Sunday, September 25, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊመንግሥት ስምንት ቢሊዮን ዶላር ለሚፈጀው ፕሮጀክት 600 ሚሊዮን ዶላር ብድር አገኘ

  መንግሥት ስምንት ቢሊዮን ዶላር ለሚፈጀው ፕሮጀክት 600 ሚሊዮን ዶላር ብድር አገኘ

  ቀን:

  – ፓርላማው ሌሎች ብድሮችንም አፅድቋል

  ከ1997 ዓ.ም. ወዲህ በዓለም ባንክ በኩል ለተጀመረው የመሠረታዊ አገልግሎቶች ከለላ ድጋፍን ለሚተካው ‹‹ፍትሐዊ መሠረታዊ አገልግሎት ለጋራ ዕድገትና ተጠቃሚነት›› ፕሮጀክት፣ የዓለም ባንክ ዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር (IDA) የፈቀደውን 600 ሚሊዮን ዶላር ብድር ፓርላማው አፀደቀ፡፡

  ዓለም አቀፍ ለጋሾች እስከ 1997 ዓ.ም. ድረስ ለኢትዮጵያ ይሰጡ የነበረውን ቀጥታ የበጀት ድጋፍ በማቋረጥ፣ በፌዴራል መንግሥቱ አማካይነት ለክልሎች የሚተላለፍ የመሠረታዊ አገልግሎቶች ከለላ ፕሮግራም ላለፉት አሥር ዓመታት በዓለም ባንክ አማካይነት ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡

  የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን ፕሮግራም የሚተካ ከመስከረም 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ተግባራዊ የሚደረግ የ8.1 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ቀርጿል፡፡

  የፕሮጀክቱ ስያሜ ‹‹ፍትሐዊ መሠረታዊ አገልግሎት ለጋራ ዕድገትና ተጠቃሚነት›› የተሰኘ ሲሆን፣ ዓላማውም ለኅብረተሰቡ የሚሰጡ የመሠረታዊ አገልግሎቶችን ተደራሽነትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ማሻሻልና የአገልግሎት አሰጣጥ የተጠያቂነት ሥርዓት እንዲጠናከር የሚያግዝ መሆኑን፣ ለፓርላማ የቀረበው ማብራሪያ ያስረዳል፡፡

  ለአጠቃላይ ፕሮጀክቱ ከሚጠይቀው 8.1 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 73.4 በመቶ የሚሆነው፣ ማለትም 5.8 ቢሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ መንግሥት የሚሸፈን ሲሆን፣ ቀሪው በዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች የሚሸፈን ነው፡፡

  ከዓለም አቀፍ አበዳሪዎች ግንባር ቀደም የሆነው የዓለም ባንክ 600 ሚሊዮን ዶላር ከወለድ ነፃ ብድር ለመስጠት ከገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ጋር የተፈራረመ ሲሆን፣ ፓርላማውም ኅዳር 28 ቀን 2008 ዓ.ም. በሁለተኛ ንባብ (ለቋሚ ኮሚቴ ሳይመራ) አፅድቆታል፡፡

  የዓለም ባንክ ብድሩን የሚለቀው በየስድስት ወራት በሚያደርገው ግምገማ ነው፡፡ ለግምገማ ከተቀመጡት መመዘኛዎች መካከል አንደኛው ለክልሎች የሚተላለፈው የነፍስ ወከፍ ድጐማ በጀት ዕድገት፣ በዲፕሎማ ደረጃ የሠለጠኑ የሴት የግብርና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ቁጥር መጨመር፣ ከ5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል የተመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር መጨመር የሚሉ ይገኙበታል፡፡ የተሰጠው ብድር የስድስት ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ38 ዓመት ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው፡፡

  ፓርላማው ኅዳር 28 ቀን 2008 ዓ.ም. ሌሎች ሦስት የብድር ስምምነቶችንም አፅድቋል፡፡ አንደኛው ለጣና በለስ የተቀናጀ የውኃ ልማት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል የ5.1 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ብድር ነው፡፡ ብድሩ ከዓለም ባንክ ዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር (IDA) የተገኘ ሲሆን፣ ይኼው ተቋም ለዚሁ ፕሮጀክት ከዚህ ቀደም 45 ሚሊዮን ዶላር አበድሮ ነበር፡፡ ሌሎቹ ሁለት ብድሮች ከፈረንሣይ የልማት ኤጀንሲና ከጣሊያን መንግሥት ለአነስተኛና ለመካከለኛ ከተሞች የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ማስፈጸሚያ የተገኙ ናቸው፡፡ እንደ ቅደም ተከተላቸውም የብድሮቹ መጠን 20 ሚሊዮን ዶላርና 15 ሚሊዮን ዶላር ሲሆኑ፣ ከፈረንሣይ የተገኘው ከሰባት ዓመት የችሮታ ጊዜ በኋላ በ18 ዓመት ተከፍሎ የሚያልቅ 1.72 በመቶ ወለድ የሚከፈልበት ብድር ነው፡፡

  ከጣሊያን የተገኘው 15 ሚሊዮን ዶላር ብድር የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ40 ዓመት ተከፍሎ የሚያልቅ ከወለድ ነፃ ብድር ነው፡፡   

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኢትዮጵያ ላይ የቀጠለው የምዕራባውያን ጣልቃ ገብነት

  ምዕራባውያን አገሮች በኢትዮጵያ ላይ ጠንካራ ጫና ማሳደራቸውን ቀጥለዋል፡፡ በዲፕሎማሲም...

  የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የድጎማ በጀት ለፖለቲካ ሥራ ማስፈጸሚያ እንደሚውል የሚያሳይ ሪፖርት ቀረበ

  ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚደረግ የበጀት ድጎማ ከመደበኛው ሥራ ይልቅ ከዋናው...

  መንግሥት የሥራ ግብር ምጣኔን እንዲቀንስ ተጠየቀ

  የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) መንግሥት የሠራተኛውን የኑሮ ጫና...

  የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የአመራሮች ምርጫና ቀጣይ ዕቅዶቹ

  የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ሲጠበቅ የነበረውን...