Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትየአዲሱ አስመራጭ ኮሚቴ ምርጫና ከጉባዔው የሚጠበቀው

የአዲሱ አስመራጭ ኮሚቴ ምርጫና ከጉባዔው የሚጠበቀው

ቀን:

  • ምርጫው ከግንቦት 26 በፊት እንዲጠናቀቅ ተጠይቋል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቀጣይ አመራርን ለመምረጥ እየተደረገ የነበረው የተንዛዛ አካሄድ ምንም እንኳ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) መፍትሔ ያለውን የውሳኔ ሐሳብ ቢያሳልፍም፣ አሁንም መቋጫውን አላገኘም፡፡ በተለያዩ ግለሰባዊ ፍላጎቶች ፍትጊያዎችን ያስተናገደው ይህ ምርጫ ከበርካታ ባለሙያዎችና አስተያየት ሰጪዎች የሰላ ትችት ሲያስተናግድ ከርሟል፡፡

ትችቶቹ በአገር ውስጥ ባለሙያዎች የሚቀርቡትን ምክረ ሐሳቦች ተቀብሎ ከማስተናገድ ይልቅ የውስጥ ጉዳይን ለዓለም አደባባይ በማቅረብ አሳፋሪ ሒደትን እንዲያስተናግድ ሆኖ ከዚህ ደርሷል፡፡ ከተሞክሮ አሁንም እግር ኳሱ በሚፈልገው አግባብ ቀጣዩ ምርጫ ለመከናወኑ እርግጠኛ መሆን እንደሚከብድ አያጠያይቅም፡፡ ምክንያቱም ፊፋ፣ መጋቢት 26 ቀን 2010 ዓ.ም. የምርጫውን ሒደት አስመልክቶ ባሳሰበው መሠረት ምርጫው የፊፋን የምርጫ ምርት መከተል ይኖርበታል፡፡

ይሁንና ለእግር ኳሱ ዕድገት ምን ዓይነት የጎላ ድርሻና አስተዋጽኦ እንደሚያስፈልግ ከመግለጽ ባለፈ የግለሰቦች ማንነት፣ ፖለቲካዊ ተሳትፎና የብሔር ተዋጽኦን ለማሟላት ሲደረግ የነበረው መሻትን ለመፍታት ያቃተው አስመራጭ ኮሚቴ፣ ጉዳዩ ወደ ፊፋ በተደጋጋሚ በመውሰድ ምርጫው ይደረጋል ተብሎ በይፋ ከተገለጸበት ጥቅምት ወር 2010 ዓ.ም. አንስቶ ያለምንም መፍትሔ ወራትን አስቆጥሮ ዛሬ ላይ እንዲደርስ ምክንያት ሆኖ ቆይቷል፡፡

- Advertisement -

ማንንም ለመስማት ግድ ሳይሰጠው የቆየውን አስመራጭ ኮሚቴ ዕውቅና አንስቷል፡፡ ስብስቡ መልሶ በምትኩ አዲስ አስመራጭ ኮሚቴ እንዲሰይም መጋቢት 26 ቀን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ ምርጫውም ከግንቦት 26 በፊት መጠናቀቅ እንደሚገባው ጭምር ማሳሰቡ ታውቋል፡፡ የፊፋ መልዕክት ዛሬ ላይ ሆነው ለሩሲያው የዓለም ዋንጫ ህልም የነበራቸው የነበሩና አመራሩ አባላት የግል ፍላጎታቸውን ወደ ጎን በማለት ተቋሙም ሕጋዊ ባለቤት ይኖረው ዘንድ ቀና ሊሆኑ እንደሚገባ እየተነገረም ይገኛል፡፡

ምክንያቱም ምርጫው እስካሁን ድረስ እንዲጓተት ያደረገው ኮሚቴ ተበትኖ በምትኩ አዲስ ገለልተኛ አስመራጭ ኮሚቴ እንዲዋቀር ፊፋ ቀጭን ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ይህን ትዕዛዝ በተለያዩ ምክንያታዊ ባልሆኑ ሰበቦች ምርጫውን ማጓተት፣ ማንዛዛትና ማስቀረት አይመስልም፡፡

ሌላው ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ትልቁ የሥልጣን አካል ተደርጎ የሚወስደው፣ ከፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባዔ ብዙ አርቆ አስተዋይነት እንደሚጠበቅበት የሚናገሩ አሉ፡፡ እንደ እነዚህ አስተያየት ሰጪዎች ከሆነ፣ ይህ ጉባዔ ስሙ እንደሚገልጸው የኢትዮጵያ እግር ኳስ የወደፊት አቅጣጫ መሠረት የሚጣልበት ነው፡፡ ነገር ግን እንደ አለመታደል ሆኖ ጉባዔው ለእግር ኳሱ መሠረት ከሚሆኑ ጉዳዮች ይልቅ ‹‹ወንዜነትን›› መነሻ ባደረጉ ለአካባቢያዊ ስሜቶች ቅድሚያ ስለሚጥ የእግር ኳሱ ገመና ከውስጡም አልፎ ለዓለም አቀፍ ተቋም በመጥፎ ምሳሌነት የትኩረት አቅጣጫ እንዲሆን ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ፡፡

ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ከእኛ ይልቅ ፊፋ ሆደ ሰፊ ሆኖ ቀጣይ የአስመራጭ ኮሚቴ ምርጫና ይኼው አካል እንዴትና በምን አግባብ የአስመራጭነት ሚና እንደሚኖረው ለፌዴሬሽኑ በላከው ምላሽ አስቀምጧል፡፡ በምላሹ ካካተታቸው ነጥቦች መካከል ምርጫው ከተጠናቀቀ በኋላ ለምርጫው መጓተትና መንዛዛት እንደ ምክንያት ከሚቀርበው የምርጫ ኮድ (ሥነ ምግባር) ጀምሮ አንዳንድ የፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጾች እንዲሻሻሉ ፍላጎቱ ካለ ሙያዊ ዕገዛ እንደሚያደርግ ቃል መግባቱ ይጠቀሳል፡፡

ፊፋ በአዲስ መልክ እንደገና እንዲዋቀር የሚደረገውን አስመራጭ ኮሚቴ አስመልክቶ ጉባዔው ስያሜውን በሚመጥን መልኩ ከክልልና ብሔር ውክልና የፀዳ፣ ሙያዊ ብቃትን መነሻ ያደረገ፣ ገለልተኛ ከሆነ ተቋም ሰዎች እንዲሰየሙ ይፈልጋል፡፡ በምርጫው መጓተት የተሰላቹ ገለልተኛ ሙያተኞችም ይህ የፊፋ ሥጋት ተወግዶ ትክክለኞቹ ሰዎች በአዲሱ አስመራጭ ኮሚቴ ተካተው ችግሩም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት ማግኘት ይችል ዘንድ ይመኛሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...