Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበተወሰኑ አካባቢዎች የዕርዳታ እህል በዕጣ እየተከፋፈለ መሆኑን የፓርላማው ቡድን ገለጸ

በተወሰኑ አካባቢዎች የዕርዳታ እህል በዕጣ እየተከፋፈለ መሆኑን የፓርላማው ቡድን ገለጸ

ቀን:

‹‹የሎጂስቲክስ እንጂ የእህል የአቅርቦት ችግር የለም›› አቶ ተፈራ ደርበው

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስድስት ቡድኖች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በመዘዋወር በድርቁ ምክንያት ያለውን ጉዳትና የመንግሥት እንቅስቃሴ ለመገምገም ባደረገው ምልከታ፣ በአንዳንድ አካባቢዎች የዕርዳታ እህል በዕጣ እየተከፋፈለ መሆኑን ገለጸ፡፡

በፓርላማው የተዋቀሩ ስድስት ቡድኖች ከብሔራዊ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚቴ ባገኙት መረጃ ላይ ተመሥርተው በሁሉም ክልሎች የድርቁ ገጽታን ለማየት የሚያስችሉ አካባቢዎችን በመለየትና በሥፍራው በመገኘት፣ ከየአካባቢው ነዋሪዎችና ከአስተዳደር አካላት ጋር መወያየቱን የሁሉንም ቡድኖች ምልከታ በመወከል ሪፖርት ያቀረቡት የምክር ቤቱ አባል አቶ ታደሰ ወርዶፋ ናቸው፡፡

በአንዳንድ ቀበሌዎች ከሚታየው አድሏዊ አሠራርና በዕርዳታ አቅርቦት እጥረት የተነሳ የዕርዳታ እህል በዕጣ እየተከፋፈለ መሆኑን የገለጹት አቶ ታደሰ፣ በአብዛኛው አካባቢ ግን ከፌዴራል መንግሥት የላይኛው እርከን አንስቶ እስከ ታችኛው የክልል አስተዳደር ድረስ በተናበበ መልኩ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የተሠሩ የተፈጥሮ ሀብት ሥራዎች ድርቁ ሊያስከትል የሚችለውን የከፋ ችግር ለመቋቋም ማስቻሉን የተናገሩት አቶ ታደሰ፣ በ2005/06 የእርሻ ወቅት ምርት ያላገኙ አካባቢዎች፣ በ2007 ዓ.ም. በልግ ምርት ያላገኙ አካባቢዎች አሁን ያለውን ችግር ተቋቁመው የመገኘታቸው ሚስጥር ይህ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የድርቁ ሁኔታ በዚሁ የሚቀጥል በመሆኑ መንግሥት የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ ሊሠራ ይገባል ብለዋል፡፡ ከእህል አቅርቦት ይልቅ ዋነኛው ችግር ለሰውም ሆነ በእንስሳት የሚጠጣ ውኃ አለመኖር መሆኑን አውስተዋል፡፡

በአማራ ክልል በዋግምራ ዞን በአንድ ወረዳ ውስጥ ሰባት ቀበሌዎችን ውኃ ወዳለበት አካባቢ እንዲሰፍሩ የማድረግ ሥራ መሠራቱን ተናግረዋል፡፡

በአቅርቦት ረገድ ለሚስተዋሉ ችግሮች አቶ ታደሰ ያቀረቡት አንዱ ምክንያት፣ በአንድ ወቅት የተያዙ መረጃዎችን እስካሁን መጠቀም፣ ትክክለኛ ወቅታዊ መረጃዎችን ከመያዝ ይልቅ አጠቃላይ መረጃዎች ላይ መንተራስን ነው፡፡

የኅብረተሰቡን ይሁንታ የማግኘትና የማሳተፍ ሥራ የመከናወኑን ያህል የዚሁ ተቃራኒ በበርካታ ቦታዎች መኖሩን አመልክተዋል፡፡ በአንዳንድ አከባቢዎች አድሏዊ አሠራሮች መኖራቸውን፣ የዕርዳታ ፓኬጅ በአንድ ጊዜ ባለመቅረቡ የተነሳ ተረጂዎች ለመጉላላት መዳረጋቸውን፣ በአንዳንድ ቀበሌዎች የሚደረገው ድጋፍ በችግሩ ስፋት ልክ ባለመሆኑና በኮታ በመቅረቡ ከመርህ ውጪ በዕጣ መልክ ለማዳረስ እየተሞከረ ነው፡፡

በተለይም በአፋር ክልል ሚሌ ወረዳ አዳይቱ ውስጥ ዕርዳታው በወቅቱ ደርሶ እያለ፣ ያለ ምንም ምክንያት ዕርዳታው ያልተከፋፈለበት ሁኔታ መታየቱን ገልጸዋል፡፡

የቀረበውን ሪፖርት ተከትሎ ሊቀርቡ ለሚችሉ የማብራርያ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጡ ከተጠሩት ሚኒስትሮች መካከል፣ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው በድርቁ ምክንያት ዋና ችግር የሆነው የውኃ አቅርቦት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሕዝቡ የሰፈረበትና ውኃ ያለበት አካባቢ አይገናኝም የሚሉት ሚኒስትሩ፣ ይህም ቢሆን በቦቲና በተለያዩ አማራጮች ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ሕዝቡ ወደፊት ከአካባቢው መፈናቀል ከጀመረ ዋነኛው ምክንያት የውኃ እጦት እንደሚሆን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ‹‹ከሰብል አቅርቦት አኳያ ችግር ይኖራል ብሎ አይገመትም፡፡ ዋናው ችግር የሎጂስቲክስ ጉዳይ ነው፡፡ ከወደብ እስከ ተለያዩ የችግሩ አካባቢዎች በወቅቱ ማድረስ አስቸጋሪ ነው፤›› ብለዋል፡፡

የአገር ውስጥ የአልሚ ምግብ ፋብሪካዎች ያለባቸውን የካፒታልና የጥሬ ዕቃ ችግር መንግሥት ቀርፎላቸው፣ ሰባት ኩባንያዎች ወደ ሥራ መግባታቸውንና በውጭ አገርም የአልሚ ምግብ ግዥ መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶ/ር ከሰተ ብርሃን በበኩላቸው ድርቁን ተከትሎ ሊመጡ የሚችሉ በሽታዎች መካከል ወባ አንዱ መሆኑን፣ ወባና የምግብ ችግር ከተገናኙ ውጤቱ አስከፊ በመሆኑ 34 ሚሊዮን አጎበሮች በተመረጡ አካባቢዎች መከፋፈላቸውን ገልጸዋል፡፡

የማጅራት ገትር በሽታም ሌላኛው ወረርሽኝን ሲሆን፣ ለእዚህም ዝግጅት መደረጉን አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ግን በተወሰኑ አካባቢዎች መታየቱን አስረድተዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በበኩላቸው፣ በድርቁ ምክንያት ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ ውኃ በሚገኝባቸው አካባቢዎች በድንኳን ውስጥ የትምህርት ሥርዓቱ መቀጠሉን፣ እንዲሁም የፌዴራል መንግሥት በቅርቡ በወሰነው መሠረት ከቅርብ ጊዜ በኋላ በሁሉም አካባቢዎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በቀን አንዴ ምገባ እንዲካሄድ መወሰኑን ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...