓ.ም. የተመሠረተ ሲሆን፣ ላለፉት 20 ዓመታት የኢትዮጵያ መንግሥትን በሰላም፣ ፀጥታና ልማት ጉዳዮች ሲያማክር የቆየ ነው፡፡ በአገር አቀፍ እንዲሁም በአኅጉር ደረጃ የሚነሱ ግጭቶች አፈታት ዙሪያ አስተዋጽኦ ማድረግ፣ በእነዚሁ ጉዳዮች ላይ የአገር ውስጥ ችሎታና አቅምን በሥልጠና መገንባት፣ እንዲሁም በዲፕሎማሲ መስክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲፕሎማቶችን በሥልጠና አቅማቸውን መገንባት በ1988 ዓ.ም. በወጣው ደንብ የተሰጠው ሥልጣን ነበር፡፡

ፕሮፈሰር ክንፈ አብረሃ የመጀመሪያው የኢንስቲትዩቱ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ፣ ሕይወታቸው እስካለፈበት እ.ኤ.አ. 2007 ድረስ ድርጅቱን መርተዋል፡፡ የእሳቸውን ሕልፈት ተከትሎ ታዋቂው የሕወሓት መሥራች አባል አቶ ስበሃት ነጋ (አቦይ ስበሃት) ኢንስቲትዩቱን እንዲመሩ ተመድበዋል፡፡ በእሳቸው የኃላፊነት ዘመን ማለትም ከሁለት ዓመት በፊት ኢንስቲትዩቱ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር አለመግባባት ውስጥ ገብቶ ነበር፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ኢንስቲትዩቱ ተጠሪነቱ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመሆኑ የውጭ ጉዳይ ዲፕሎማቶችን የማሠልጠን ኃላፊነትም ተጥሎበታል፡፡ ይሁን እንጂ ተቋሙ የሥራ አፈጻጸሙን በተመለከተ ለውጭ ጉዳይ ሪፖርት እንደማያደርግና ዲፕሎማቶች የማሠልጠን ተልዕኮውን ባለመወጣቱ፣ ሚኒስቴሩ ማሠልጠኛ ለመክፈት መገደዱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቤቱታውን አቅርቦ ነበር፡፡

ከአንድ ወር በፊት የፀደቀው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ማሻሻያ ደንብ ቁጥር 347/2008 የተቋሙ ተጠሪነት አሁንም ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲሆን በመወሰን፣ የሥራ ኃላፊነቱን ግን በአብዛኛው በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩር አድርጓል፡፡

“የአገሪቱን የውጭ ግንኙነትና አገራዊ ደኅንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ መሠረት በማድረግ የምርምር ሥራዎችን፣ ጉዳዮችን፣ የውይይትና የገለጻ መድረኮች በማከናወን አማራጭ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን በማፈላለግ ምክረ ሐሳብ ማቅረብ” ከኢንስቲትዩቱ ዋና ዓላማዎች መካከል አንዱ ነው፡፡

የውጭ ግንኙነትና አገራዊ ደኅንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ፣ በአፈጻጸም በአጠቃላይ በዲፕሎማሲና በዳያስፖራ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር በማድረግ አማራጭ የአፈጻጸም ሥልቶች ላይ ምክረ ሐሳብ የማቅረብ ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡

ቀደም ሲል ተቋሙ ከመንግሥት ድጎማ በተጨማሪ ከተለያዩ ለጋሾች በጀቱን ያገኝ ነበር፡፡ የማሻሻያ አዋጁ ግን የተቋሙ ሙሉ በጀት ከመንግሥት ብቻ እንዲሆን ወስኗል፡፡

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አሁንም አቶ ስበሃት ነጋ ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...