Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበአሥር ቀናት ውስጥ እንዲካሄድ የተወሰነው የኢትዮጵያ የግብፅና የሱዳን ስብሰባ ተላለፈ

በአሥር ቀናት ውስጥ እንዲካሄድ የተወሰነው የኢትዮጵያ የግብፅና የሱዳን ስብሰባ ተላለፈ

ቀን:

ከአሥር ቀናት በፊት በግብፅ በተካሄደው ዘጠነኛው የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን የጋራ ቴክኒክ ኮሚቴ፣ ለዚህ ሳምንት አሥረኛ ጉባዔውን በሱዳን ለማካሄድ ይዞት የነበረው ቀጠሮ ላልተወሰነ ጊዜ ተላለፈ፡፡

ጉባዔው የተላለፈው የኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር አቶ ሞቱማ መቃሳ በገጠማቸው አስቸኳይ የመንግሥት ኃላፊነት ወደ ውጭ በመጓዛቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡ በመሆኑም ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ ከጉዞአቸው በኋላ በቀጣዩ ሳምንት መጨረሻ ወይም የሦስቱ አገሮች የጋራ ኮሚቴ ተስማምቶ በሚወስነው መሠረት ቀጣዩ ጉባዔ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

የጋራ የቴክኒክ ኮሚቴው ለዚህ ሳምንት ለመገናኝት ቀጠሮ ይዞ የነበረው የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግብድ ተፅዕኖዎችን ለመገምገም የተመረጡት፣ የኔዘርላንዱ ዴልታ ሬዝ ኩባንያና የፈረንሣዩ ቢአርኤል ኢንጂነርስ መካከል መግባባት ለመፍጠር ነበር፡፡

በጥናቶቹ ላይ የ30 በመቶ ተሳትፎ ብቻ እንዲኖረው ሆኖ የተመረጠው የኔዘርላንዱ ኩባንያ በዋና አጥኙ ኩባንያው የፈረንሣዩ ቢአርኤል የቀረበውን የጥናት መመርያ ባለመቀበል፣ ራሱን ከሥራው ማግለሉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በግብፅ በኩል ተሳትፎው የሚፈለገው የኔዘርላንዱ ዴልታ ሬዝ ራሱን በማግለሉ በኢትዮጵያ በኩል ሁለት አማራጮች ማለትም፣ የፈረንሣዩ ኩባንያ ብቻውን ጥናቱን ያከናውን ወይም ቀደም ሲል ከተወዳደሩት ሌሎች ኩባንያዎች መምረጥ የሚሉ ሐሳቦች ቀርበው ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ግብፅ ሁለቱን የኢትዮጵያ ሐሳቦች ባለመቀበል ዴልታ ሬዝና ቢአርኤል የተባሉት ኩባንያዎችን ማደራደር እንደሚሻል በመጠቆሟ ነበር ለዚህ ሳምንት ቀጠሮው የተያዘው፡፡

በአሁኑ ወቅት በመገንባት ላይ ያለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ 48 በመቶ መድረሱን፣ ሰሞኑን የወጡ የመንግሥት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...