Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትሁለት ጨዋታ እየቀረው ሻምፒዮናው ቅዱስ ጊዮርጊስ ዋንጫውን አንስቷል

ሁለት ጨዋታ እየቀረው ሻምፒዮናው ቅዱስ ጊዮርጊስ ዋንጫውን አንስቷል

ቀን:

  • ተፎካካሪዎቹ ለመርሐ ግብር ማሟያ ይጫወታሉ

ከእግር ኳሳዊ ፉክክሩ ይልቅ አለመግባባቱና እንኪያ ሰላንቲያው የተመልካቾችን ቀልብ አግኝቶ የቆየው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ፣ ሁለት ጨዋታ እየቀረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ዋንጫውን አንስቷል፡፡ ተፎካካሪዎቹ ለመርሐ ግብር ማሟያና ላለመውረድ ይጫወታሉ፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ዓመታት ያለተቀናቃኝ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ከፍ ማድረጉን ያረጋገጠው፣ በ28ኛው ሳምንት መርሐ ግብር የዘንድሮውን ጨምሮ ለዓመታት ላለመውረድ እየተጫወተ የሚገኘውን ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ0 በሆነ ጠባብ ውጤት ከረታ በኋላ ነው፡፡ ለውድድሩ ድምቀትም ሆነ ለዋንጫው ተስፋ ተጥሎባቸው የቆዩት ተከታዮቹ ደደቢትና ሲዳማ ቡና ለተጋጣሚዎቻቸው እጅ መስጠታቸው ከወዲሁ የቅዱስ ጊዮርጊስን የዋንጫ ባለቤትነት አረጋግጧል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ቀጣይ ትኩረቱ ከፕሪሚየር ሊጉ ይልቅ በአፍሪካ የክለቦች ሻምፒዮና ምድብ ድልድል እንዲሆን ዕድሉ ተመቻችቶለታል፡፡ ማክሰኞ ግንቦት 15 ቀን 2009 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቱኒዚያው ኤስፔራንስ ጋር ሁለተኛውን የሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድል ጨዋታውን ያደርጋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሜዳው ውጪ ከደቡብ አፍሪካው ሰንዳውን ጋር ተጫውቶ 0 ለ0 መለያየቱ ይታወሳል፡፡

በ28ኛው ሳምንት ጨዋታ ወደ ከፍተኛው ሊግ መውረዱን ካረጋገጠው የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በተጨማሪ፣ የሁለቱ ቀሪ ወራጅ ክለቦች ጨዋታ የፕሪሚየር ሊጉን ቀሪ ሁለት ጨዋታዎች ተጠባባቂ አድርጎት ይቆያል፡፡ በመውረድ ሥጋት ውስጥ የሚገኙት ደግሞ ወላይታ ድቻ 30 ነጥብ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ 29 ነጥብ ጅማ አባቡና 29 ነጥብና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 29 ነጥብ ይዘው ይገኛል፡፡

የፕሪሚየር ሊጉ አወዳዳሪ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ የ29ኛውን ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብር መቼ እንደሚያካሂድ ይፋ ባያደርግም፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከወልዲያ፣ ጅማ አባቡና ከሐዋሳ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ወላይታ ድቻ ከአርባ ምንጭ የሚያደርጉት የጨዋታ መርሐ ግብር ነው ተጠባቂነቱን የሚያሳየው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...