Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየወተቱ እንቆቅልሽ

የወተቱ እንቆቅልሽ

ቀን:

አቶ ደረጀ ዳዲ በሰንዳፋ ከተማ ወተት አምራች ነው፡፡ የራሱን ብቻም ሳይሆን ከአካባቢው ገበሬዎች እየሰበሰበ አዲስ አበባ አምጥቶ ለአከፋፋዮች ያስረክባል፡፡ በቀን እስከ 800 ሊትር ወተት ያቀርብ የነበረ ቢሆንም፣ በቅርቡ የዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት (IRLI) ጥናትን በመጥቀስ በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ ዙሪያ ከሚገኙ ከተሞች በተሰበሰቡ ወተቶች ውስጥ አፍላቶክሲን የተሰኘ ኬሚካል መገኘት በመገናኛ ብዙኃን በመዘገቡ ምክንያት፣ ትልቅ ኪሳራ እንደደረሰበት አቶ ደረጀ ለሪፖርተር ገልጿል፡፡

በዚህም በአሁኑ ወቅት በቀን ከ300 ሊትር በላይ ማቅረብ አልቻለም፡፡ በወተት ውስጥ ለአፍላቶክሲን መገኘት ምክንያት የሆነው የሻገተ ፋጉሎ መሆኑ በጥናቱ ቢጠቀስም፣ ሪፖርተር በተለያዩ የሰንዳፋ ከተማ ወረዳዎች ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው ወተት አምራቾች ፋጉሎን ለመኖነት መጠቀም ካቆሙ ዓመታት መቆጠራቸውን ገልጸዋል፡፡ ከኑግ ዘይት ሲጨመቅ ተረፈ ምርት የሆነው ፋጉሎ ዋጋ በኩንታል 800 ብር መሆኑም፣ ከዋጋ አንፃር ተመራጭ እንደማያደርገውም ያስረዳሉ፡፡ በበረህ ወረዳ ከዳቤ ቀበሌ ወተት አምራች የሆነው አቶ ይገዙ አሰፋም የአፍላቶክሲን መገኘት ዜና በእጅጉ ገቢያቸውን እንደጐዳው ገልጿል፡፡ ባለፈው ሳምንት ተቀባዮች ሙሉ በሙሉ ወተት እንዳልተረከቡት ይናገራል፡፡

እሱም በአካባቢው ፋጉሎን ለእንስሳት መኖ ጥቅም ላይ እንደማይውል፣ ይልቁንም ቢሾፍቱ ከተማ ከሚገኝ ዓለማ ካውዳይስ የእንስሳት መኖ ከተሰኘ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተመጣጠነ መኖ እየገዙ እንደሚጠቀሙ አስረድቷል፡፡ በበረህ ወረዳ ግራር ቀበሌ ኗሪና ለሰንዳፋ አካባቢ የእንስሳት መኖ አቅራቢና ወተት አምራች የሆነው አቶ ተሾመ መንግሥቱም፣ በአካባቢው ፋጉሎን ለመኖነት እንደማይጠቀሙ ይናገራል፡፡ እሱም በቀን እስከ 160 ሊትር ወተት ያቀርብ የነበረ ቢሆንም፣ ባለፈው ሳምንት ምንም ተረካቢ አለማግኘቱን ገልጿል፡፡

በወተት ንግዳቸው ላይ እንደዚህ ያለ ኪሳራ ያስከተለው መረጃ ትክክል አለመሆኑ በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙኃን ቢገለጽም፣ ብዙም የተቀየረ ነገር እንደሌለ አምራቾቹ ሪፖርተር ባነጋገራቸው ወቅት ገልጸዋል፡፡ ምርምሩ የተካሄደው ከአዲስ አበባ፣ ከቢሾፍቱ፣ ከሰበታ፣ ከሰንዳፋና ከሱልልታ ከተማ በተወሰዱ የወተት ናሙናዎች ላይ ሲሆን፣ አፍላቶክሲን በወተት ናሙናዎቹ ውስጥ (0.41 ማይክሮ ግራም በሊትር) መገኘት ዜና በኋላ ለወትሮ የወተት ገበያ ግርግር በነበረበት ሰንዳፋ ከተማ፣ ገበያው እረጭ ማለቱን ሪፖርተር በከተማው ተዘዋውሮ ካነጋገራቸው አምራቾች ማረጋገጥ ችሏል፡፡ አምራቾቹ ወጣ የተባለው ምርምር ገበሬውን ክፉኛ የጐዳ፣ በአገር ሀብት ላይም ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳደረ በመሆኑ ነገሮች ወደነበሩበት ይመለሱ ዘንድ መንግሥትና የሚመለከታቸው ሁሉ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ጥናቱን በሚመለከት የመንግሥትንና ጥናቱን የሠራው የዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት አስተያየትን፣ እንዲሁም መንግሥት የወሰዳቸውን ዕርምጃዎች በሚመለከት የቀረበውን ዘገባ ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...