Sunday, January 29, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ የ40/60 ሱቅ ለመግዛት ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ አቀረበ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ የአዲስ አበባ ከተማ የቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ የንግድ ቤቶችን ለመሸጥ ባወጣው ጨረታ፣ 156 ካሬ ሜትር የ40/60 ሱቅ ለመግዛት 26.6 ሚሊዮን ብር የመጫረቻ ዋጋ አቀረበ፡፡

ባንኩ የሰጠው ዋጋ ለሁሉም ሱቆች ከተሰጡት ዋጋዎች በከፍተኛነት ተመዝግቧል፡፡

መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ.ም. በተከፈተው ጨረታ ኢንተርፕራይዙ 320 ሱቆችን ለጨረታ አቅርቦ ነበር፡፡ የተጠቀሱትን ሱቆች ለመግዛትም 4,100 የጨረታ ሰነዶች ተሸጠዋል፡፡፡

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ለመግዛት በተጫረተው ጨረታ ለካሬ ሜትር 171 ሺሕ ብር ከ50 ሳንቲም የሰጠ ሲሆን፣ አብሮ ተፎካካሪ ከነበረው ሁለተኛ ተጫራች በ50 ሳንቲም በካሬ የተሻለ ዋጋ አቅቧል፡፡

ሦስት መቶ ሃያ ሱቆች በቅርቡ ተጠናቀው ለገዥዎች እየተላለፉ የሚገኙት የሠንጋ ተራና የክራውን የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሳይት የሚገኙ ሲሆን፣ በጨረታው አብዛኛው ከፍተኛ የመጫረቻ ዋጋ ያቀረቡትም ባንኮች መሆናቸው ታውቋል፡፡ ‹‹እኛም ሆነ ሌሎች ተጫራቾች የሰጠነው ዋጋ ከፍተኛ ቢሆንም፣ በአካባቢው የራሳችንን ሕንፃ ለመገንባት በቂ ቦታ የለም፤›› ያሉት የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ፣ ‹‹በተጨማሪ በአካባቢው እንከራይ ብንል የምናወጣው ወጪም ከፍተኛ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ባንኩ በሚቀጥለው ዓመት የራሱን ሕንፃ ለመገንባት እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን፣ ‹‹አስፈላጊ ከሆነ ሕንፃውን ገንብተን እንደጨረስን ሱቁን እንሽጠው ብንል አሁን በጨረታው ካቀረብነው በላይ ዋጋ ማግኘት እንችላለን፤›› ሲሉ አቶ አቤ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በጨረታው ለሽያጭ የቀረቡት ሱቆች እያንዳንዳቸው ከ70 ካሬ ሜትር እስከ 395 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው ናቸው፡፡ ከፍተኛ የመጫረቻ ዋጋ ያገኘው 155.97 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ሱቅ በካሬ ሜትር መነሻ ዋጋው 19,346 ብር ነበር፡፡

ይህ የመነሻ ዋጋ በአጠቃላይ ሱቁን ለመገንባት የወጣውን ወጪ ያህል ነው ሲሉ የጨረታ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አብርሃም ተስፋዬ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ ‹‹አስፈላጊውን ማጣራት አድርገን የጨረታውን ውጤት በቅርቡ ይፋ እናደርጋለን፤›› ብለዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች