Monday, December 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናአንድነት ፓርቲ የቢሮ ኪራይ ባለመክፈሉ ክስ ተመሠረተበት

  አንድነት ፓርቲ የቢሮ ኪራይ ባለመክፈሉ ክስ ተመሠረተበት

  ቀን:

  አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ላለፉት ስድስት ወራት የተጠቀመበትን የቢሮ ኪራይ ባለመክፈሉ፣ የቤቱ አከራይ አቶ ዘካሪያስ ብርሃኑ ክስ መመሥረታቸውን ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡

  ቀበና አካባቢ የሚገኘውን ይህ ቤት ፓርቲው ላለፉት አራት ዓመታት ያህል በዋና ጽሕፈት ቤትነት እየተገለገለበት የሚገኝ ሲሆን፣ በምርጫ 2007 ዋዜማ በተፈጠረው ትርምስ ምክንያት በምርጫ ቦርድ ዕውቅና ተሰጥቷቸው የፓርቲው ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ትዕግሥቱ አወሉ፣ “የደረሰኝ ምንም ዓይነት የፍርድ ቤት መጥሪያ የለም፡፡ ፓርቲው በዚህ ጉዳይ መከሰሱንም አላውቅም፤” በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

  ምንም እንኳን አቶ ትዕግሥቱ ይህን ቢሉም የቤቱ አከራይ አቶ ዘካሪያስ ግን “ሐምሌ 3፣ 9 እና 29 ቀን 2007 ዓ.ም. እንዲሁም ኅዳር 3 ቀን 2008 ዓ.ም. የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት መጥሪያዎችን ቢልክም የፓርቲው ተወካዮች አልቀረቡም፤” ብለዋል፡፡

  አንድነት ፓርቲ አሁን የሚገኝበትን ዋና ጽሕፈት ቤት በምርጫ ቦርድ ዕውቅና ተነፍጎት ከፓርቲው የተለያየው የቀድሞ አመራር በ15,600 ብር ተከራይቶት የነበረ ቢሆንም፣ የአቶ ትዕግሥቱ አመራር ቡድን ከመጣ ጀምሮ ክፍያ እንዳልተፈጸመ አከራዩ ገልጸዋል፡፡

  የቤቱ ባለቤት አቶ ዘካሪያስ ግን፣ ‹‹የቤቱን ኪራይ 40,000 ብር እንደማደርግ አሳውቄ ነበር፤” ሲሉ፣ “ዋጋ እንደሚጨምር ሲነገረን በዚህ ላይ ባለመስማማታችን ክፍያ አልፈጸምንም፡፡ በመጀመሪያ ውሉ መሠረት ክፍያ እንፈጽማለን፤” በማለት አቶ ትዕግሥቱ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

  “የሰርቪስ ቤቱን ለፓርቲው እንዲያከራዩ ዋናው ቤት ደግሞ እንዲከራይ ወይም እንዲታደስ ተነጋግረን ነበር፡፡ ክስ ስለሚባለው ነገር አላውቅም፡፡ ያለብንን ውዝፍ ግን እንከፍላለን፤” በማለት አቶ ትዕግሥቱ አስረድተዋል፡፡ የቤት ኪራዩ ዋጋ ውድ እንደሆነባቸው የገለጹት አቶ ትዕግሥቱ፣ “እንደ ማንኛውም ፓርቲ ለቢሮ የሚሆን ቤት እንዲሰጠን መንግሥትን እንጠይቃለን፡፡ መንግሥት ለቢሮ የሚሆን ቤት ከሰጠን ደግሞ እንለቃለን፤” ብለዋል፡፡

  ለቢሮ የሚሆን ቤት ለማግኘት ለሚመለከተው አካል ጥያቄ አቅርበው እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ትዕግሥቱ፣ “እስካሁን ጥያቄ አላቀረብንም” በማለት መልሰዋል፡፡

  ቤቱን ያከራዩት አቶ ዘካሪያስ ግን፣ “ችግሩን ለመፍታት ከማን ጋር እንኳን መነጋገር እንደምችል አላውቅም፡፡ አመራሮቹ ቢሮ ውስጥም የሉም፤” በማለት ያጋጠማቸውን ችግር በፍርድ ቤት ለመፍታት መምረጣቸውን አስታውቀዋል፡፡ “የፓርቲው ተወካዮች ግን ፍርድ ቤትም ቢሆን ቀርበው ስለጉዳዩ አላስረዱም፤” ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...