Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልላምብ ፊልም በአይሁድ ፊልም ፌስቲቫል በቀዳሚነት ሊቀርብ ነው

ላምብ ፊልም በአይሁድ ፊልም ፌስቲቫል በቀዳሚነት ሊቀርብ ነው

ቀን:

በዓለም አቀፍ መድረኮች በቅርቡ ለእይታ የበቃው የያሬድ ዘለቀ ‹‹ላምብ›› (ዳንግሌ) ፊልም በሚቀጥለው ወር በኒውዮርክ በሚካሄደው የአይሁድ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ሊቀርብ ነው፡፡

የ25ኛ ዓመት የኒውዮርክ አይሁድ ፊልም ፌስቲቫል አዘጋጆች የሊንከን ሴንተር ፊልም ሶሳይቲና የአይሁድ ሙዚየም እንዳስታወቁት፣ ከጥር 3 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ሳምንት ያህል የሚካሄደው ፌስቲቫሉ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ በኢትዮጵያው ላምብ ፊልም ይታጀባል፡፡ በእንግሊዝኛ የግርጌ መግለጫ ያለው የአማርኛው ፊልም ላምብ በካነስ ፊልም ፌስቲቫል በመመረጥ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ፊልም ሲሆን በኦስካር ለምርጥ የውጭ ቋንቋዎች  ፊልምም ታጭቶ ነበር፡፡

በያሬድ ዘለቀ ተፅፎ የተዘጋጀው ‹‹ላምብ››፣ ኤፍሬም በተባለ ታዳጊ ላይ ያተኮረ ፊልም ነው፡፡ ጩኒ የተባለችው የበግ ግልገል የኤፍሬም ብቸኛ ጓደኛ ናት፡፡ አባቱ ራቅ ወዳለ ስፍራ በመሔዱ ከዘመዶቹ ጋር ለመኖር ይገደዳል፡፡ ዘመዶቹም ጩኒን ለዓመት በዓል ለማረድ ይወስናሉ፡፡ ኤፍሬም የጩኒን ሕይወት ለመታደግ የሚያየውን ውጣ ውረድ ፊልሙ ያስቃኛል፡፡

‹‹ላምብ›› ያሬድ በኒውዮርክ ፊልም ትምህርት ቤት ስኩል ይማር በነበረበት ወቅት የተዘጋጀ ጽሑፍ ሲሆን ሲጀመር 20 ገጽ የነበረው ጽሑፉን ወደ ፊልም እንዲያሳድግ ሐሳብ ያቀረቡት ከያሬድ መምህራን አንዱ ነበሩ፡፡ 

የፊልሙ ጽሑፍ እ.ኤ.አ. በ2012 በአሚኤንስ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ባገኘው ገንዘብም ሊሠራ ችሏል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2013 የፊልሙ ጽሑፍ ሲኤንሲ አውክስ ሲኒማስ ዱምንዴ ከተባለ ድርጅትና ከፈረንሳዊ ፊልም አከፋፋዮች ድጐማ ያገኘው ፊልሙ እንደ ፍራንስ 24 ገለጻ፣ ለፊልሙ በአጠቃላይ 1.5 ሚሊዮን ብር በጀት ማግኘት ተችሏል፡፡

ላምብ በሚቀርብበት በዘንድሮው የአይሁድ ፊልም ፌስቲቫል የብር ኢዮቤልዩ መሰናዶ ከ12 አገሮች 38 ፊልሞች እንደሚቀርቡ ታውቋል፡፡ ከአሥራ ሦስት ቀናት በኋላ ፌስቲቫሉ ሲዘጋ በምሽት የሚቀርበው ፊልም የእሥራኤል አሜሪካዊ ናታሊ ፓርትማን ‹‹ኤ ቴል ኦፍ ላቭ ኤንድ ዳርክነስ›› ፊልም ሲሆን ቋንቋው ዕብራይስጥ ሲሆን የግርጌ መግለጫው እንግሊዝኛ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...