Saturday, December 9, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

ክቡር ሚኒስትሩ አማካሪያቸውን ቢሯቸው ያስጠሩታል

[ክቡር ሚኒስትሩ ከአንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ጋር ተገናኝተው እያወሩ ነው]

 • ስለተገናኘን ተደስቻለሁ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እኛ እኮ ወንድማማቾች ነን፡፡
 • እርስዎም ተቀይረዋል፡፡
 • ምን እያልከኝ ነው?
 • ማለቴ ከልብዎ ነው?
 • ከልቤ ስለሆነ መሰለኝ ያገኘሁህ?
 • ስለዚህ እንደ ድሮው ጠላቶች አይደለንም?
 • የምን ጠላትነት አመጣህ?
 • ክቡር ሚኒስትር እኔ እኮ ከቤቴ ይልቅ እስር ቤቱን ነው በደንብ የማውቀው?
 • እሱ የድሮ ታሪክ ነው፡፡
 • ያው እናንተ ስለማትታመኑ ነው፡፡
 • አሁን በአዲስ መልክ ነው ሥራ የጀመርነው፡፡
 • ልክ እንደ ምግብ ቤት?
 • ቀልዱን ትተህ ወደ ቁም ነገር እንግባ፡፡
 • ምን ላድርግ ከእናንተ ተምረን እኮ ነው?
 • ምንድነው ያስተማርናችሁ?
 • መቀለድ ነዋ፡፡
 • የምን ቀልድ ነው?
 • ይኸው ላለፉት 27 ዓመታት ስትቀልዱብን ነበር፡፡
 • ምን አድርገን?
 • የፖለቲካ ምኅዳሩ ሰፍቷል ብላችሁ ሳትጨርሱ በጣም ጠባብ ጨለማ ቤት ውስጥ ትከቱናላችሁ፡፡
 • በቃ የድሮ አልፏል አልኩህ እኮ?
 • አይ ክቡር ሚኒስትር ይተውት እስቲ፡፡
 • ምን ሆነሃል?
 • ብዙ ጊዜ ነው እንደዚህ ያላችሁን፡፡
 • አሁን ግን ከልባችን ነው፡፡
 • ለነገሩ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከልባቸው ይመስላል፡፡
 • ባለፈው የራት ግብዣው ላይ ነበርክ አይደል?
 • እጄ እስኪላጥ ሲያስጨበጭቡኝ ነበር፡፡
 • ታዲያ ንግግራቸው የሚታመን አይደለም?
 • የሚያወሩት ነገርማ በጣም ደስ የሚል ነው፡፡
 • ወደድከው አይደል?
 • እሳቸው ራሳቸው ተቃዋሚ ነው የሚመስሉት፡፡
 • ለምን እንዲህ አልክ?
 • በቃ የእኛን አጀንዳ ነበራ የሚያወሩት፡፡
 • አሁን የፖለቲካ ምኅዳሩን ለማስፋት ቆርጠን ተነስተናል፡፡
 • የጠቅላይ ሚኒስትሩ አካሄድ ግን አሳስቦናል፡፡
 • ምኑ ነው ያሳሰባችሁ?
 • የሚያወሩትን ነገር ይተገብሩታል ወይ የሚለው ነዋ፡፡
 • አትጠራጠር ይተገበራል፡፡
 • መተግበሩ ግን እኛን ያሳስበናል፡፡
 • እንዴት ሆኖ?
 • ለዓመታት የታገልንባቸውን አጀንዳዎች ያስጥለናላ፡፡
 • ታዲያ የምትታገሉት ለዚህ አይደል እንዴ?
 • ሁሉንም አጀንዳዎቻችንን ወስደው እኛን ባዶ ሊያስቀሩን ነው እኮ?
 • ምን ችግር አለው ታዲያ?
 • ከዚያ በኋላ እኛን ማን ሊሰማን ነው?
 • የሕዝብን ድጋፍ ለማግኘት እናንተም ጠንክራችሁ መሥራት አለባችኋ?
 • ለማንኛውም አጀንዳዎቻችን እየተወሰዱብን ስለሆነ በቅርቡ መጠየቃችን አይቀርም፡፡
 • ምንድነው የምትጠይቁት?
 • ፍትሐዊ የአጀንዳ ክፍፍል!

