Tuesday, April 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናግብፅ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲዘገይ ጠየቀች

ግብፅ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲዘገይ ጠየቀች

ቀን:

ግብፅ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲዘገይ ጠየቀች

ኢትዮጵያ የታላቁን ህዳሴ ግድብ ግንባታ እንድታዘገይ ግብፅ በድጋሚ ጠየቀች፡፡ የግብፅ የውኃና፣ መስኖ ሚኒስትር አማካሪ መግሐውሪ ሽታት ከግብፅ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያ ሆን ብላ የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን የጋራ ቴክኒክ ኮሚቴን ውይይት እያዘገየች ነው ሲሉም ወቅሰዋል፡፡

አማካሪው እንደሚሉት ላለፉት ስድስት ወራት በጋራ ቴክኒክ ኮሚቴው ሲካሄድ የከረመው ውይይት በአንድ ወር ውስጥ መጠናቀቅ ነበረበት፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ባለፈው እሑድ ይጀመራል ተብሎ የነበረው የሦስቱ አገሮች የስድስት ሚኒስትሮች የጋራ ስብሰባ፣ ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር በነበረባት ሌላ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሳቢያ ለቀጣዩ ሳምንት እንዲተላለፍ በመጠየቋ ተላልፏል፡፡

በተደጋጋሚ ውይይቶች እየተላለፉ ወደ ውጤት መምጣት ባለመቻሉ የግብፅን ጥቅም የሚጎዳ ነው ያሉት አማካሪው፣ ጥናቱ ቢካሄድም በአሁኑ ወቅት የግድብ ግንባታው ካልቆመ በጥናቱ የሚገኘውን ምክረ ሐሳብ ማካተት አይቻልም ሲሉም ተከራክረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የግድብ ግንባታውን እንድታዘገይ የጠየቁት አማካሪው፣ በዚህ ለሚደርስባት ጉዳት ግብፅ ካሳ እንደምትከፍልም አመልክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በበኩሏ ጥናት እንዲደረግባቸው የተባሉት ሁለት ምክረ ሐሳቦች ቀደም ብለው የተጠኑ መሆናቸውን በማስታወስ፣ በድጋሚ የሚጠኑበት ምክንያት በሦስቱ አገሮች መካከል መተማመን ለመፍጠር በመሆኑ የግድቡ ግንባታ ይቁም የሚል ጥያቄ ተሰሚነት እንደሌለው ይፋዊ አቋም ይዛለች፡፡

ሌሎች ባለሙያዎች ደግሞ ከቀረቡት ሁለት ምክረ ሐሳቦች መካከል ዋነኛ የሚባለው የግድቡ ውኃ አያያዝና አለቃቀቅ (ኃይድሮ ሲሙሌሽን ሞዴል) በመሆኑ፣ የግድቡ ግንባታ መዘግየት ወይም መፍጠን የሚጎዳ የሚጠቅም ባለመሆኑ ተቀባይነት የሚኖረው ጥያቄ እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...