Friday, December 8, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ዓባይ ኢንሹራንስ ከሦስት ዓመት ኪሳራ በኋላ ወደ አትራፊነት መሸጋገሩን አስታወቀ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከምሥረታው ጀምሮ ላለፉት ሦስት ዓመት እንደጀማሪ የንግድ ኩባንያ ኪሳራ ሲያስተናግድ የቆየው ዓባይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር፣ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ወደ ትርፋማነት በመሸጋገር 26 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማስዝገብ መቻሉን ይፋ አደረገ፡፡

የዓባይ ኢንሹራንስ የዳይሬክተሮች ቦርድ ይፋ እንዳደረገው፣ መድን ድርጅቱ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ያስመዘገበው ያልተጣራ ትርፍ 35.5 ሚሊዮን ብር እንደነበረና ያስዘመገበው የተጣራ የዓረቦን ገቢም 96.6 ሚሊዮን ብር እንደነበር አስታውቋል፡፡

ኩባንያው 18 ቅርንጫፎችን ከፍቶ ባደረጋቸው እንቅስቃሴዎች በጠቅላላው የ150 ሚሊዮን ብር ጠቅላላ የዓረቦን ውሎችን አስመዝገቧል፡፡ በአሁኑ ወቅት ዓባይ ኢንሹራንስ ያስዘመገበው የተከፈለ ካፒታል 69.3 ሚሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን 75 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል መጠን ለማሟላት የሚቀጥለውን ዓመት እንደሚጠብቅ አስታውቋል፡፡

ከ18 ሺሕ በላይ ደንበኞችና 128 ሠራተኞች እንዳሉት መድን ድርጅቱ ባቀረበው ሪፖርት አመላክቶ፣ ያስመዘገበው ጠቅላላ ሀብትም 255.6 ሚሊዮን ብር መድረሱን አስታውቋል፡፡

በአገሪቱ 16 የግልና አንድ የመንግሥት የመድን ድርጅቶች፣ 369 ቅርንጫፎችን ይዘው እንደሚንቀሳቀሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በእነዚህ ኩባንያዎች አማካይነትም 4400 ሠራተኞች የሥራ ዕድል ማግኘታቸውን፣ 1800 የሽያጭ ወኪሎች፣ 50 ደላሎች እንዲሁም 88 የኪሳራ ገምጋሚዎች በኢንዱስትሪው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች