Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅየአዞዎቹ አንገት

የአዞዎቹ አንገት

ቀን:

አዞዎች ጠላቶቻቸውን በቡድን ሆነው በማጥቃት ይታወቃሉ፡፡ ማንኛውንም የኮሽታ ድምፅ ሲሰሙም፣ ድምፁን ወደ ሰሙበት አቅጣጫ አንገታቸውን ያሰግጋሉ፡፡ በአርባ ምንጭ በሚገኘው የአዞ እርባታ ጣቢያም ድምፅ የሰሙ አዞዎች ጠላቶቻቸውን ለማጥቃት በአንድ ላይ ድምፁ ወደ መጣበት አቅጣጫ አንገታቸውን አቅንተው ይታያሉ፡፡

(ፎቶ በታምራት ጌታቸው)

…………………

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ብቸኝነት

ሰው ነው ለሰው ጉልበት፣ ሰው ነው የሰው ኃይሉ

የሰው ልጅ ነውና ከሰው መንጋ ሸንጎ አይሸሽም ከውሉ

      መኖር ቢማር ከሰው

ደስታን ቢሻ ከሰው

ቢታመም አዳኙ፣ ቢሞት ቀባሪው ሰው

ብቸኝነትን መቼም የትም አያገኘው!

ለብቻው ብቻውን መቼ ተፈጠረ

ራቁቱን እንጂ ብቻውን አልኖረ

ብቸኝነት ሲኦል የልም አገር ህልም ነው

ቢሹት አይገኝም አይኖር ሩቅ ነው

‹‹ብቸኛ ነኝ እኔ›› ብሎ ማለት ዘበት

ለብቻ ላይገፉት የኑሮን አቀበት

ከሰው ተገልሎ ብቻነትን መኖር

ለብቻ መኮብለል ብቸኝነት አገር

የት?… እንዴት ተብሎ…? የማይመስል ነገር!

  • ተፈሪ ዓለሙ፣ የካፊያ ምች፣ 2007 ዓ.ም.
  •  

 

‹‹እኔም ሲጀማምረኝ እንዲህ ያደርገኝ ነበር››

ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም በዘመነ መንግሥታቸው ነው አሉ፡፡ በከተማችን ያሉ ሆስፒታሎችንና በሽተኞችን የመጎብኘት ዕቅድ ይዘው ተነሱ፡፡ በዕቅዳቸውም መሠረት ሆስፒታሎቹን አዳርሰው ማሳረጊያቸውን አማኑኤል የአዕምሮ በሽተኞች ሆስፒታል አደረጉ፡፡

እዛም እንደደረሱ ሆስፒታሉን የሚያስጎበኛቸው ዶክተር ጠጋ አላቸውና ‹‹ጓድ ሊቀመንበር ያው እንግዲህ እዚህ ያሉት ትንሽ የአዕምሮ በሽተኞች በመሆናቸው ያልተገባ ባህርይና ንግግር ቢያደርጉም ይቅርታ ያድርጉላቸው፤›› ሲል ገለጻውን ጀመረ፡፡ መንግሥቱም እየተዘዋወሩ ተመልክተው በሽተኞቹን ሲጠይቁ አመናጫቂያቸው፤ ወራፊያቸው በዛ፡፡ ያው ግን [የአእምሮ በሽተኞች] ናቸውና ማንም ምንም አላደረጋቸውም፡፡ ጤነኛ ናቸው ተብሎ የሚታሰቡ ቢሆን አብዮታዊና እብደታዊ ዕርምጃ ይወሰድባቸው ነበር፡፡

በስተመጨረሻ ዶክተሩ ከሕመማቸው አገግመው ሊወጡ ጥቂት ቀናት የቀራቸው በሽተኞች ዘንድ አደረሷቸውና ‹‹ጓድ እነዚህ እንግዲህ የተሻላቸው ናቸው፤ በቅርቡ ድነው ይወጣሉ›› አለ፡፡ ኮሎኔል መንግሥቱ ግን የዶክተሩን ንግግር በተግባር ለመፈተን ፈልገው ነው መሰል በማገገም ላይ ለሚገኙት በሽተኞች ሰላምታ ከሰጧቸው በኋላ፣ ‹‹ለመሆኑ እኔ ማን? ነኝ አውቃችሁኛል?›› ሲሉ ጠየቁ፡፡ ነገር ግን ማንነታቸውን የሚያውቅ ሰው የፋ ‹‹ኧረ አናውቅህም›› ተባሉ፡፡ ይኼኔ ታዲያ መንግሥቱ ራሳቸውን ለማስተዋወቅ ‹‹እኔ ማለት የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የደርግ ሊቀመንበር፣ የኢሠፓኮ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ፣ የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት…›› ቀጠሉ፡፡ ይኼኔ አንደኛው በሽተኛ በጩኸት አቋረጣቸው፡፡ ‹‹ኦ ሰውዬ! እኔንም ሲጀማምረኝ እንዲሁ ያናግረኝ ነበር፤›› ሲል በጓዶቻቸው ፊት ኩም አደረጋቸው ይባላል፡፡

