Thursday, December 1, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  ካስትል ግሩፕ የዘቢዳር ቢራን 58 በመቶ ድርሻ መግዛቱን ይፋ አደረገ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  ካስትል ግሩፕ የዘቢዳር ቢራ ፋብሪካን 58 በመቶ ድርሻ መግዛቱን ይፋ አደረገ፡፡ ካስትል የቢራ  ፋብሪካውን ድርሻ የገዛው፣ የዘቢዳር ቢራን 60 በመቶ ድርሻ ከያዘውና ዩኒብራ ከተባለው የቤልጅየም ኩባንያ በደረሰው ስምምነት መሠረት እንደሆነ አስታውቋል፡፡

  ከመጋቢት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. ከማርች 28፣ 2018) ጀምሮ ዘቢዳር ቢራ በካስትል ግሩፕ ሥር ከሚገኙ ሌሎች አራት የቢራ ፋብሪካዎች ጋር መቀላቀሉን ካስትል ግሩፕ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ ጠቅሷል፡፡

  ካስትል ግሩፕ በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት በላይ የቆየ ከመሆኑም በላይ፣ ኩባንያው ዛቢዳር ቢራን መግዛቱ በኢትዮጵያ ያለውን የገበያ ድርሻ ለማስፋት ያለውን ዕቅድ አመላቷል፡፡

  የዘቢዳር ቢራ 40 በመቶ ድርሻዎች ዥማር አክስዮን ማኅበር በተሰኘው አገር በቀል ኩባንያ የተያዙ ናቸው፡፡ ዥማር በሥሩ ከ2,000 በላይ ባለአክሲዮኖችን ያቀፈ የንግድ ተቋም ነው፡፡

  spot_img
  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች