Wednesday, December 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናበሽብር ወንጀል ተግባር ተጠርጥረው የተከሰሱት የዋልድባ መነኮሳት ከእስር ተፈቱ

  በሽብር ወንጀል ተግባር ተጠርጥረው የተከሰሱት የዋልድባ መነኮሳት ከእስር ተፈቱ

  ቀን:

  ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ድርጅት የገንዘብ ዕርዳታ በማድረግና ሌሎች የሽብር ወንጀል ተግባር ተጠቅሶባቸው ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩት ሁለት የዋልድባ መነኮሳት፣ መንግሥት ክሳቸው እንዲቋረጥ በማድረጉ ዓርብ ሚያዝያ 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ከእስር ተፈቱ፡፡ የሌሎች 112 ተከሳሾችም ክስ በመቋረጡ ከእስር ተፈተዋል፡፡

  ሁለቱ መነኮሳት አባ ገብረ ሥላሴ ወልደ ሃይማኖትና አባ ገብረ የሱስ ኪዳነ ማርያም የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የመሠረተባቸውን ክስ እንደማይቃወሙ፣ ክሱን እየመረመረው ለነበረው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ገልጸው ነበር፡፡ በመሆኑም ዓቃቤ ሕግ ምስክሮቹን እንዲያሰማ ለሚያዝያ 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡

  ነገር ግን የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለ17 ቀናት ካደረገው ስብሰባና ውሳኔ በኋላ ታኅሳስ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው የሚገኙና ፍርድ አርፎባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙ እስረኞችን ክስ እንደሚያቋርጥና ይቅርታ እንደሚያደርግ በተናገረው መሠረት፣ የመነኮሳቱና የሌሎች 112 ተከሳሾች ክስ ተቋርጦ ከእስር ተፈተዋል፡፡

  መነኮሳቱ በ2008 ዓ.ም. መጨረሻ ወራት አካባቢ በቁጥጥር ሥር ውለው አንድ ዓመት ከአራት ወራት መታሰራቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹እኛ የዓለም ጉዳይ በቅቶን ራሳችንን አስረን ባለንበት ወቅት እንዴት ለሌላ እስር እንዳረጋለን?›› በማለት የሚጠይቁት መነኮሳቱ፣ የዓለም ነገር የማያጓጓቸውና እነሱ ከታሰሩ ሌሎች ቢታሰሩ ብዙ ሊደንቅ እንደማይገባ ገልጸዋል፡፡ ለሁሉም የሚበጀው ማሰርና መታሰር ሳይሆን በፍቅርና በመተባበር ኢትዮጵያን ወደፊት ማራመድ እንደሆነ መነኮሳቱ ተናግረዋል፡፡ በተለያየ የወንጀል ድርጊት ተጠርጥረው ታስረው የነበሩ 112 ግለሰቦችም ክሳቸው ተቋርጦ ተለቀዋል፡፡    

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ...