Sunday, March 26, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኤስቢጂ በ80 ሚሊዮን ብር ካፒታል የጁስ ማምረቻ ፋብሪካ ሊገነባ ነው

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በቅርቡ አርኪ የተባለውን የታሸገ ውኃ በማምረት ለገበያ ያቀረበው ኤስቢጂ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በ80 ሚሊዮን ብር ካፒታል የታሸጉ የፍራፍሬ ጭማቂዎች ማምረቻ ፋብሪካ ለመገንባት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሔኖክ ሙላቱ እንደገለጹት፣ የታሸጉ የፍራፍሬ ጭማቂ ማምረቻቸውን ለመገንባት አስፈላጊውን የገበያና የኢንቨስትመንት ጥናት አጠናቀዋል፡፡

ከታሸገ ውኃው ምርት ጐን ለጐን በኤስቢጂ ኩባንያ በኩል ተመርቶ ለገበያ የሚቀርቡትን የታሸጉ ፍራፍሬዎች ጭማቂዎች ማምረቻ በሱሉልታ ይገነባል፡፡ በ40 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተቋቋመው ይህ የታሸገ ውኃ ማምረቻ፣ በቀን ከ260,000 በላይ የታሸገ ውኃ የማምረት አቅም እንዳለው ተገልጿል፡፡ ፋብሪካው በሱሉልታ አካባቢ በ34 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን፣ አዲስ የሚቋቋመው የታሸጉ ፍራፍሬዎች መጭመቂያ ፋብሪካም የሚገነባው በዚሁ ቦታ ላይ መሆኑን አቶ ሔኖክ ተናግረዋል፡፡

ከኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለሥልጣን የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የተሰጠው ሲሆን፣ የመጠጥ ደኅንነቱንም ለማረጋገጥ የአይኤስኦ 22,000፡2005 የተባለውን የምግብ ደኅንነት ሥርዓት ሰርተፍኬት በቅርቡ እንደሚያገኝ ተናግረዋል፡፡

የታሸገ ውኃ ማምረቻው 109 ለሚሆኑ ዜጐች የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ የማኅበራዊ ግዴታ ኃላፊነቱን ከወዲሁ ለመወጣት እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ በዚህ መሠረትም ከእያንዳንዱ ውኃ ሽያጭ 0.02 ሳንቲም ለኩላሊት እጥበት ገንዘብ ለሚያሰባስቡ ድርጀቶች እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡ ምንም እንኳ ገበያ ውስጥ ከገቡ ጥቂት ጊዜ ብቻ ያስቆጠሩ ቢሆንም፣ ከወዲሁ አንዳንድ ተግዳሮቶች እየገጠሟቸው መሆኑን አቶ ሔኖክ አልሸሸጉም፡፡ እንደ እሳቸው ገለጻ አብዛኞቹን ጥሬ ዕቃዎች ከውጭ የሚያስገቡ ሲሆን፣ በተፈጠረው የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንደ ልብ ለመንቀሳቀስ ማነቆ ሆኖባቸዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች