Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊብሔራዊ ባንክ የቦንድ ግዢ ሰነድ ላይ የተሠራ ጥናት የመንግሥትን ውሳኔ እየጠበቀ ነው

ብሔራዊ ባንክ የቦንድ ግዢ ሰነድ ላይ የተሠራ ጥናት የመንግሥትን ውሳኔ እየጠበቀ ነው

ቀን:

– የኢንሹራንስ ኩባንያዎችና ሌሎቹ ተቋማት የቦንድ ግዢ ተሳታፊ ይደረጋሉ

በሥራ ላይ ያለው የብሔራዊ ባንክ ቦንድ ግዥ ሰነድ (NBE Bill) ተግባራዊነት በአዲስ አሠራር እንዲተካ ለማድረግ ያስችላል የተባለ ጥናት፣ ለመንግሥት ቀርቦ ውሳኔ እየተጠበቀበት መሆኑ ተገለጸ፡፡ ከግል ባንኮች በተጨማሪ የኢንሹራንስ ኩባንያዎችና ሌሎች ተቋማት የቦንድ ግዢ ተሳታፊ ይደረጋሉ ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ ሰሞኑን እንደገለጹት፣ እስካሁን ሲሠራበት የነበረው የቦንድ ሰነድ ግዢ ማዕቀፍ በአዲስ የመተካቱ ሥራ ከስድስት ወራት በላይ ጥናት ተደርጐበት፣ ለመጨረሻ ውሳኔ ለመንግሥት የቀረበ በመሆኑ በቅርቡ ፀድቆ ሥራ ላይ ይውላል፡፡

በአዲሱ አሠራር ላይ ጠለቅ ያለ ማብራሪያ ከመስጠት የተቆጠቡት አቶ ተክለ ወልድ፣ በአዲሱ መመርያ ግን የቦንድ ግዥው በግል ባንኮች ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ  አይቀርም፡፡

እስካሁን 27 በመቶ የቦንድ ግዥ እንዲፈጽሙ ከሚገደዱት የግል ባንኮች በተጨማሪ፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎችም በአዲሱ አሠራር መሠረት እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል፡፡

ከባንክና ከኢንሹራንስ ኩባንያዎች በተጨማሪ በቦንድ ግዥው የግል ጡረታ ፈንድ፣ የመንግሥት ጡረታና የጤና ፈንድም ተካተውበት አዲሱ መመርያ ተግባራዊ እንደሚደረግ አቶ ተክለ ወልድ አስታውቀዋል፡፡ እነዚህ ተቋማት በምን ዓይነት ሁኔታ የቦንድ ግዢ እንደሚፈጽሙ ግን አልተብራራም፡፡

እስካሁን ባለው አሠራር የግል ባንኮች የቦንድ ግዥውን እንዲፈጽሙ የሚደረገው ከሚሰጡት እያንዳንዱ ብድር 27 በመቶ ተሠልቶ ነው፡፡ ይህ መጠን ይቀንስ ወይም ይጨምር ባይታወቅም፣ ማስተካከያ ይደረግበታል ተብሏል፡፡

ይህ የብሔራዊ ባንክ አዲስ አሠራር የንግድ ባንኮች ከሚሰጡት ብድር ላይ 27 በመቶ እያሠሉ ለቦንድ ግዥ እንዲያውሉ ሲደረግ የነበረው አሠራር የሚቀጥል መሆኑን ብቻ ሳይሆን፣ ተጨማሪ ሌሎች ተቋማትም በተመሳሳይ መንገድ እንዲገቡ መደረጉ አዲስ ክስተት ይሆናል፡፡

በማሻሻያው መሠረት ለቦንድ ግዥ የሚውለው መቶኛ ምን ያህል ሊሆን እንደሚችል አልተጠቆመም፡፡ እስካሁን ባለው ሒደት ብሔራዊ ባንክ በቦንድ ሽያጮቹ ከ45 ቢሊዮን ብር በላይ ማሰባሰብ የቻለ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

የቦንድ ግዥ የተፈጸመበት ገንዘብ እንዴት ይመለሳል የሚለው ጉዳይ ጥያቄ ቀርቦበታል፡፡ እንደ አቶ ተክለ ወልድ ገለጻ የቦንድ ሰነዱ ይቀየራል ማለት ይህ 45 ቢሊዮን ብር ለባንኮቹ ይሰጣል ማለት አይደለም፡፡ ‹‹ይህ ገንዘብ ከተሰጠ የዋጋ ንረቱ 40 እና 50 በመቶ እንዲደርስ ያደርጋል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ረገድ የምንሠራቸው ሁለት ነገሮች ይኖራሉ፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹የመጀመሪያው ይህ ገንዘብ ኢኮኖሚው ውስጥ ገብቶ ግሽበት እንዳይሆን በምን ዓይነት መንገድ ነው የምንከላከለው የሚለው መታየት ይኖርባታል፤›› ሲሉ አቶ ተክለ ወልድ አስታውቀዋል፡፡

ሁለተኛው ደግሞ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ልማት ባንከ ከ106 ቢሊዮን ብር በላይ ይፈልጋል፡፡ ይህንን ገንዘብ በምን ሒሳብ ነው ማሰባሰብ የሚቻለው የሚለውን ጨምሮ ሁለት ጉዳዮች ታሳቢ ተደርገው ጥናቱ የተሠራ መሆኑን የገለጹት አቶ ተክለ ወልድ፣ ልማት ባንክ የሚፈልገውን ገንዘቡን ለማሰባሰብ ባንኮቹ ብቻ ሳይሆኑ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች፣ የጡረታ ተቋማት ሳይቀሩ የሚገቡበት አሠራር እንደሚኖር ገልጸዋል፡፡

ወደ ልማት ባንክ ገብቶ ለብድር የሚውለው ገንዘብ ደግሞ በአብላጫው የሚገኘው ከባንኮች የቦንድ ግዥ የሚሰበሰብ መሆኑንም አቶ ተክለ ወልድ አስታውቀዋል፡፡

በቀጣዮቹ ዓመታት የሚፈለገው የገንዘብ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ፣ ይህንን ለመሙላት ያስችላል የተባለው አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ቦንድ ሰነድ ግዥ ማሻሻያ ምላሽ ይሰጣል ተብሏል፡፡     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...