Monday, June 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየፍሎራይድን መጠን የሚቀንሰው ቴክኖሎጂ ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ

የፍሎራይድን መጠን የሚቀንሰው ቴክኖሎጂ ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ

ቀን:

በስምጥ ሸለቆ አካባቢ ለመጠጥና ለምግብ የሚውለው ውኃ ውስጥ የሚኖረውን የፍሎራይድ መጠን ለመቀነስ እንዲቻል፣ በ1999 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ሁለት ቀበሌዎች በሙከራ ደረጃ የተጀመረው ቴክኖሎጂ ውጤታማ ሆኖ በመገኘቱ፣ በአሁኑ ጊዜ በአምስት ወረዳዎች ውስጥ ባሉት የተለያዩ ቀበሌዎች የሚኖረው ከ30 ሺሕ በላይ  ሕዝብ የውጤቱ ተጠቃሚ ለመሆን መብቃቱ ተገለጸ፡፡

ቴክኖሎጂውን ያስገባው በኦሮሚያ ራስ አገዛዝ ድርጅት (ሰልፍ ኽልፕ ኦርጋናይዜሽን) የፍሎራይድ ሪሙቫል ቴክኖሎጂ ማዕከል ነው፡፡ ማዕከሉ ሙከራውን ለአንድ ዓመት ያህል ያካሄደው በመቂ መዮገብርኤልና በሻሸመኔ ወረዳ ጨለለቃ ቀበሌዎች ውስጥ ሲሆን፣ ሙከራውንም ያከናወነው፣ በአንድ ሊትር ውኃ ውስጥ ያለውን አሥር ሚሊ ግራም ፍሎራይድ ወደ 1.5 ሚሊ ግራም እንዲወርድ በማድረግ ነው፡፡

አቶ ኢሳያስ ሳሙኤል የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ እንደገለጹት፣ የፍሎራይድ መጠኑን ለመቀነስ የዋለው ቴክኖሎጂ፣ ተቃጥሎ የተፈጨ የከብት አጥንት ወይም ቦን ቻር (Bone Char) ነው፡፡

ጥራቱን ጠብቆ የሚመረተው ቦን ቻር፣ በቤትና በጋራ ደረጃ መጠቀም የሚቻል ሲሆን፣ በቤት ውስጥ መጠቀም የሚቻለው፣ ቦን ቻሩን ወይም የደቀቀውን አጥንት ባሊ ውስጥ ከትቶ በላዩ ላይ ያልተጣራውን ውኃ መጨመር ነው፡፡ በጋራ መጠቀም የሚቻለው ደግሞ የማኅበረሰብ የውኃ ማጣሪያ ጣቢያ በማቋቋም ነው፡፡

ኅብረተሰቡ የተጣራ ውኃ የሚያገኝበት ጣቢያ የተቋቋመ ሲሆን፣ ቀኑን ሙሉም ክፍት ነው፡፡ የሚተዳደረውም ከማኅበረሰቡ በተመረጡ የውኃ ኮሚቴ አማካይነት ሲሆን፣ የማዕከሉ የሥራ ድርሻ ቴክኖሎጂውን የማስተዋወቅ፣ ድጋፍና ሥልጠና የመስጠት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

ማጣሪያው ወይም ቦን ቻሩ ቢያንስ እስከ 20 ዓመት ድረስ ያገለግላል፡፡ ነገር ግን መቀየር ካስፈለገ የውኃው ናሙና ተወስዶ፣ በውስጡ ያለው የፍሎራይድ መጠን ምን ያህል እንደሆነ አረጋግጦ መቀየር ይቻላል፡፡ ቦን ቻሩን ማስወገድ ካስፈለገ ደግሞ አጥንቱ ካልሲየምና ፎስፌት ስላለበት እርሻ ላይ ቢበተን  ለማዳበሪያነት ያገለግላል፡፡

በሙከራ ደረጃ በተካሄደበት ወቅት የተጠቃሚዎች ቁጥር 120 አባወራዎች ብቻ እንደነበሩ፣ በአሁኑ ጊዜ ግን ይህ ዓይነቱ ቴክኖሎጂ በአዳማ፣ በዓለም ጤና፣ በዱግደና በዝዋይ ወረዳዎች ባሉት በበርካታ ቀበሌዎች እንደተስፋፋም ገልጸዋል፡፡ በተጠቀሱትም ወረዳዎች ውስጥ ባሉ በተወሰኑ ቀበሌዎች እያንዳንዳቸው እስከ 350 ሺሕ ብር ወጪ የተደረገባቸው 13 የማኅበረሰብ የውኃ ማደያ ጣቢያዎች ተቋቁመዋል፡፡

የማጣሪያው ማምረቻ የሚገኘው ሞጆ አካባቢ ሲሆን፣ በዚህም አካባቢ በአንድ ጊዜ 10 ሺሕ አጥንቶችን የማቃጠል አቅም ያለው ፈርነስ መቋቋሙን፣ አጥንቶቹም የሚሰበሰቡበት ከአዳማ፣ ከካራና ከቡራዩ ቄራዎች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማኅበራት ኅብረት ባለፈው ሳምንት ባዘጋጀው የ2008 ዓ.ም. የመልካም ተሞክሮ ውድድር፣ ማዕከሉ በአንደኛ ደረጃ ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል፡፡

 

     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...