[ክቡር ሚኒስትሩ አማካሪያቸውን ቢሯቸው ያስጠሩታል]

 • ምንድነው የሚፈልጉት?
 • እነማን ክቡር ሚኒስትር?
 • እነዚህ ኒዮሊብራሎች ናቸዋ፡፡
 • ይረጋጉ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እንዴት ነው የምረጋጋው?
 • በጣም ተናደዋል እኮ፡፡
 • እንዴት አልናደድ ታዲያ?
 • ምን ተፈጥሮ ነው ለመሆኑ?
 • አሁን አንተም አማካሪ ተብለህ ደመወዝ ይከፈልሃል?
 • ይቅርታ ክቡር ሚኒስትር?
 • አሜሪካኖቹ አፀደቁት እኮ፡፡
 • ምኑን?
 • የአቋም መግለጫውን ነዋ፡፡
 • እነሱ ደግሞ ወዳጅ መስለው ከኋላ ነው የሚወጉት፡፡
 • በጣም ነው ያዘንኩት፡፡
 • የሚያሳዝነው ደግሞ ክቡር ሚኒስትር፣ አዳዲስ ለውጦችን እያመጣንበት ባለበት ወቅት ማፅደቃቸው ነው፡፡
 • እኛ እኮ ወሳኝ አጋራቸው መሆናቸውን ይረሱታል ልበል?
 • የሚፈልጉትን ግን እያደረግንላቸው አይደል እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
 • እነሱ እኛን የሚፈልጉት ለመጋለብ ነዋ፡፡
 • እሱንማ ማድረግ አይችሉም፡፡
 • አሁን እኮ ስማችንን ሊያጠፉት ነው፡፡
 • እንዴት አድርገው?
 • ይኸው አገሪቱ ውስጥ ዴሞክራሲ ቅብርጥሶ የለም እያሉ ነዋ፡፡
 • እንዴ ክቡር ሚኒስትር ዴሞክራሲ በአገሪቷ ስለሰፈነ እኮ ነው የዓለማችን ዕውቁ ተጫዋች ሳይቀር ኢትዮጵያን ጎብኝቶ የሄደው?
 • እነሱ መቼ ይገባቸዋል?
 • ታዲያ ተጫዋቹ በዓለም ታዋቂ ስለሆነ ለምን ስለኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊነት እንዲያወራ አናስደርገውም?
 • ተጫዋቹም ቢሆን እንደዚያ አያደርግልንም፡፡
 • ምን ተሻለ ታዲያ ክቡር ሚኒስትር?
 • እኛም ተመሳሳይ የአቋም መግለጫ ማውጣት አለብን፡፡
 • እስማማለሁ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • የአቋም መግለጫው እኮ ወደፊት ሕግ ሆኖ ከወጣ ለእኛም ሥጋት አለው፡፡
 • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
 • ወደ አሜሪካ እንደፈለግን መሄድ አንችልማ፡፡
 • እሱማ ልክ ነው፡፡
 • በዚያ ላይ አሜሪካም ሀብታችንን ማስቀመጥ አንችልም፡፡
 • አሳሳቢ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ከዚያም አልፎ ተርፎ ቤተሰቦቻችንም አሜሪካ ላይገቡ ይችላሉ፡፡
 • ታዲያ ምን ተሻለ?
 • እኛም አሜሪካኖቹ በሶሪያ የሚሠሩትን ግፍ ካላቆሙ ተመሳሳይ ዕርምጃ እንወስዳለን እንበላ፡፡
 • ምን ዓይነት ዕርምጃ?
 • የአሜሪካ ባለሥልጣናት ወደ ኢትዮጵያ መግባት አይችሉም፡፡
 • እ…
 • አንድም ዶላር በኢትዮጵያ ባንክ ውስጥ ማስቀመጥ አይችሉም፡፡
 • እኛ ግን የዶላር እጥረት አለብን እኮ፡፡
 • አይቻልም አልኩህ አይቻልም፡፡
 • እሺ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ስለዚህ አሁን የነገርኩህን ነገር እንደ አቋም መግለጫ አድርገህ አዘጋጀው፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር ይህ ግን የአቋም መግለጫ መሆን አይችልም፡፡
 • ታዲያ ምንድነው?
 • የምኞት መግለጫ!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚስታቸው ጋር እያወሩ ነው]

 • የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ሰማኸው?
 • የትኛውን?
 • ከባለሀብቶች ጋር ያደረጉትን ነዋ፡፡
 • እዚያ ነበርኩ እኮ፡፡
 • ታዲያ ምን እያሰብክ ነው?
 • ስለምኑ?
 • ከተናገሩት ውስጥ በአብዛኛው አንተን የሚመለከት ነው፡፡
 • እሱንማ አውቃለሁ፡፡
 • ከሁሉም በላይ የብላክ ማርኬቱ ጉዳይ ነው ያሳሰበኝ፡፡
 • ምኑ ነው ያሳሰበሽ?
 • ከሁሉም ቢዝነሳችን እኮ አሁን ጥሩ ትርፍ እያገኘን ያለነው ከብላክ ማርኬት ቢዝነስ ነው፡፡
 • እሱማ ልክ ነሽ፡፡
 • ዕርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ጠቁመዋል እኮ፡፡
 • ከዚህ በኋላ በጣም በጥንቃቄ መሥራት አለብን፡፡
 • ደግሞ ውጭ ያላችሁን ዶላር እንድታስገቡ ብለዋል፡፡
 • እሱን እንኳን ማስገደድ ስለማይችሉ ችግር የለውም፡፡
 • እዚህ የቀረችንንም ራሱ በአፋጣኝ ማውጣት ነው ያለብን፡፡
 • እኔ እንዴት እንደምናወጣው ነው የጨነቀኝ?
 • አንድ አፍታ ወጣ ብለህ ለምን አትመጣም?
 • የውጭ ጉዞ ራሱ ተከልክሏል፡፡
 • ለተቃዋሚዎቹ ምኅዳሩ ሲሰፋ ለእናንተ ግን እየጠበበ ነው፡፡
 • ከዚህ በኋላማ የባሰ እየጠበበ ነው የሚመጣው፡፡
 • ምርጫውንስ ምን ልታደርግ ነው?
 • ምርጫው እኮ ተራዝሟል፡፡
 • የትኛው ምርጫ?
 • የአዲስ አበባን ምርጫ ነው የምትይኝ?
 • ኧረ ከሚኒስትርነት ወይም ከኢንቨስትመንት የተባለውን ነው እንጂ?
 • ከሁሉ በላይ የጨነቀኝ እሱ ነው፡፡
 • አንተ ግን የምትመርጠው መቼም ግልጽ ነው፡፡
 • የትኛውን ልምረጥ?
 • እንዲህ ተንቀባረን የምንኖረው በምን እንደሆነ ታውቃለህ?
 • ሚኒስትር ስለሆንኩ ነዋ፡፡
 • አትሳሳት፣ ኢንቨስተር ባትሆን ኖሮ የትም መድረስ አንችልም ነበር፡፡
 • እና ኢንቨስተርነቱ ይሻልሃል እያልሽኝ ነው?
 • ከእሱ ሌላማ ምርጫ ሊኖርህ አይገባም፡፡
 • ኢንቨስተር እንድሆን ያደረገኝ እኮ የሚኒስትርነት ማዕረጉ ነው፡፡
 • ምንም ብትለኝ ዋናው ውጤቱ ነው፡፡
 • እኔ ግን ተራ ኢንቨስተር መሆን አልፈልግም፡፡
 • ምን እያልክ ነው?
 • ሚኒስትር የምትለውን ስም ግን እፈልጋታለሁ፡፡
 • ኢንቨስተርነቱን ምረጥና ስሙ የሚገባበትን ዘዴ እንፈልጋለና፡፡
 • የምን ዘዴ?
 • እንደ ጓደኞችህ ኢንቨስተርነቱን በማዕረግ እንዲሰጡ ማድረግ ነዋ፡፡
 • በምን ማዕረግ?
 • በሚኒስትር ማዕረግ!

