Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናፓርላማው ረቂቅ ሕጐችን ከማፅደቁ በፊት በድረ ገጹ ለሕዝብ እንዲደርሱ ሊያደርግ ነው

ፓርላማው ረቂቅ ሕጐችን ከማፅደቁ በፊት በድረ ገጹ ለሕዝብ እንዲደርሱ ሊያደርግ ነው

ቀን:

– ደንቦችንና መመርያዎችን በሦስት ወራት ውስጥ ማውጣት አስገዳጅ ሊሆን ነው

አዋጆች ከመፅደቃቸው በፊት በኅብረተሰቡና በባለድርሻ አካሎች ተሳትፎ እንዲዳብሩ፣ ረቂቅ ሕጐችን እንደ አዲስ እየተሠራ ባለው የፓርላማው ድረ ገጽ ላይ እንዲጫኑ ሊደረግ ነው፡፡

ከፓርላማው ጽሕፈት ቤት ሪፖርተር ያገኛቸው መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በአሁኑ ወቅት ፓርላማው ያለው ድረ ገጽ የፀደቁ ሕጐችን ማግኘት የሚያስችል ነው፡፡ የኅብረተሰቡን ተሳትፎ የበለጠ ለማጐልበትና ረቂቅ ሕጐች ማካተት የሚገባቸውን ሳያካትቱ ሕግ ሆነው እንዳይወጡ ሲባል፣ ረቂቅ ሕጐቹ በድረ ገጽ ወደ ኅብረተሰቡ እንዲደርሱ እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በጥቂት ወራት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባል ተብሎ የሚጠበቀው ድረ ገጽ ረቂቅ አዋጆች እንዲጫኑበት ብቻ የሚያገለግል ሳይሆን፣ በረቂቅ አዋጆቹ ላይ ባለድርሻ አካላትና ማንኛውም ዜጋ አስተያየታቸውን መስጠት ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

ድረ ገጹ በመዘጋጀቱ ምክንያት ፓርላማው የሚያዘጋጃቸው ሕዝባዊ ውይይቶች እንደማይቀሩና ተጨማሪ የሕዝብ ተሳትፎ የሚፈጥር እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሕጐች ፀድቀው በነጋሪት ጋዜጣ ከወጡ በኋላ ደንብ ማውጣት የሚገባው የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ እንዲሁም መመርያዎችን ጨምሮ ዝርዝር ድንጋጌዎችን የማውጣት ኃላፊነት የሚሰጣቸው አስፈጻሚ አካላት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በሦስት ወራት ውስጥ እንዲያወጡ ሊገደዱ ነው፡፡

ግዳጁን የሚጥለው ፓርላማው ሲሆን፣ ይህንንም አስገዳጅ ሁኔታ የመከታተልና የመቆጣጠር ኃላፊነትም ራሱ ፓርላማው ወስዷል፡፡ ፓርላማው ይህንን ያደረገው በተለያዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ምክንያት ደንቦችና መመርያዎች በጊዜ የማይወጡ መሆናቸውን በመለየቱ ነው፡፡  

በኢትዮጵያ ሕግ የአገሪቱ የበላይ ሕግ ከሆነው ሕገ መንግሥት ጋር የሚጋጩ የተዋረድ ሕጎች እንደ ሕግ የማይቆጠሩ ሲሆን፣ ዋናው ሕግ አውጪ አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማው) የሚያወጣው አዋጅ የሚደነግጋቸው ጠቅላላ ሕጎች ላይ፣ ዝርዝር የአፈጻጸም ሁኔታን እንዲወስኑ እንደ አስፈላጊነቱ ሁኔታ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ወይም ለአስተዳደራዊ አካላት ውክልና ሊሰጥ ይችላል፡፡ ይሁንና በአዋጅ የተጣሉ መብቶችና ግዴታዎች በዝርዝር የተዋረድ ሕጎች (ደንብ፣ መመርያ፣ ትዕዛዝ፣ ሰርኩላር ደብዳቤ …) አለመውጣት በጥቅም ላይ ሳይውሉ የቀረቡባቸው አጋጣሚዎች በርካታ ናቸው፡፡ ይህ የሦስት ወራት አስገዳጅ ድንጋጌ ተግባራዊ ከሆነ እነዚህን ችግሮችም ይቀርፋል ተብሎ ተስፋ ተደርጓል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...