Thursday, September 21, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ከሚድሮክ 15 ቤቶች ተረከበ

የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ከሚድሮክ 15 ቤቶች ተረከበ

ቀን:

ለተሿሚዎች መኖርያ ቤት ማቅረብ ያልቻለው የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ለሚድሮክ ኢትዮጵያ ካከራያቸው ቤቶች ውስጥ 15 ቤቶችን ተረከበ፡፡

ሚድሮክ በተለያዩ ጊዜያት ወደ አዲስ አበባ ለሚያመጣቸው እንግዶቹ ሲኤምሲ ግቢ ውስጥ 50 አፓርታማዎችን ከመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ተከራይቷል፡፡ ነባር ተከራዮችን በማስለቀቅ ለተሿሚዎች መኖሪያ ቤት በማቅረብ የተጠመደው የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ፣ ሚድሮክ ከያዛቸው ቤቶች የተወሰኑትን እንዲመልስለት ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ሚድሮክ 15 ቤቶችን ለመልቀቅ በመስማማቱ ኤጀንሲው ርክክብ በማድረግ ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡ እነዚህ ቤቶች ለሚኒስትር ዴኤታዎች እየተሰጡ መሆኑን የኤጀንሲው ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ በሲኤምሲ ግቢ ውስጥ 507 ቤቶች ይገኛሉ፡፡ 50 ቤቶች በሚድሮክ፣ 40 ቤቶች ደግሞ በተሿሚዎች የተያዙ ናቸው፡፡ የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ለ630 ተሿሚዎች መኖርያ ቤቶች እንዲያቀርብ መመርያ ተሰጥቶታል፡፡ ነገር ግን ኤጀንሲው ግንባታ እያካሄደ ባለመሆኑ የታዘዘውን መኖርያ ቤቶች ማቅረብ አለመቻሉ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

ኤጀንሲው የተሰጠውን መመርያ ለመፈጸምና የተሿሚዎችን ፍላጎት ለማሟላት ትኩረት ያደረገው ነባር ተከራዮችን በማስወጣት ላይ ነው፡፡ ከመኖሪያ ቤታቸው እንዲፈናቀሉ የተደረጉ ነዋሪዎችም ቅሬታቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡

የኤጀንሲው ምንጮች ግን በተለይ በሲኤምሲ የሚገኙ ተከራዮች የመንግሥት ቤት ለሦስተኛ ወገን እስከ 60 ሺሕ ብር ድረስ እያከራዩ፣ እነሱ በተለያዩ የኮንዶሚኒየም ሳይቶች በአነስተኛ ዋጋ ይከራያሉ ብለዋል፡፡ ብዙዎቹ ቤቶቹ ውስጥ ስለማይኖሩ ማስረጃ አቅርቡ ሲባሉ የሚይዙት የሚጨብጡት ይጠፋባቸዋል በማለት የኤጀንሲውን መቸገር ያስረዳሉ፡፡

ኤጀንሲው በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተሞች 17 ሺሕ ቤቶችን በማስተዳደር ላይ ይገኛል፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የኤጀንሲው በርካታ ቤቶች በመልሶ ማልማት ምክንያት እየፈረሱ ቢሆንም፣ ኤጀንሲው ግንባታ እንዲያካሂድ ባለመፈቀዱ ይዞታው እየተመናመነ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በርካታ አፓርታማዎቹ እርጅና የተጫጫናቸው ናቸው፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከሚኖሩባቸው አፓርታማዎች ውስጥ 150 ቤቶች ለኑሮ ምቹ ባለመሆናቸው እንዲታሸጉ መደረጉን የኤጀንሲው ምንጮች ይናገራሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...