[ለክቡር ሚኒስትሩ ደላላ ወዳጃቸው ደወለላቸው]

 • ሰላም ነህ ወዳጄ?
 • ምን ሰላም አለ ክቡር ሚኒስትር?
 • ምን ሆንክ ደግሞ?
 • ኧረ እንቅልፍ እምቢ ካለኝ ሰነባበትኩ፡፡
 • ለምን እምቢ አለህ?
 • እርስዎ እየተኙ ነው?
 • እኔማ ስንት ኃላፊነት አለብኝ፡፡
 • የመዝረፍ ኃላፊነት ነው?
 • አንተ ደግሞ ልቅ ነህ፡፡
 • ምንም እኮ ሊያምረኝ አልቻለም፡፡
 • ምኑ ነው ያላማረህ?
 • የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አካሄድ፡፡
 • እንዴት?
 • የሚያወራው ሁሉ ስለእኛ እየመሰለኝ መተኛት አልቻልኩም፡፡
 • እ…
 • በፊት እንኳን ስትጠሩት ሙስና ነበር የምትሉት፡፡
 • አሁንስ?
 • ይኸው ሌብነት እያለው እያስቃዠኝ ነው፡፡
 • ምን ታደርገዋለህ?
 • በተለይ የእርስዎ ጉዳይ በጣም አሳስቦኛል፡፡
 • እንዴት ማለት?
 • እንዳይቀደሙ እየፈራሁ ነው፡፡
 • እኔም እያሰብኩበት ነው፡፡
 • ምን ሊያደርጉ?
 • ሳልቀደም ልቀድም ነዋ፡፡
 • አልገባኝም?
 • ላስገባ ነው፡፡
 • ምንድነው የሚያስገቡት?
 • የሥራ መልቀቂያ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ በግሉ ኢንሹራንስ ዘርፍ ሁለተኛውን የገበያ ድርሻ ለመያዝ ያስቻለውን ውጤት ማስመዝገቡን ገለጸ

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ የባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት፣ የመለዋወጫ ዕቃዎች...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ ነው? እንዴት? አለቃዬ ዕረፍት የለው፣ እኔንም አላፈናፍን ብሎኛል። ታድለሽ። ታድለሽ? ሥራ ገደለኝ ዕረፍት አጣሁ እኮ ነው ያልኩሽ? ገብቶኛል። ምነው እኔንም...

[ክቡር ሚኒስትሩ የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸማቸውን ለተከበረው ምክር ቤት ካቀረቡ በኋላ ከምክር ቤቱ አባላት የሚነሱ ጥያቄዎችን እየተቀበሉ ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው]

ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ለሕዝብ ይፋ ያደረገው ነገር ከምን እንደደረሰ ቢያብራሩልን? ምንድነው ይፋ ያደረገው? ጥያቄውን ትንሽ ቢያብራሩት? ከአራት ዓመት በፊት በኦጋዴን አካባቢ ነዳጅ መገኘቱን ለሕዝብ በቴሌቪዥን አብስሮ...

[ክቡር ሚኒስትሩ አንድ የካቢኔና የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ አባል የሆኑ ከፍተኛ አመራር የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያደመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረግህ፣ ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...