Friday, September 22, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የአይሻ ንፋስ ኃይል ፕሮጀክት ለቻይና ኩባንያ ሊሰጥ ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

የአይሻ ንፋስ  ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን ለቻይናው ግዙፍ ኩባንያ ዳንግ ፉንግ ለመስጠት፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሥራ አመራር ቦርድ ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዳንግ ፉንግ ጋር ሲያካሄድ የቆየውን ድርድር አጠናቆ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ለሚመራው የሥራ አመራር ቦርድ ማቅረቡን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

የሥራ አመራር ቦርዱ ካፀደቀው ዳንግ ፉንግ በሶማሌ ክልል የሚገኘውን ይኼንን የአይሻ ንፋስ ኃይል ማመንጨት ፕሮጀክት ይረከባል፡፡

የአይሻ ንፋስ ኃይል ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ትልቁ የንፋስ ኃይል ማመንጫ በመሆን፣ 300 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል ተብሏል፡፡ ዳንግ ፉንግ ለዚህ ፕሮጀክት የሚያስፈልገውን 250 ሚሊዮን ዶላር ከቻይና መንግሥት የፋይናንስ ተቋማት እንደሚያመጣ ታውቋል፡፡

ይህ የአይሻ ንፋስ ኃይል ፕሮጀክት በ2007 ዓ.ም. በተጠናቀቀው የመጀመርያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ የተካተተ ነበር፡፡

ይኼንን ፕሮጀክት ለመረከብ የጀርመን ኩባንያ የሆነው ላፍቶ የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን፣ ከቻይናው ዳንግ ፉንግ ጋር ፕሮጀክት አቅርቦ ነበር፡፡

ከእነዚህ ኩባንያዎች ጋር ሲደረግ የነበረው የፕሮጀክት ፕሮፖዛል ግምገማና ድርድር ረጅም ጊዜ የወሰደ ሲሆን፣ በመጨረሻ የሚፈለጉትን መሥፈርቶች በሙሉ ዳንግ ፉንግ ሟሟላቱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

መንግሥት የኃይል አቅርቦቱ በውኃ ላይ ብቻ እንዳይመሠረት ዕቅድ አስቀምጧል፡፡ ምክንያቱም አገሪቱ ድርቅ ካጋጠማት ግድቦች ውኃ መያዝ ስለማይችሉ የኃይል አቅርቦቱ ላይ ችግር ይፈጥራል በሚል ነው፡፡

ይኼ ሥጋት ዘንድሮ በግልጽ የታየ በመሆኑ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በቅርቡ ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በድርቁ ምክንያት የኃይል ማመንጫ ግድቦች መያዝ ያለባቸውን ያህል እንዳልያዙ ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን በአማራጭ ኃይል አቅርቦት በኩል የታቀደው ዕቅድ ተግባራዊ አልተደረገም፡፡ መንግሥት በተጠናቀቀው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ከንፋስ ኃይል 894 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት ዕቅድ ነበረው፡፡ ቢሆንም በዕቅድ ዘመኑ ማመንጨት የቻለው 324 ሜጋ ዋት ኃይል ብቻ ነው፡፡ ከአይሻ በተጨማሪ ይጠበቁ የነበሩት መሰቦ ሐረና 42 ሜጋ ዋት፣ አሰላ 100 ሜጋ ዋት እና ደብረ ብርሃን 100 ሜጋ ዋት ይገኙበታል፡፡

ኃይል ማመንጨት የጀመሩት ደግሞ አዳማ አንድና ሁለት፣ አሸጎዳ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች በድምሩ 324 ሜጋ ዋት ያመነጫሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች