Thursday, May 30, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዝንቅየዘንባባው እሑድ- ሆሣዕና

የዘንባባው እሑድ- ሆሣዕና

ቀን:

ከፋሲካ አንድ ሳምንት በፊት የሚከበረው የሆሣዕና በዓል (የዘንባባ እሑድ) ዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2010 ዓ.ም. ይከበራል፡፡ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዐበይት በዓላት አንዱ የሆነ ሆሳዕና፣ ክርስቶስ ኢየሱስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም የገባበት ዕለት ይታሰብበታል፡፡ በወቅቱ ተሰባስበው የነበሩት የዘንባባና የወይራ ዝንጣፊ ይዘው በደስታ በዝማሬ ‹‹ሆሣዕና የዳዊት ልጅ›› እያሉ በምስጋና የተቀበሉበትን ሁነት ይታሰብበታል፡፡ 

ሁዳዴ (ዐቢይ ጾም) በተጀመረ በስምንተኛው ሳምንት የሚውለው ሆሣዕና፣ የቃሉ መገኛ አራማይስጥ (አራማይክ) ሲሆን፣ ፍቺውም ‹‹አድነን›› ማለት ነው፡፡ በዕብራይስጥም በግእዝም ተመሳሳይ ፍች አለው፡፡

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት፣ ሆሣዕና እሑድ በሁለት ነገሮች ይዘከራል፡፡ አንደኛው በቅዳሴ ጊዜ ‹‹ያለ ሕማምና ያለ ደዌ፣ ያለ ድካምም ለከርሞም ያድርሰን ያድርሳችሁ›› እያሉ ካህናቱ ዘንባባ የሚያድሉበት ሲሆን፣ ሁለተኛው ካህናቱና ምዕመናኑ በቤተ ክርስቲያኑ ዙርያ የሚያደርጉት ዑደት ነው፡፡ ‹‹በታወቀችው በዓላችን መለከቱን ንፉ›› እያሉ የቅዱስ ያሬድ መዝሙር እየተዘመረ፣ በአራቱም ማዕዘናት ዕለቱን በተመለከተ አራቱ ወንጌላት እየተነበቡ ይከበራል፡፡

- Advertisement -

ሆሣዕና ባህላዊ ገጽታዎች የሚታዩበት ነው፡፡ በሁሉም የኢትዮጵያ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ዐውደ ምሕረት ምእመናኑ እየተገኙ የዘንባባ ዝንጣፊ ከመያዝ ባሻገር፣ ከአዋቂ እስከ ሕፃን በዘንባባው ቅጠል ለጣታቸው ቀለበት፣ ለእጃቸው እንደ አልቦ፣ ለራሳቸው እንደ አክሊል የሚጠለቅ አድርገው ያዘጋጃሉ፡፡ ምዕመናኑም የመስቀል ምልክት በመሥራት በቤታቸው ይሰቅሉታል፡፡

በሆሣዕና እሑድ እግዚእ ኢየሱስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁነት በማስታወስ በአንዳንድ አድባራት ተመሳሳይ ሥርዓት ይከናወናል፡፡ በኢትዮጵያ በመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን በአክሱም ጽዮን የበዓሉ አከባበር ለየት ያለ ነው፡፡ ከምዕመናን ባለፈ ቱሪስቶችን የሚስብ ሥነ በዓል አለው፡፡ የአከባበሩ ትውፊት ለአዲስ አበባም ተርፏል፡፡

በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ ትርዒቱ የተካሄደው 112 ዓመት በፊት ነበር፡፡ ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስየዘመን ታሪክ ትዝታዬ በዳግማዊ ምኒልክ ዘመነ መንግሥትበሚለው የትዝታ ድርሳናቸው እንደጻፉት፣ የሆሣዕና በዓል በአክሱም ሥርዓት ዓይነት ሆኖ እንጦጦ ላይ መከበር የተጀመረው 1898 .ም. መጋቢት 30 በሆሣዕና ዕለት ነው፡፡

ከአክሱም የመጡ አንድ መምህር ከበዓሉ ቀን ቀደም ብለው ጀምረው የሥነ ሥርዓቱን አፈጻጸም ለደብሩ ካህናትና ለሕፃናት መዝሙር አስጠንተዋል፡፡ በበዓሉ ዕለት አንዲቱን የበቅሎ ግልገል በወርቅ ጥልፍ የተለጠፈ ባለመረሻት (የበቅሎ የማዕርግ ልብስ፣ በልዩ ልዩ ሐሮች ተጠልፎ የተዘጋጀ ወርቀ ዘቦ) ኮርቻ ተጭኖባት ድባብ ደብበውላትና አጅበዋት ወደ ቤተ ክርስቲያን አመጡዋት፡፡ ዑደት ተደረገ፡፡ ከአክሱም የመጣው የሆሣዕና በዓል ሥነ ሥርዓት ጃንሆይ ዳግማዊ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ መኳንንትም ሁሉ ባሉበት መከበሩ ተመዝግቧል፡፡

  • ሔኖክ መደብር
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን...

የኢትዮ ኤርትራ ሰሞነኛ ሁኔታና ቀጣናዊ ሥጋቱ

“ግንቡን እናፍርስ ድልድዩን እንገንባ” የሚል ፖለቲካዊ መፈክር ጎልቶ በሚሰማበት፣...

ኦሮሚያ ባንክ ከተበዳሪ ደንበኞቼ ውስጥ 92 በመቶ የሚሆኑት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው አለ

ኦሮሚያ ባንክ ለደንበኞቹ ከሰጠው ብድር ውስጥ ለአነስተኛና ለመካከለኛ ኢንተርፕራይዞች...

ሽቅብና ቁልቁል!

ጉዞ ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ ጀምረናል። ተሳፋሪዎች የዕለት ጉርሳቸውን መሸፈን...