የመካከለኛውና ምሥራቅ አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ሊካሄድ አንድ ቀን ቀደም ብሎ በተከናወነው የውድድሩ ጠቅላላ ጉባዔ በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል በተደረገው ስብሰባ፣ ለዞኑ ፕሬዚዳንት ተወዳድረው የነበሩት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ ሳይሳካላቸው መቅረቱ ታውቋል፡፡ ኢትዮጵያ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዝርዝር ውስጥ እንኳ እንዳልተካተተች ተሰምቷል፡፡
በስብሰባው የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሴፕ ብላተርን ተክተው ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩት የዮርዳኖሱ ልዑል ዓሊና የፈረንሣዩ ዤሮም ሻምፓኝ ለ12 አባል አገሮች ፕሬዚዳንቶች ስለወቅታዊው የፊፋ ጉዳይ ገለጻ አድርገዋል ተብሏል፡፡ የፊፋ ዕጩ ተወዳዳሪዎች በሴካፋ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ መገኘት ያልተጠበቀ እንደነበርም ተገልጿል፡፡