Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአዲስ አበባ አስተዳደር አምስት የመሬት ቢሮ ባለሥልጣናት ተዘዋወሩ

የአዲስ አበባ አስተዳደር አምስት የመሬት ቢሮ ባለሥልጣናት ተዘዋወሩ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ሁለት ምክትል ኃላፊዎችን ጨምሮ አምስት ባለሥልጣናት ከቦታቸው ተነስተው አዲስ ኃላፊነት ተሰጣቸው፡፡

ሁለቱ ምክትል ኃላፊዎች አቶ ኃየሎም ጣውዬና አቶ ሐሰን አቡዲ ናቸው፡፡ አቶ ኃየሎም የፌዴራል ቴክኒክና ትምህርት ሥልጠና ኢንስቲትዩት ምክትል ፕሬዚዳንት፣ አቶ ሐሰን ደግሞ የአዲስ አበባ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡

በተጨማሪም የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኃረጎት ዓለሙና ምክትላቸው ወ/ሮ ሃይማኖት ወልደ ገብርኤል ከቦታቸው ተነስተዋል፡፡

አቶ ኃረጎት የቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ሲሾሙ፣ ወ/ሮ ሃይማኖት ደግሞ በከንቲባ ጽሕፈት ቤት ሥር ሆኖ እንዲደራጅ የተደረገው የቅሬታና አቤቱታ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡

የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ አፀደ ዓባይ ደግሞ ካሉበት ቦታ ተነስተው፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ ምክትል ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡

የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ኃይሌ ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ እስካሁን ሁነኛ አመራር ባለመገኘቱ አሁንም በቦታቸው ላይ ይገኛሉ፡፡

ለረጅም ዓመታት በማያቋርጥ የመዋቅርና የሰው ኃይል ለውጥ ሲካሄድበት የቆየው የአዲስ አበባ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ በድጋሚ የሰው ኃይል ለውጥና በአነስተኛ ደረጃም ቢሆን የመዋቅር ለውጥ ተደርጎበታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ ባስተዋወቀው የመዋቅር ለውጥ የመሬት ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ በክላስተር እንዲመራ አድርጓል፡፡ ክላስተሩን የከተማው ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው እንዲያስተባብሩ ተሾመዋል፡፡

አምስቱ ዋና ዋና አመራሮችም እንዲሁ ብዙም ካልቆዩበት ሥልጣን እንዲነሱ የተደረገ ሲሆን፣ የሚተኳቸው አመራሮች እስካሁን ይፋ አለመደረጋቸው ታውቋል፡፡

አቶ ኃየሎም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተነሱት የፌዴራል መንግሥት ባደረገላቸው ጥሪ ሲሆን፣ ፓርቲያቸው ብአዴን ስለፈቀደላቸው ከቦታቸው መነሳታቸው ታውቋል፡፡ በአንፃሩ ሌሎቹ ባለሥልጣናት የተነሱበት ምክንያት ይፋ ባይደረግም፣ እየተካሄደ ባለው የአዲስ አበባ አስተዳደር የሥልጣን ሽግሽግ ምክንያት እንደሆነ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...