Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየጤና መድን ዋስትና ከጥር ወር መጨረሻ ጀምሮ ተግባራዊ ሊሆን ነው

የጤና መድን ዋስትና ከጥር ወር መጨረሻ ጀምሮ ተግባራዊ ሊሆን ነው

ቀን:

የኢትዮጵያ የጤና መድን ኤጀንሲ ከመጪው ጥር ወር 2008 ዓ.ም. መጨረሻ ጀምሮ፣ ማኅበራዊ የጤና መድን ዋስትና አገልግሎት እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡

‹‹ከጥር ወር መጨረሻ ጀምሮ ከአሠሪና ከሠራተኞች ደመወዝ መሰብሰብ ይጀመራል፡፡ ከየካቲት ወር መጀመርያ ጀምሮ ደግሞ አባላት አገልግሎት የሚያገኙበትን አሠራር ከጤና ተቋማት ጋር ውል በመግባት አገልግሎቱ ይጀመራል፤›› በማለት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አታክልቲ አብርሃ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ምንም እንኳ የጤና መድን ዋስትና አገልግሎት ለመስጠት የወጣው አዋጅ ሁሉም የመንግሥት ሠራተኞች፣ ጡረተኞችና ከአሥር በላይ ሠራተኛ ባላቸው የግል ተቋማት ተግባራዊ እንደሚደረግ ቢደነግግም፣ ኤጀንሲው አገልግሎቱን የሚጀምረው ግን በመንግሥት ሠራተኞች፣ በጡረተኞችና በተወሰኑ የግል ተቋማት እንደሆነ ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹አሁን የምንጀምረው በመንግሥት ሠራተኞችና በጡረተኞች ላይ ነው፡፡ አዋጁ አሥርና ከዚያ በላይ ቢልም እነዚህን ድርጅቶች የማግኘት፣ የማደራጀት፣ የገንዘብ ፍሰቱና አሰባሰቡ እንዴት መሆን አለበት የሚለው ከአቅም አንፃር ትንሽ ጊዜ ይፈልጋል፡፡ እንደየክልሉ 50 እና ከዚያ በላይ ወይም 100 እና ከዚያ በላይ ያሏቸው ሠራተኞችን ካዳረስን በኋላ ለተቀሩት ደግሞ በቀጣይ እየሠራን እንሄዳለን፣›› ብለዋል፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት የጤና መድን አገልግሎትን ተግባራዊ ለማድረግ የነበረው ዕቅድ እስከ አሁን  ሳይተገበር ስለቆየበት ምክንያት ሪፖርተር ላቀረበው ጥያቄ፣ ‹‹ተግባራዊ ለማድረግ የነበረው ዕቅድ ሁለት ጊዜ ተላልፏል፡፡ ይኼም የሆነበት ምክንያት አንደኛ ኤጀንሲው ይኼን ለማስፈጸም ተቋማዊ ዝግጅቱ የነበረበትን ሁኔታ በማየት ነው፡፡ አስፈላጊ መዋቅሮች ተቀርፀውና አስፈላጊ ቅጥሮች ተከናውነው አቅሙ ጠንካራ ነው ወይ? ገንዘብ መሰብሰብ ቢጀምር የሕዝብ ገንዘብን ማስተዳደር ይችላል ወይ? የሚሉት ተገምግመው አንዳንድ መሟላት የሚገባቸው ነገሮች ስለነበሩ ነው፤›› በማለት መልሰዋል፡፡

አገልግሎቱ እንዳይጀመር ያደረገው ሌላኛው ምክንያት ደግሞ፣ ከአገልግሎት ሰጪ ጤና ተቋማት ዝግጁነት ጋር የተያያዘ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡ ‹‹ሕዝቡ በፕሮግራሙ ጠቃሚነት ተስማምቶ በዋናነት ይጠይቀው የነበረው ጥያቄ ክፍያ ከፈጸምን በኋላ የጤና ተቋማቱ ሙሉ አገልግሎት ሊሰጡን ዝግጁና ብቁ ናቸው ወይ? የሚለውን ነበር፡፡ ከዚህ አንፃርም ተቋማቱን ፈትሸን መሥፈርትና ደረጃ አውጥተን አጠናቀናል፡፡ በመሆኑም አሁን ኤጀንሲው ከማንኛውም ጊዜ በላይ በሰው ኃይል፣ በዕውቀትና በልምድ የውስጥ አሠራሩን በተሻለ ሁኔታ ዘርግቷል፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡

የገንዘብ አሰባሰብን በተመለከተም፣ ‹‹ለጊዜው ያለውን የመንግሥት የገንዘብ አሰባሰብ ሥርዓትን ተጠቅመን ነው የምንሰበስበው፤›› ብለዋል፡፡ ሁለት ሚሊዮን አባላት እንደሚኖሩት የሚገመተው ይህ አገልግሎት፣ አንድ ቤተሰብ አምስት አባላት እንደሚኖሩ ታሳቢ አድርጎ አጠቃላይ የተጠቃሚውን ቁጥር አሥር ሚሊዮን እንደሚሆን ተገምቷል፡፡

የጤና መድን አስቀድሞ በሚደረግ አነስተኛ መዋጮ ወይም ክፍያ ግለሰቦች ወይም ቤተሰቦች የጤና መታወክ ባጋጠማቸው ጊዜ፣ ካልታሰበ ከፍተኛ የሕክምና ወጪ የሚጠበቁበት ሥልት እንደሆነ ኤጀንሲው በተለያዩ ወቅቶች ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ የጤና መድን ኤጀንሲ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 191/2003 የተቋቋመ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ተስፋ የተጣለባቸው የንግድ ማዕከላት

ፆም ሲገባ ዋጋቸው ከሚጨምሩ የምግብ ፍጆታዎች ውስጥ አትክልትና ፍራፍሬ ...

የወጣቶችን ፈጠራ የሚያስቃኘው የስታርት አፕ ዓውደ ርዕይ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያዘጋጀው ‹‹ስታርት አፕ ኢትዮጵያ›› ዓውደ ርዕይ...

በግጭት ለተጎዱ ልጆች 80 ሺሕ መጻሕፍት ማሠራጨት መጀመሩን ኢትዮጵያ ሪድስ አስታወቀ

በኢትዮጵያ በግጭት ምክንያት ከትምህርት ቤት ለተስተጓጐሉ፣ በሥነ ልቦናና በሌሎች...

የም እና መስህቦቿ

በቱባ ሀገሬ የም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሚገኝ ሲሆን ከአዲስ አበባ በ239...