ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሐሙስ ሚያዝያ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. የ16 ሚኒስትሮችን ሹመት አቅርበዋል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል፡፡ ተሿሚዎቹም ቃለ መሀላ ፈጽመዋል፡፡
- አቶ ሽፈራው ሽጉጤ – የግብርናና እንስሳት ሀብት ሚኒስትር
- አቶ ሲራጅ ፈጌሳ – የትራንስፖርት ሚኒስትር
- ሒሩት ወልደ ማርያም (ዶ/ር) – የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
- አምባሳደር ተሾመ ቶጋ – የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር
- አቶ ኡመር ሁሴን – በሚኒስትር ማዕረግ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር
- ወ/ሮ ኡባ መሐመድ – የመገናኛ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
- አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
- አቶ ሞቱማ መቃሳ – የአገር መከላከያ ሚኒስትር
- ወ/ሮ ፎዚያ አሚን – የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር
- አቶ አህመድ ሺዴ – በሚኒስትር ማዕረግ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር
- አቶ ጃንጥላ ዓባይ – የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር
- አቶ መለሰ ዓለሙ – የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር
- አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ – ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ
- ወ/ሮ ያለም ፀጋዬ – የሴቶችና ሕፃናት ጉዳዮች ሚኒስትር
- አቶ መላኩ አለበል – የንግድ ሚኒስትር
- አሚር አማን (ዶ/ር) – የጤና ጥበቃ ሚኒስትር