Monday, May 29, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዲስትሪክቶች ከሐምሌ ጀምሮ በክልል ደረጃ ሊዋቀሩ ነው

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በተለያዩ ክልሎች የሚቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር ለመፍታት የታቀደው ያልተማከለ ክልላዊ አደረጃጀት፣ ከሐምሌ 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ታወቀ፡፡ በዚህም መሠረት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዲስትሪክቶች ከሐምሌ 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በክልሎች ይዋቀራሉ፡፡

      የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቀደም ሲል የነበረውን በ15 ሪጅኖችና በ450 ማዕከላት የተዋቀረውን አደረጃጀት በመቀየር፣ 11 ክልላዊ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መሥሪያ ቤቶች በ28 ዲስቲሪክቶችና በ517 ማዕከላት በድጋሚ ለማዋቀር ተዘጋጅቷል፡፡

      እስካሁን ባለው አደረጃጀት ዲስትሪክቶች ተጠሪነታቸው በፌዴራል ደረጃ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነው፡፡ ዲስትሪክቶቹ ከክልሎች ጋር  ተመካክረው የማይሠሩ ስለሆነና ሪፖርታቸውንም ለክልሎች ስለማያቀርቡ፣ የክልል መንግሥታትም የነዋሪዎች ቅሬታ ትክክል መሆኑን ቢያምኑም ጣልቃ ለመግባት የሚችሉበት ዕድል ስለሌለ፣ ቅሬታቸውን ለፌዴራል መንግሥት ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡

እያጋጠሙ ያሉት ችግሮች ከፍተኛ ቅሬታ እየፈጠሩ በመሆናቸው፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አደረጃጀቱን እንዲያስተካክል ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የውስጥ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ባዩ ለገሰ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ያልተማከለ አደረጃጀት ለመፈጠር የተለያዩ ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተው፣ በአሁኑ ወቅት አብዛኛዎቹ ሥራዎች በመጠናቀቃቸው ተግባራዊ ለማድረግ ወደ ዝግጅት ተገብቷል፡፡

      ‹‹በአዲሱ አደረጃጀትም ቢሆን ያልተማከለ አደረጃጀቱ ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነው፡፡ ነገር ግን አዲሱ አደረጃጀት ዲስትሪክቶች ከክልሎች ጋር በጋራ የሚሠሩበት ሰፊ ዕድል ይፈጥራል፡፡ ይህም የተሻለ ለውጥ ያመጣል፤›› ሲሉ አቶ ባዩ ገልጸዋል፡፡

አዲሱ አደረጃጀት በሐምሌ 2010 ዓ.ም. ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ የሰው ኃይል ምደባውም አብሮ የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል፡፡

      በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ 4,300 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ብትችልም፣ ይህን ኃይል ለተጠቃሚዎች በማከፋፈል በኩል ከፍተኛ ችግር መኖሩ በስፋት ይነገራል፡፡

ይህንን ችግር ለመፍታት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ አበባን ጨምሮ በሰባት ከተሞች የኃይል ማከፋፈያዎችና የኤሌክትሪክ መስመሮችን እየቀየረ ይገኛል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች