የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከታኅሳስ 11 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊቀርብ ነው፡፡
ከምክር ቤቱ በተገኘ መረጃ መሠረት የምክር ቤቱ አባላት ከታህሳስ 11 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በዕቅዱ በተካተቱ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ የሚመክሩ ሲሆን፣ ዓርብ ታህሳስ 14 ቀን 2008 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ ተገኝተው ካስረዱ በኋላ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል፡፡
በምክር ቤቱ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ታኅሳስ 11 ቀን 2008 ዓ.ም. የብሔራዊ ፕላኒንግ ኮሚሽን ኮሚሽነሩ ዶ/ር ልናገር ደሴ ቀርበው ከአባላት ጋር ውይይት ያደርጋሉ፡፡
በቀሪዎቹ ቀናትም በየዘርፉ የሚገኙ የአስፈጻሚው አካላት አመራሮች በተያዘላቸው ጊዜ መሠረት በምክር ቤቱ በመቅረብ ተመሳሳይ ውይይትና የማስረዳት ሥራ እንደሚያከናውኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