Monday, December 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየጠቅላይ ሚኒስትሩ የምርጫ ክልል ነዋሪዎች በመልካም አስተዳደር ዕጦት ተቸግረናል አሉ

  የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምርጫ ክልል ነዋሪዎች በመልካም አስተዳደር ዕጦት ተቸግረናል አሉ

  ቀን:

  በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን በዳሞት ሶሬ ወረዳ ሥር የምትገኘው የጉኑኖ ከተማ ነዋሪዎች በመልካም አስተዳደር ዕጦት፣ በመሠረተ ልማቶች አለመገንባትና በአስተዳዳሪዎች ያላግባብ በሥልጣን መጠቀም እየተጉላሉ እንደሆነ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

  ዳሞት ሶሬ ወረዳ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የትውልድ መንደር 17 ኪሎ ሜትሮች ያህል የምትርቅ ሲሆን፣ በ2007 ዓ.ም. በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተወዳደሩባት የምርጫ ክልል ነች፡፡

  ‹‹በአካባቢያችን ከልማት አኳያ ከ2000 ዓ.ም. ወዲህ የተሠራ ነገር የለም፡፡ ባለሥልጣናት የከተማና የገጠር መሬት በመሸጥ ያላግባብ ተጠቃሚ እየሆኑ ነው፤›› በማለት በሥፍራው ተወልደው እንዳደጉ የገለጹት አቶ እንዳለ ዓለማየሁ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

  ‹‹ሰሚ የለም፡፡ እስከ ክልል ድረስ ሄደን ጉዳያችንን ብንገልጽም እስካሁን ድረስ የተሰጠን ምላሽ የለም፡፡ የመንግሥት ሀብት ያላግባብ እየባከነ ነው፡፡ በየዓመቱ ከመንግሥት የሚመደበው በጀት ያላግባብ እየፈሰሰ ነው፡፡ የሕዝቡን ጩኸት የሚሰማ ዳኛ የለም፡፡ ችግራችንን ለሚመለከታቸው የክልሉ ኃላፊዎች ብናስረዳም፣ ምንም ምላሽ ባለማግኘታችን አሁን ጉዳዩን ወደ ፌዴራል ለመውሰድ እየተንቀሳቀስን ነው፤›› በማለት አክለው አቶ እንዳለ አስረድተዋል፡፡ በተንሠራፋው የመልካም አስተዳደር እጦት ከፍተኛ ችግር እየደረሰባቸው እንደሆነም አመልክተዋል፡፡

  በተመሳሳይ አቶ ደመቀ ዳታ የተባሉ የከተማው ነዋሪ፣ ‹‹ሥፍራዋ በ1999 ዓ.ም. ወረዳ ከሆነች ጀምሮ ምንም ዓይነት ልማት አልተከናወነም፡፡ የካቢኔ አባላት በሙሉ ለግል ጥቅማቸው ያደሉ ናቸው፡፡ ከማዘጋጃ ቤት ኃላፊዎች ጋር በመተባበር መሬት እየሸጡ ነው፤›› በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡

  ‹‹ከዚህ በፊት በኅብረተሰቡ ቅሬታ መሠረት ሰባት ሰዎች ከማዘጋጃ ቤት ታስረው የነበሩ ቢሆንም፣ ቀጣዮች አመራሮች ግን ከዚህ ሳይማሩ መሬት በመሸጥ ላይ ተሰማርተዋል፤›› በማለትም አክለዋል፡፡

  ‹‹ከዚህ በፊት ‹እከሌ አጥፊ ነው›፣ ‹ልማትን የሚጠላ ነው›፣ ‹የሃይማኖት ልዕልና የሚነካ ነው› በሚል በይፋ በሃይማኖት መሪዎችም ሆነ በአካባቢው ነዋሪዎች ጥቆማ ሲደረግ መንግሥት ይሰማን ነበር፡፡ አሁን ግን ሰሚም ሆነ ምላሽ ሰጪ የለም፤›› በማለት አስተያየታቸውን የሰጡት ደግሞ የቀበሌ 02 ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ሰብሳቢ የሆኑት አቶ መንገሻ መለቁ ናቸው፡፡

  የወረዳው ዋና አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታከለ ታደሰ በበኩላቸው፣ ‹‹እኛ ዘንድ የሚመጡ ጥያቄዎች አሉ፡፡ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚፈቱ አካሎችም አሉ፡፡ ቅሬታን በተመለከተ ከየአካባቢው ከከተማ መሬትና ከገጠር መሬት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች አሉ፡፡ እነዚህንም በአግባቡ እየፈታን ነው፤›› በማለት የተጋነነ ችግር አለመኖሩን ገልጸዋል፡፡

  ‹‹ምናልባት ከመመርያና ከደንብ ውጪ ተገቢ ያልሆነ ጥያቄ የሚያቀርቡ አሉ፡፡ ከዚህ ባለፈ እንደ ቅሬታ አቅራቢ ማንም ቢመጣ የማይስተናገድበት ምክንያት የለም፡፡ ቅሬታ ያላቸውን እናስተናግዳለን ተገቢ ምላሽም ያገኛሉ፡፡ ዞሮ ዞሮ ምላሽ አላገኘንም የሚሉት ሰዎች ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው የሚለው መታወቅ አለበት፡፡ ያልሆነ ጥያቄ የሚያቀርቡ ናቸው፡፡ ወረዳውን ለማወክ የሚፈልጉ ናቸው፤›› በማለት አቤቱታ አቅራቢዎችን አጣጥለዋል፡፡

  በልማት ወደኋላ መቅረትን በተመለከተ ደግሞ፣ ‹‹ይህ ወረዳ ከተመሠረተ ገና ዘጠኝ ዓመቱ ነው፡፡ ከሌሎች ወረዳዎች ጋር ስናነፃፅር ይህ ወረዳ ምን ያህል አደገ ምን ያህልስ ወደኋላ ቀረ የሚለውን ነገር ለተመልካች መተው ይሻላል፡፡ ልማት የለም የሚል ሰው የልማት ጥማት ሳይሆን የነገር ጥማት የያዘው ሰው ቢሆን ነው፤›› በማለት አቶ ታከለ አስተያየታቸውን አጠቃለዋል፡፡

  የሪፖርተር ዘጋቢ በወረዳው ተዘዋውሮ እንዳየው ከሆነ በቅርብ የተገነቡ የሚመስሉ መሠረተ ልማቶች በየቦታው ይታያሉ፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...