Monday, December 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  የዋጋ ግሽበት መጠነኛ መሻሻል አሳየ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  የመጋቢት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 15.2 በመቶ ተመዘገበ፡፡ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ባወጣው ሪፖርት እንደተመለከተው የዋጋ ግሽበቱ መጠነኛ የሆነ መሻሻል አሳይቷል፡፡  

  በዚህም መሠረት የመጋቢት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ከየካቲት ወር ጋር ሲነፃፀር መጠነኛ መሻሻል ታይቷል፡፡ የካቲት ወር የዋጋ ግሽበት 15.6 በመቶ ደርሶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

  በመጋቢት ወር የምግብ የዋጋ ግሽበት 19.9 በመቶ ሲመዘገብ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች ዋጋ ደግሞ አሥር በመቶ ከፍ ብሏል፡፡ በተለይም ምግብ ነክ ያልሆኑ የግንባታ ግብዓት የሆኑት የሲሚንቶና የብረት ዋጋዎች ላይ ጭማሪዎች ታይተዋል፡፡

  ለግንባታ ግብዓቶች ዋጋ መጨመር በዋናነት የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንደ ምክንያት ይጠቀሳል፡፡ በተጨማሪም ከምግብ ነክ ምርቶች ጋር በተያያዘ ከየካቲት ወር ጋር ሲተያይ የእህል ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ የአትክልት፣ የጥራጥሬና የፍራፍሬ ዋጋ ላይ መጠነኛ የሚባል ጭማሪ ተመዝግቧል፡፡

  ባለፉት ወራት በአገሪቱ ተከስቶ በነበረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ሳቢያ የምግብ ምርቶችን ከቦታ ወደ ቦታ ማዘዋወር ባለመቻሉ ለዋጋ ግሽበት ዋነኛ ምክንያት መሆኑ አይዘነጋም፡፡  

  spot_img
  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች