Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ሥነ ፍጥረትካንሰር የማያጠቃው የአይጥ ዝርያ

  ካንሰር የማያጠቃው የአይጥ ዝርያ

  ቀን:

  ካንሰር በእንስሳቱ ዓለም የተለመደ በሽታ ነው፡፡ የሞት መጠኑም በካንሰር ከሚሞቱ ሰዎች ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ከሰው ልጆች ጋር አብረው የሚኖሩት ውሻና ድመት በተለያዩ የካንሰር በሽታዎች ዓይነት ይጠቃሉ፡፡ የቤት እንስሳት በካንሰር እንዲያዙ ትልቁን ሚና የሚጫወተው ለሲጋራ ጭስ ተጋላጭ መሆናቸው ነው፡፡ ሆኖም የዱር እንስሳትም ለካንሰር የተጋለጡ ናቸው፡፡

  የተበከሉ ባህሮች የአሳ ዝርያዎችንና እንስሳትን ለካንሰር የማጋለጥ አቅማቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ሲ ላየንስ በመባል የሚታወቁት ዝርያዎች ‹‹በዩሮጄንታል›› ካንሰር በአብዛኛው የሚጠቁ ናቸው፡፡ ለትላልቆቹ የባህር አሳዎች የሆድ ዕቃ ካንሰር ሁለተኛው ገዳይ በሽታቸው ነው፡፡ ከካንሰር ነፃ ተብሎ ለብዙ ዓመታት ሲነገርለት የቆው ሻርክም ቢሆን ‹‹ሚላኖሚያ›› በሚባል የቆዳ ካንሰር እንደሚጠቃ ተረጋግጧል፡፡ አንዳንድ እንስሳት ደግሞ በካንሰር አይጠቁም፡፡ በሕይወት ዘመናቸውም እጢ በሰውነታቸው አይወጣም፡፡ አይጦች ለካንሰር ተጋላጭ ከሆኑ እንስሳት ቢመደቡም፣ ‹‹ኔክድ ሞል ራት›› ማለትም የተሸበሸበ ቆዳ ኖራቸው ምንም ፀጉር የሌላቸው የአይጥ ዝርያዎች፣ ካንሰር አይዛቸውም፡፡ በረዣዥም የፊት ጥርሳቸው የሚለዩት እነዚሁ የአይጥ ዝርያዎች፣ በተፈጥሮ ካንሰርን የመከላከል አቅም አላቸው፡፡ የትናንሽ እንስሳት ዕድሜ በአሥራዎቹና ከዚያም በታች የተወሰነ ቢሆንም ‹‹ኔክድ ሞል ራት›› 30 ዓመት ድረስ ይኖራሉ፡፡

  የእነዚህ አይጦች ሳንሰርን የመከላከል አቅም የሰው ልጆችን ካንሰር ለማከም የሚያስችል ጥናት ለማድረግ ያግዛል፡፡

  (ቢቢሲ ኧርዝ፣ ሕዳር 2008 ዓ.ም.)

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...