Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሃይማኖት ተቋማት ድርቁን አስመልክተው አገር አቀፍ የፀሎት ፕሮግራም ሊያደርጉ ነው

የሃይማኖት ተቋማት ድርቁን አስመልክተው አገር አቀፍ የፀሎት ፕሮግራም ሊያደርጉ ነው

ቀን:

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በአገሪቱ የተከሰተውን ድርቅ አስመልክቶ አገር አቀፍ የፀሎት ፕሮግራም ለማዘጋጀት መወሰኑን አስታወቀ፡፡ በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ክልልና በአማራ ክልል ጐንደር አካባቢ የተፈጠሩ አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ የጠየቀ ሲሆን፣ በቅርቡ በአንዋር መስጊድ የደረሰውን የቦምብ ጥቃትንም በጽኑ እንደሚያወግዝ አስታውቋል፡፡

መንግሥት ድርቅ የተከሰተባቸውን አካባቢዎች አስቀድሞ በመለየት መደረግ ስለሚገባቸው ቅድመ ጥንቃቄዎችና ከድርቁ ጋር ተያይዞ ስለሚከሰቱ ልዩ ልዩ የእንስሳትና የሰዎች የጤና ሥጋቶች ተከታታይ ማሳሰቢያ መስጠቱን ያስታወሰው መግለጫው፣ የሃይማኖት አባቶች በሃይማኖት ተቋማት ኅብረተሰቡ እርስ በእርሱ እንዲረዳዳና በፀሎትም ፈጣሪን እንዲለምን ልዩ ልዩ መልዕክቶች፣ ውሳኔዎችና ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ሲያደርጉ መቆየታቸውን የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አስታውቋል፡፡

ለዚህ እንቅስቃሴም ይረዳ ዘንድ ሁሉም የእምነት ተቋማት በየሃይማኖታቸው አስተምህሮ መሠረት አገር አቀፍ ፀሎት ለማድረግ መወሰናቸውን አስታውቋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹በአገሪቱ ስላለው የሰላም ሁኔታና ድርቁ ባስከተለው ጉዳት ዙሪያ ላይ የሃይማኖት አባቶች የጋራ የፀሎት ጊዜ እንዲወሰን ያደርጋሉ፤›› በማለት ያስታወቀ ሲሆን፣ የጋራ የፀሎት ጊዜውም ሁሉም ቤተ እምነቶች በሚስማሙበት መሠረት በቅርቡ ለሕዝቡ እንደሚገለጽ ጠቁሟል፡፡

በተመሳሳይ በቅርቡ በአገሪቱ የተከሰተውን አለመረጋጋት መንግሥት ከኅብረተሰቡ ጋር ግልጽ ውይይት በማድረግ እንዲፈታው ጥሪ አቅርቧል፡፡

‹‹በአገራችን የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ አለመግባባቶች አሉ፡፡ በዚህም ምክንያት መንግሥት ከኅብረተሰቡ ጋር የጀመራቸው ውይይቶች በተጠናከረ መንገድ መቀጠል አለበት፤›› በማለት የሃይማኖት አባቶች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በቅርቡ በአንዋር መስጊድ የደረሰውን አደጋ በጽኑ እንደሚያወግዙ የገለጹት የሃይማኖት አባቶች፣ እንዲህ ዓይነት ድርጊቶች ኢሰብዓዊ ናቸው ብለዋል፡፡

‹‹በሃይማኖት ሽፋን የሚደረግ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ሕዝባችንን ሰላሙንና ሃይማኖቱን ሊያደናቅፉት አይገባም፤›› በማለትም መግለጫው አሳስቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...