የምስር ክክ ሾርባ አሠራር (ለሁለት ሰው)
- 1 የሻይ ኩባያ ምስር ክክ 200 ግራም (የተቀቀለ)
- 1 ራስ ቀይ ሽንኩርት (የተከተፈ)
- 2 ነጭ ሽንኩርት (የተፈጨ)
- 1 ማጂ መረቅ
- ግማሽ ሌትር ውኃ
- 1 ማንኪያ የተፈጨ ድንብላል
- 1 የሾርባ ማንኪያ የአትክልት (የሱፍ) (የወይራ ዘይት)
- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
- 1 ቁንጥር ጨው
- 1 ሎሚ (ጭማቂውን)
- 4 ዳቦ
አዘገጃጀት
- በተዘጋጀው ድስት ውስጥ ዘይት በመጨመር ጥቂር ከጋለ በኋላ ተከትፎ የተዘጋጀውን ቀይና ነጭ ሽንኩርት ቀላ እስከሚል ድረስ መጥበስ፣
- ተቀቅሎ የተዘጋጀውን ምስር ከተፈጨው ድንብላል ጋር በድስት ውስጥ መጨመርና ከ2-3 ደቂቃ አብሮ ማቁላላት፣
- ከዚያ ግማሽ ሌትር ውኃ በመጨመር ከ15-20 ደቂቃ ማፍላት፣
- በመጨረሻም ማጂ መረቅ፣ ቁንዶ በርበሬና ጨው በመጨመር ከ8-10 ደቂቃ እሳቱን በመቀነስ ማንተክተክ
- ሱ ሼፍ ጌታዋ በሪሁን