Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየአፍሪካ ሰርከስ

የአፍሪካ ሰርከስ

ቀን:

የአፍሪካ ሰርከስ አርቲስቶችን በማጣመር ግንባር ቀደም እንደሆነ የሚነገርለትን የሰርከስ ፌስቲቫል ብዙዎች በጉጉት ይጠባበቁ ነበር፡፡ በኦሮሞ ባህል ማዕከል የተገኙ ታዳሚዎች ትዕይንቱ እስኪጀመር ከመድረክ ይለቀቁ በነበሩ የአፍሪካ ሙዚቃዎች ይንቀሳቀሱ ነበር፡፡

በመድረኩ ቅድሚያ የተሰጠው ለፌስቲቫሉ አዘጋጅ ለፍካት ሰርከስ ነበር፡፡ ታዳጊና ወጣቶቹ የፍካት ሰርከስ አባላት አስገራሚ ትዕይንቶችን አቅርበዋል፡፡ አክሮባት፣ ሚዛን መጠበቅና ሌሎች ትዕይንቶቻቸው የታዳሚዎችን ቀልብ ገዝተው ነበር፡፡

ከፍካት ሰርከስ በኋላ የሴኔጋሉ ‹‹ሴንሪክ››፣ የደቡብ አፍሪካው ‹‹አክሽንአርቴ›› እና የኬንያው ‹‹ድራመርስ›› የተሰኙ የሰርከስ ቡድኖች በተከታታይ ትዕይንቶቻቸውን አቅርበዋል፡፡

ከኅዳር 17 እስከ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. በተካሄደው የሰርከስ ፌስቲቫል ከግብፅ ‹‹ሬድ ቶማቶ››፣ ከዛምቢያ፣ ‹‹ሰርከስ ዛምቢያ›› ከማዳጋስካር ‹‹አሊያዴስ ፖሊብሌስ››፣ ከኬንያ ‹‹ሰራካሲ ትረሰት›› እንዲሁም ከኢትዮጵያ ደብረብርሃን ሰርከስ ተሳትፈዋል፡፡

ፌስቲቫሉ ከተጠናቀቀ በኋላ ደግሞ የሁለት ቀናት ውይይት በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ ተካሂዷል፡፡ የፈርስት አፍሪካን ሰርከስ አርትስ ፌስቲቫል ፕሮጀክት ማናጀርና የፍካት ሰርከስ ፕሬዚዳንት አቶ ደረጀ ዳኜ ለሪፖርተር እንደተናገረው፣ አፍሪካ ውስጥ ያሉ የሰርከስ አርቲስቶች አንድ ላይ ሥራቸውን የሚያቀርቡበት መድረክ አለመኖሩን ከግምት በማስገባት ፌስቲቫሉ ተዘጋጅቷል፡፡

ለፌስቲቫሉ የተመረጡት ቡድኖች በአጠቃላይ ሶሻል ሰርከስ ላይ ያተኮሩ እንደሆኑ ይናገራል፡፡ ከዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የተውጣጡ ግለሰቦችን የሚያሳትፈውን ሶሻል ሰርከስ ማስፋፋት ቀዳሚ ዓላማቸው እንደሆነም ያክላል፡፡ ከአሥር ዓመታት በፊት የተመሠረተው ፍካት ሰርከስ ኢትዮጵያ ውስጥ በሶሻል ሰርከስ ዘርፍ ከሚጠቀሱት አንዱ ነው፡፡ በዘርፉ ከአፍሪካ ሰርከስ አርቲስቶች ጋር ልምድ ለመለዋወጥ ፌስቲቫሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ያምናል፡፡

በፌስቲቫሉ የተሳተፉ ወደ 80 የሚሆኑ ባለሙያዎች በጥምረት የሚሠሩበት ማኅበር የመመሥረትም ዓላማ አላቸው፡፡ በውይይታቸው ከተነሱት ጉዳዮች የማኅበሩ ምሥረታና ፌስቲቫሉ በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የሚቀጥልበትን መንገድ ማመቻቸት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ፌስቲቫሉ የተዘጋጀበት ሌላው ዓላማ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰርከስ የሚሰጠውን ዝቅተኛ ግምት መለወጥ ነው፡፡ ሰርከስ አንዳች መልዕክት የሚተላለፍበትና አዝናኝም እንደሆነ ለማሳየት ፌስቲቫሉ እንደሚረዳ ፕሬዚዳንቱ ይናገራል፡፡ በሌሎች አገሮች በርካታ የሰርከስ ፌስቲቫሎች እንደሚካሄዱ ኢትዮጵያ ውስጥም ይህ መለመድ እንዳለበት ያሳስባል፡፡

ለመጀመርያ ጊዜ የተካሄደው ፌስቲቫሉ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሰርከስ አርቲስቶች ዕውቀት የሚቀስሙበት፣ የፈጠራ ሥራዎች የሚነሳሱበት፣ ሙያው  ከሰርከስ አርቲስቶች በተጨማሪ ለማኅበረሰቡ ስላለው ፋይዳ ግንዛቤ የሚገኝበት እንደሚሆን ተስፋ ያደርጋል፡፡

ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የተውጣጡ የሰርከስ አርቲስቶች ከአህጉሪቷ ውጭ በሚካሄዱ ፌስቲቫሎች ቢሳተፉም፣ አፍሪካ ውስጥ ተመሳሳይ መድረክ እንደማያገኙ  ከሁለት ዓመት በኋላ ፌስቲቫሉን ኢትዮጵያ ውስጥ የማዘጋጀትና ቀጣይነቱንም የመጠበቅ ዓላማ እንዳላቸውም ይገልጻል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...