  • አሸናፊ ደምሴ፣ የኢሕአዴግ የማርያም መንገድ፣ 2007 ዓ.ም.
  •  

‹‹ፈረዝ መጋላ››

ወደ አማርኛ ሲመለስ ‹‹የፈረስ ገበያ›› ማለት ነው፡፡ በምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች ያሉ የአውቶቡስ መናኸሪያዎች በወል በዚህ ስም ይጠራሉ፡፡ ታዲያ እኔ የለመድኩት አጠራር ‹‹ፈረስ መጋላ›› እንጂ ‹‹ፈረዝ መጋላ›› ስላልነበር ‹‹አንድ የአማርኛና አንድ የኦሮምኛ ቃል እንዴት ቢቀናጁ ነው ‹ፈረስ መጋላን› ሊያሰኙ የቻሉት?›› በማለት ለረጅም ጊዜ ስገረም ቆይቻለሁ፡፡ የሀረሩን ‹‹ፈረዝ መጋላ›› ካየሁ በኋላ ግን አግራሞቴ መልኩን ይዟል፡፡

ፈረዝ መጋላ እንደስሙ ‹‹የፈረስ ገበያ›› ነበር፡፡ በተለይም ከደጋማው የጋረ ሙልአታ አውራጃ (ከሀረር ከተማ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ የሚገኝ ተራራማ አውራጃ) የሚመጡ ገበያተኞች የደራ የፈረስ ግብይት ያካሂዱበት እንደነበር የሀረሪ ሽማግሌዎች ይናገራሉ፡፡ ያ ዘመን አልፎ ተሽከርካሪ ወደ ሀረር ሲገባ ደግሞ ፈረዝ መጋላ የአውቶቡሶች የተሳፋሪ ማውረጃና መጫኛ ቦታ ሆኖ ሲያገለግል ኖረ፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን የከተማ ታክሲዎችና የባለ ሦስት እግሮቹ ‹‹ባጃጆች›› የስምሪት መነሻና መድረሻ ሆኗል፡፡

በ‹‹ፈረዝ መጋላ›› ዙሪያ ‹‹አሚር አብዱልላሂ መገስ ጋር›› (የአሚር አብዱላሂ ቤተ መንግሥት እና የመድኃኒአለም ቤተ ክርስቲያንን ጨምሮ በርካታ ሕንፃዎች ይገኛሉ፡፡ ከእነርሱ ውስጥ እኔን ያስገረመኝ ግን በጽሑፍ ምንጮች ብዙም ያልተወራለት ‹‹ካፍቴሪያ አሊባል›› ነው፡፡ ዕድለኛ ሆናችሁ ወደ ‹‹ካፍቴሪያ አሊባል›› ከገባችሁ ‹‹በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ካፍቴሪያ›› ውስጥ መሆናችሁን እወቁት፡፡

  • አፈንዲ ሙተቂ፣ ሀረር ጌይ፣ 2004 ዓ.ም.
  •  

የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር በታዳጊው በቦክስ ተመቱ

የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያኖ ራጆይ በሰሜናዊ ስፔን በምትገኘው ፖንቴቮድራ የምርጫ ቅስቀሳ እያደጉ ባሉበት ወቅት በ17 ዓመት ታዳጊ በቦክስ ተመቱ፡፡

ሜትሮ እንደዘገበው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጎዳና ላይ ቅስቀሳ እያደጉ ባሉበት ወቅት ከአጠገባቸው በመሆን በእጁ የድል ምልክት ሲያሳይ በነበረ ወጣት ነው በቦክስ የተመቱት፡፡ ሚኒስትሩ በጠንካራው ምት መሬት የወደቁ ቢሆንም ከመነፅራቸው መሰበርና ከጉንጫቸው መበለዝ በስተቀር የከፋ ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ዘገባው ያሳያል፡፡ ሚስተር ራጆይ ከፖንቴቮድራ አቅራቢያ ወደምትገኘው ኮሩና ከተማ ቅስቀሳ ለማድረግ ሲያቀኑ እየሳቁ እንደነበር የስፓኒሽ ሚዲያ ዘግቧል፡፡ የ17 ዓመቱ ታዳጊም በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ የሚስተር ራጆይ ተቀናቃኝ የሆነውና ዛሬ በሚካሄደው የአገሪቱ ምርጫ የሚሳተፈው ፓርቲ፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የተቃጣውን ጥቃት አውግዟል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...