Friday, February 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት ጥረት ሲደረግ ባለሥልጣናት ጣልቃ እንደሚገቡ ተጠቆመ

ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት ጥረት ሲደረግ ባለሥልጣናት ጣልቃ እንደሚገቡ ተጠቆመ

ቀን:

‹‹ኢንቨስተር ነው ዳያስፖራ ነው እየተባለ ጫና ይደርስብናል›› የገቢዎችና ጉምሩክ ኃላፊዎች

የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሥራ ኃላፊዎች ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር በአገሪቱ ውስጥ መኖሩ የማይካድ መሆኑን፣ ለፓርላማው የበጀትና የፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳወቁ፡፡ የባለሥልጣናት ጣልቃ ገብነት መኖሩንም ተናገሩ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የባለሥልጣኑን የ2008 ዓ.ም. ዕቅዱና የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ባለፈው ሰኞ ታኅሳስ 4 ቀን 2008 ዓ.ም. ባዳመጠበት ወቅት፣ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርን በተመለከተ ባለሥልጣኑ ምን እያደረገ እንደሆነ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጥያቄ ቀርቦለት ነበር፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በጉዳዩ ላይ ምላሽ መስጠት የጀመሩት የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አለባቸው ዋሲሁን፣ በዋናነት ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርን መግታት የሚመለከታቸው ብሔራዊ ባንክና የፋይናንስ ደኅንነት ማዕከል መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ገቢዎችና ጉምሩክ ደግሞ የማስፈጸም ኃላፊነትን በጉምሩክ ጣቢያዎች ወይም በመግቢያና መውጫ በሮች ላይ በመቆጣጠር እንደሚወጣ ገልጸዋል፡፡

ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር መኖሩን የባለሥልጣኑ ኃላፊ ገልጸው፣ ቁጥጥር በሚደረግበት ወቅት ግን ከተለያዩ አካላት ጫና እንደሚገጥማቸው ተናግረዋል፡፡

በዋናነት ሦስት መውጫና መግቢያ በሮች እንዳሉ የገለጹት አቶ አለባቸው፣ የመጀመርያው ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደሆነ፣ ሁለተኛው ነገር ግን ዋናውና ሰፊው የጂቡቲ ጋላፊ ጠረፍ ጉምሩክ በር መሆኑን፣ ሌላኛው ደግሞ የሞያሌና የሱዳን በሮች እንደሆኑ ጠቁመዋል፡፡

በቦሌ አውፕላን ማረፊያ በኩል ያለው በቂ ቁጥጥር እንደሚደረግበትና ውጤታማ ሥራ የሚሠራበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዋናው ችግር ያለው በጂቡቲ ጋላፊ በር በኩል መሆኑን የሚናገሩት አቶ አለባቸው፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ ከብሔራዊ ባንክ፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ፣ ከንግድ ሚኒስቴር የተውጣጣ ቡድን ችግሩን ለመቅረፍ ኃላፊነት እንደተሰጠው ተናግረዋል፡፡

በየቀኑ 2,200 ተሽከርካሪዎች ወደ ጂቡቲ ከኢትዮጵያ የሚገቡ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊው፣ ለዚህ ሁሉ የውጭ ምንዛሪ ማቅረብ ባለመቻሉ በሁለቱ አገሮች የቆየ ስምምነት እስከ 200 ብር ድረስ በጂቡቲ ውስጥ ግብይት ለማድረግ መፈቀዱን፣ በኢትዮጵያም በኩል እንዲሁ እንዲሆን መደረጉን ተናግረዋል፡፡

አሁን ይህ 200 ብር ከበቂ በታች በመሆኑ የተዋቀረው ኮሚቴ የመፍትሔ ሐሳብ ይዞ እንዲቀርብ ኃላፊነት እንደተሰጠው ገልጸዋል፡፡

ሌሎቹ መውጫ በሮች ሞያሌና ሱዳን ቢሆኑም የከፋ ዝውውር እንደሌለ አቶ አለባቸው ከጠቆሙ በኋላ፣ ‹‹ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ግን በኢትዮጵያ አለ፡፡ ይህ አይካድም፤›› ብለዋል፡፡

የአቶ አለባቸው የሥራ ባልደረባ የሆኑት ሌላ ኃላፊ በበኩላቸው ይህንን ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ለመግታት ኃላፊነት የተሰጠው ብሔራዊ ባንክ ቢሆንም አስፈጻሚው ጉምሩክ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህንን ኃላፊነት ከፌዴራል ፖሊስ ጋር በመሆን በመውጣት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

‹‹በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የውጭ አገር ገንዘቦች ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህን በምንይዘበት ወቅት ኢንቨስተር ነው፣ ዳያስፖራ ነው እየተባለ ከተለያዩ (የመንግሥት) አካላት ጫና ይደርስብናል፤›› ብለዋል፡፡

‹‹ይህንን የማነሳው ቋሚ ኮሚቴው ድጋፍ እንዲያደርግልን ብዬ ነው፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በርካታ የሥራ አፈጻጸሞች ላይ አድናቆቱን ገልጾ፣ ትኩረት ይሻሉ ባላቸው ጉዳዮች ላይም አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል...

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የፈጠሩት አምቧጓሮ

ባለፈው ቅዳሜና እሑድ በአዲስ አበባ የተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት 37ኛው...

የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ትግበራ የፈጠራቸው አሉታዊና አዎንታዊ ጎኖች

የአገሪቱ ንግድ ባንኮች በዓመት የሚሰጡት የብድር መጠን ላይ የኢትዮጵያ...

ቱግ ቱግ!

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ለመታደም የመጡ እንግዶችን ሸኝተን ከፒያሳ ወደ...