Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከ14 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የሕክምና ግብዓቶች በበጀት ዓመቱ እንደሚቀርቡ ተገለጸ

ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የሕክምና ግብዓቶች በበጀት ዓመቱ እንደሚቀርቡ ተገለጸ

ቀን:

የኢትዮጵያ የመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ በዘንድሮ በጀት ዓመት 14.8 ቢሊዮን ብር የሚያወጡና በአገሪቱ ዋና ዋና የጤና ችግሮች ላይ ያተኮሩ መድኃኒቶች፣ የሕክምና መሣሪያዎች፣ ኬሚካልና ለሕክምና የሚውሉ አጋዥ መገልገያዎች (ሪ-ኤጄንቶች) በግዥና በዕርዳታ ለማቅረብ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በ2007 በጀት ዓመት 13.4 ቢሊዮን ብር፣ በ2006 በጀት ዓመት 9.9 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ መድኃኒቶች፣ የሕክምና መሣሪያዎች፣ አጋዥ መገልገያዎች በግዥና በዕርዳታ ማቅረቡንም የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አድና በሬ ተናገረዋል፡፡

የዘንድሮ በጀት ዓመት አቅርቦት ከ2007 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ1.4 ቢሊዮን ብር፣ የ2007 በጀት ዓመት ከ2006 በጀት ዓመት ጋር ሲተያይ በ3.5 ቢሊዮን ብር ከፍ ማለቱን ተናግረዋል፡፡ መድኃኒቶቹ፣ መሣሪያዎቹ፣ ኬሚካሎችና አጋዥ መገልገያዎቹ በዕርዳታና በግዥ ከቀረቡ በኋላ ሥርጭቱ ደግሞ በዕቅድ እንደሚመራ አስረድተዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከዚህ አኳያ በ2006 በጀት ዓመት 10.4 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ መድኃኒቶች፣ የሕክምና መሣሪያዎች፣ ኬሚካልና አጋዥ መገልገያዎች ወደ ጤና ተቋማቱ ተሰራጭተዋል፡፡ ይህም ሥርጭት ከአቅርቦቱ ጋር ሲታይ ቁጥሩ ከፍ ሊል የቻለው ከባለፈው በጀት ዓመት በክምችት ከቆዩት ጋር አብረው በመሠራጨታቸው ነው፡፡ በ2007 በጀት ዓመት ደግሞ 12.5 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ መድኃኒቶች፣ መሣሪያዎች፣ ኬሚካልና አጋዥ መገልገያዎች መሠራጨታቸውን፤ ይህም ከአቅርቦቱ ጋር ሲነፃፀር የሥርጭቱ መጠን ዝቅ ሊል የቻለው ለክምችት የተያዙ በመኖራቸው ነው፡፡

ለሕይወት እጅግ አስፈላጊ፣ መቅረትና ለአንድ ጊዜ እንኳን መስተጓጎል የሌለባቸው ተብለው ከተለዩና ክትትል ከሚደረግባቸው 35 መሠረታዊ መድኃኒቶች ውስጥ፣ በ27ቱ እና በ270 የጤና ተቋማት ላይ በተካሄደው ጥናት መሠረትም፣ ኤጀንሲው የመድኃኒት አቅርቦትን 89 ከመቶ መሸፈኑን ተናግረዋል፡፡

ጥናቱ የተካሄደው በ2006 ዓ.ም. ሲሆን፣ የተከናወነውም በውጭ አጥኚዎች አማካይነት ነው፡፡ 27 መድኃኒቶች ለጥናት የተመረጡትም፣ በአንድ አገር ውስጥ መሠረታዊ መድኃኒቶች ለመኖራቸው አመላካች ለመሆናቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ የወጣውን መሥፈርት አሟልተው በመገኘታቸው ነው፡፡

ለሕይወት እጅግ አስፈላጊ፣ መቅረት የሌለባቸው ተብለው ከተለዩትና ክትትል ከሚደረግባቸው ልዩ ልዩ መድኃኒቶች መካከል የኤችአይቪ፣ የቲቢ፣ የወባና የካንሰር  ተጠቃሾች ናቸው፡፡ 

በአንዳንድ የጤና ተቋማት ውስጥ በውድ ዋጋ ተገዝተው የቀረቡት የሕክምና መሣሪያዎች በተበላሹ ቁጥር የሚጠግናቸው ባለሙያ በመታጣቱ የተነሳ ያለአገልግሎት ተቀምጠው ይስተዋላሉ፡፡ ወ/ሮ አድና እንደሚሉት፣ የጤና ተቋማቱ ላስገቧቸው የሕክምና መሣሪያዎች አምራቹ ወይም አቅራቢው ዋስትና ይገባል፡፡ በገባውም ዋስትና መሠረት መሣሪያዎቹን ይተክላል፣ ሲበላሹ ይጠግናል፣ ሥልጠናም ይሰጣል፡፡ ሆኖም አካሄዱ ቀጣይነት እንዲኖረው ኤጀንሲው ባለፈው በጀት ዓመት በዳይሬክቶሬት ደረጃ የተዋቀረ አንድ የሥራ ሒደት ተቋቁሟል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...