የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ሠራተኞች በማመፃቸው ምክንያት በቦሌ ዓለም አቀፍ ኢንተርናሽናል አውሮፕላን ማረፊያ ተቋርጠው የነበሩ በረራዎች ቀጠሉ፡፡
ዛሬ ሚያዝያ 9 ቀን 2010 ዓ.ም. የበረራ ተቆጣጣሪ ሠራተኞች በማመፃቸው ለአንድ ሰዓት ከአውሮፕላን ማረፊያው የሚነሱ በረራዎች ተስተጓጉለው ነበር፡፡ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው ለኢቢሲ እንደገለጹት፣ ሠራተኞቹ በረራውን ሊያስተጓጉሉት የቻሉት ከትርፍ ሰዓት አከፋፈል ጋር በተፈጠረ ውዝግብ ነው፡፡ ሠራተኞቹ ለበዓል የሠሩበት ክፍያ ካልተከፈለን በማለት ማመፃቸውን አስታውቀዋል፡፡