Wednesday, December 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናአመፅ በማስነሳት ልዩ ዞን ለማቋቋም ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተከሰሱ

  አመፅ በማስነሳት ልዩ ዞን ለማቋቋም ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተከሰሱ

  ቀን:

  ትጥቅ በመያዝ የእርስ በርስ ጦርነት በማነሳሳት የሸኮ ተወላጆችን ከሸኪቾ ብሔሮች በመለየት ‹‹ሸኮ መዠንገር›› የሚባል ልዩ ዞን ለማቋቋም ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ አራት ተጠርጣሪዎች፣ ኅዳር 20 ቀን 2008 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

  ተከሳሾቹ በደቡብ ክልል ሸካ ዞን የኪ ወረዳ ቴፒ ከተማ የሚኖሩ ሲሆኑ፣ ‹‹የሸኪቾ ብሔር ተወላጆች ከሌላ ቦታ መጥተው ሲኖሩ ዝም ስላልናቸው መሬታችንን እየወረሩት ነው፤›› በማለት፣ እነሱ የተጨቆኑ በማስመሰል፣ የእርስ በርስ ጦርነት አስነስተው ልዩ ዞኑን በማቋቋም በጋምቤላ ክልል ሥር መተዳደር እንዳለባቸው በማመን፣ አመፅ ማስነሳታቸውን ዓቃቤ ሕግ ያቀረበባቸው ክስ ያስረዳል፡፡

  ሚስጥሩ ሲሳይ (በቅፅል ስሙ መቅደላ ዮሐንስ)፣ ስማቸው አርጋው፣ ስንታየሁ ወይሳና ምክትል መቶ አለቃ ብሩ አይደፈር የተባሉት ተከሳሾች፣ በእነሱ አጠራር ‹‹ደገኞች›› የሚሏቸውን ሸክቾዎች አካባቢያቸውን ለቀው መውጣት እንዳለባቸው በመስማማት፣ የጦር መሣሪያ ማለትም ክላሽኒኮቭ፣ የእጅ ቦምብ፣ ጋሻና ጦር በመያዝ ጥቃት መፈጸማቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡

  ተከሳሾቹ ‹‹ዱንቻይ›› የተባለ ጫካ ውስጥ በመግባት ከሌሎች ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን፣ በየኪ ወረዳ ፃኑ ቀበሌ ጉፍታ ንዑስ ውስጥ በነበሩ ፖሊሶች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን፣ ሰላምና ፀጥታ በማወክ ዘረፋ መፈጸማቸውን፣ ቁጥራቸው ያልታወቁ የሸኪቾ ነዋሪዎችን በመግደልና በማቁሰል የተደራጀ የትጥቅ ወንጀል መፈጸማቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያብራራል፡፡

  ተከሳሾቹ ራሱን የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር-ግንቦት ሰባት በማለት ከሚጠራው ድርጅት ጋር ለመሳተፍ በማሰብ ከኢሳት ሚዲያ ጋር ግንኙነት መፍጠራቸውን፣ ዕርዳታ እንዲደረግላቸው በመጠየቅ ከእንግሊዝ አገር በድምሩ 700 ዶላር ተልኮላቸው ለሽብር ዓላማ ማዋላቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡ ምክትል መቶ አለቃ ብሩና ስማቸው አርጋው በሰሜን ሸዋ ሸዋ ሮቢት የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ እንደነበር በክሱ ተጠቁሟል፡፡

  ስማቸው አርጋው የተባለው ተከሳሽ በፈጸመው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በፔቲ ከተማ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት የ11 ዓመታት ጽኑ እሥራት ተወስኖበት፣ በሸካ ዞን ማሻ ማረሚያ ቤት አንድ ዓመት ከአምስት ወራት ከታሰረ በኋላ ማምለጡንም ክሱ አክሏል፡፡ ተከሳሾቹ በአጠቃላይ በተጠረጠሩበት ወንጀል ዓቃቤ ሕግ በተደራጀ የትጥቅ አመፅ እንቅስቃሴ ውስጥ ተካፋይ በመሆን፣ በሽብርተኝነት ድርጅት ውስጥ በመሳተፍና ከእስር በማምለጥ ወንጀሎች ሦስት ክሶችን  መሥርቶባቸዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የፔሌ ምኞትና የብራዚል የኳታር ዓለም ዋንጫ ጉዞ

  የ20ኛው ክፍለ ዘመን ድንቅ ተጫዋችና የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ዓርማ...

  ሞሮኮ ሩብ ፍፃሜውን የተቀላቀለች ብቸኛዋ አፍሪካ

  በኳታር የዓለም ዋንጫ ወደ ሩብ ፍፃሜ ለመግባት ከስፔን ጋር...

  በሰባት የመንግሥት ተቋማት ላይ ሰፊ የወንጀል ምርመራ እየተካሄደ መሆኑ ተሰማ

  በስምንት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲጀመር ተወስኗል ከ1.4 ቢሊዮን...

  በደቡብ ክልል የዛላ ወረዳ ነዋሪዎች በከፍተኛ ረሃብ ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ

  በደቡብ ክልል ጎፋ ዞን የዛላ ወረዳ ነዋሪዎች ከፍተኛ ረሃብ...