Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በየዓመቱ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ለልማት እንደሚያውሉ ተገለጸ

መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በየዓመቱ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ለልማት እንደሚያውሉ ተገለጸ

ቀን:

መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በአጠቃላይና በተለይም የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማኅበራት ኅብረት (ሲሲአርዲኤ) አባል ድርጅቶች፡ በኢትዮጵያ ዜጎችን ከድኅንት ለማውጣትና ለዘላቂ ልማት እንቅስቃሴ በየዓመቱ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት እንደሚያደርጉ ዶ/ር መሸሻ ሸዋረጋ የኅብረቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ፡፡

ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት በተገኙበትና ኅዳር 16 ቀን 2008 ዓ.ም. በኅብረቱ አዳራሽ በተካሄደው የመልካም ተሞክሮ ፕሮግራም ላይ፣ ዋና ሥራ አስኪያጁ እንደገለጹት፣ ድርጅቶች ይህን ያህል ገንዘብ ኢንቨስት የሚያደርጉት ቁልፍ በሆኑ ማኅበራዊ ዘርፎች ላይ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ የኅብረቱ አባል በሆኑ ድርጅቶች መካከል ሥነ ምግባርን፣ መልካም አስተዳደርን፣ የውስጥና የውጭ ተጠያቂነትን ለማበልፀግ የሚያስችል መቆጣጠሪያ (ሰልፍ ሪጉሌሽን) እንዳላቸው አስርድተዋል፡፡

ሲሲአርዲኤ በ1965 ዓ.ም. በአባልነት ያቀፋቸው ድርጅቶች 13 ብቻ እንደነበሩ፣ በዘንድሮ በጀት ዓመት ግን የአባል ድርጅቶች ቁጥር ወደ 400 ከፍ ማለቱን፣ ለተለያዩ የልማት ሥራዎችም በየዓመቱ 11 ቢሊዮን ብር የሚደርስ እንደሚያወጡም ከዶ/ር መሸሻ ንግግር ለመረዳት ተችሏል፡፡

ዶ/ር አሚር አማን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ የማኅበራት ድርጅቶች (ሲቪል ሶሳይቲ) ለማኅበረሰብና ለቤተሰብ ተኮር ጤና አገልግሎት ማደግ፣ ለጤናና ሥነ ተዋልዶና ለቤተሰብ ምጣኔ ፕሮግራም፣ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር፣ ለአካባቢና ለግል ለንጽሕና መበልፀግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ ተናግረዋል፡፡

የጤናው ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ፕላን በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚሆን ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመው፣ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የአገሪቱን የጤና ሥርዓት በማጠናከር ጥራቱን የጠበቀና ፍትሃዊ የሆነ የጤና አገልግሎት ለመስጠት በሚያካሂደው እንቅስቃሴ ላይ የማኅበራት ድርጅቶች እገዛና ትብብር እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡

ዶ/ር አብርሃም ተከስተ በሚኒስቴር ዴኤታ ማዕረግ የፕላኒንግ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የመጀመርያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ፕላን ለተለያዩ ዘርፎች የተቀመጡትን ግቦች በማሳካት ረገድ ውጤታማ በሆነ መልኩ መጠናቀቁን አመልክተው፤ የልማት አጋሮችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለፕላኑ ስኬታማነት ያበረከቱትን የሥራ ድርሻ መንግሥት እንደሚያደንቀው፣ በአንፃሩም ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ረቂቅ ላይ ግብዓት ለመፍጠር ባካሄደው መድረክ ከኅብረተሰቡና ከማኅበራት ድርጅቶች የታየው ተሳትፎ ፍሬያማ ውጤት እንዳስገኘ ተናግረዋል፡፡

አቶ ካሳ ተክለብርሃን የፌዴራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር ልማት ሚኒስትር፣ መንግሥት የበጎ አድራጎትና ማኅበራት አዋጅን ያወጣውና ኤጀንሲውን ያቋቋመው፣ ድርጅቶቹ የሚያከናውኑትን የበጎ አድራጎት ሥራ በተደራጀና ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማካሄድ እንዲያስችላቸው በማሰብ ነው ብለዋል፡፡

ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት የመጀመርያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ፕላን አገሪቱ በትክክለኛው የልማት አቅጣጫ ላይ መሆኗን አመላክቷል፤ ለሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ፕላን የሚያስፈልጉ የማጠናቀቂያ ሥራዎች እንዳበቁና በቅርቡም ተግባራዊ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡

የዜጎችን ፍላጎት መንግሥት ብቻውን ሊያሳካ እንደማይችል ፕሬዚዳንቱ ገልጸው፣ በዚህም የተነሳ የልማት አጋሮችና የማኅበራት ድርጅቶች በተደራጀና በተቀናጀ መልክ የሚያከናውኑት ሥራ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

በክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማኅበራት ኅብረት የስብሰባ አዳራሽ በተከናወነው ሥነ ሥርዓት ላይ የ2008 ዓ.ም. የመልካም ተሞክሮ አሸናፊ የሆኑ አሥር መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ልዩ ልዩ ሽልማት ተቀብለዋል፡፡

የኅብረቱ አባል በሆኑ ድርጅቶች የተዘጋጀው ኤግዚቢሽንም በታዳሚዎች ተጎብኝቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...