Friday, June 2, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የ40/60 ሱቆች ጨረታ ተከፈተ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ በ40/60 ቤቶች ፕሮግራም የተገነቡ ሱቆችን ለመሸጥ ያወጣው ጨረታ፣ ረቡዕ መጋቢት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ተከፈተ፡፡

ኢንተርፕራይዙ በሰንጋ ተራና በክራውን ሳይቶች ኮንዶሚኒየም ቤቶች ወለል ላይ የሚገኙ 305 ሱቆችን ለጨረታ ያቀረበ ሲሆን፣ 4,103 የጨረታ ሰነዶች መሸጣቸው ታውቋል፡፡

ጨረታው በመጀመርያ የወጣው ጥር 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ቢሆንም፣ ሽያጩ ሁለት ጊዜ መራዘሙ ተገልጿል፡፡ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ እስከ መጋቢት 17 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጥሎ መጋቢት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. በማዘጋጃ ቤት በይፋ ተከፍቷል፡፡

በአጠቃላይ የጨረታ ሰነዶቹን የሞሉት 858 ተወዳዳሪዎች ሲሆኑ፣ እነዚህም ለቀረቡት 305 ሱቆች ተወዳዳሪ ሆነው ቀርበዋል፡፡

ሱቆቹ ከ62 ካሬ ሜትር እስከ 120 ካሬ ሜትር ስፋት ሲኖራቸው፣ የመጫረቻ ዋጋቸው በካሬ ሜትር 19,364 ብር ነው፡፡

ጨረታው በየዕለቱ እየከፈተ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ መሆኑ ታውቋል፡፡ ለጨረታ የቀረቡት ሱቆች የፓርኪንግ ቦታ፣ እንዲሁም አስፈላጊው መሠረተ ልማት የተሟላላቸው መሆናቸው ታውቋል፡፡

ጨረታው በዘመናዊ ሶፍትዌር ታግዞ የተከፈተ በመሆኑ አለመግባባቶችን ያስቀራል ተብሏል፡፡ አለመግባባት ተከስቶ ቅሬታ በአምስት ቀናት ውስጥ ከቀረበ ምላሽ ይሰጣል ተብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች