Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከድህነት ወለል በታች የሚገኙ ነዋሪዎችን አንድ ዕርምጃ ለማሻገር

ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ ነዋሪዎችን አንድ ዕርምጃ ለማሻገር

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ድሪባ ኩማ ረቡዕ ሚያዝያ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. አስተዳደራቸው ጉልህ ሥፍራ ከሚሰጣቸው ፕሮግራሞች አንዱን ጎብኝተዋል፡፡ ከንቲባ ድሪባ ከከፍተኛ የከተማው ባለሥልጣናት ጋር ሆነው የጎበኙት በአዲስ አበባ ከተማ ከደኅንነት ወለል በታች የሚገኙ ነዋሪዎችን ለማቋቋም በዓለም ባንክ የሚደገፈውን ግዙፍ ፕሮግራም ነው፡፡ ይህ ፕሮግራም በ2009 ዓ.ም. የተጀመረ ሲሆን 123 ሺሕ ተጠቃሚዎችን አቅፏል፡፡ በዚህ ዓመት ደግሞ ይህ ቁጥር ወደ 200 ሺሕ የሚያድግ ሲሆን፣ የደሃ ደሃ የተባሉ ነዋሪዎች በሁለት መንገድ ለማቋቋም ያለመ ነው፡፡ የመጀመርያው አቅም እያላቸው የሥራ ዕድል ያልተፈጠረላቸውን ነዋሪዎች በአካባቢ ፅዳት፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በተፋሰስ ልማት፣ በከተማ ግብርና ልማትና በመሳሰሉት ዘርፎች በማሰማራት ክፍያ እንዲያገኙ ማድረግ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ አቅመ ደካማ የሆኑ ነዋሪዎችን ቀጥታ የደመወዝ ተከፋይ በማድረግ ኑሮአቸው እንዲስተካከል ማድረግ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ ጉብኝቱ ከተካሄደባቸው ቦታዎች መካከል በጉለሌ ክፍለ ከተማ ጫካ ሚካኤል አካባቢ 21 ሔክታር መሬት ላይ የተሠሩ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች ይገኙበታል፡፡ ከንቲባ ድሪባ ፕሮግራሙ መልካም ጅማሮ ማሳየቱን ሲገልጹ፣ በፕሮግራሙ የታቀፉ ነዋሪዎች ደግሞ ክፍያው አነስተኛ መሆኑን በመግለጽ እንዲሻሻል ጠይቀዋል፡፡ ከንቲባው የነዋሪዎችን ጥያቄ በመቀበል በቅርቡ ክፍያው በ15 በመቶ እንደሚያድግ ተናግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ በአገር አቀፍ ደረጃ የከተሞች የምግብ ዋስትና ፕሮግራም የተዘረጋ ሲሆን፣ ከመንግሥትና ከዓለም ባንክ 450 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተመደበለት ግዙፍ ፕሮግራም ነው፡፡ በምሥሉ ላይ ከንቲባ ድሪባ ኩማና የሥራ ባልደረቦቻቸው የተፋሰስ ልማት ሥራዎችን ሲጎበኙ ይታያል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...