Saturday, September 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊኢቦላ አሁንም የኅብረተሰብ ጤና ሥጋት ነው ተባለ

ኢቦላ አሁንም የኅብረተሰብ ጤና ሥጋት ነው ተባለ

ቀን:

– 34 አገሮች የጣሉትን የጉዞ ዕገዳ እንዲያነሱ ተጠየቀ

የዓለም የጤና ድርጅት በምዕራብ አፍሪካ የኢቦላ ወረርሽኝ መቀስቀስን ተከትሎ ያቋቋመው ኮሚቴ ሰኞ ታኅሣሥ 11 ቀን 2008 ዓ.ም. ለቀናት ያካሄደውን ውይይት ሲያጠናቅቅ ኢቦላ አሁንም የኅብረተሰብ ጤና ሥጋት መሆኑን አስታውቋል፡፡

ኮሚቴው በአሁኑ ወቅት ኢቦላ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የጤና ሥጋት መሆኑ አብቅቷል ወይስ እንዳለ ነው በሚሉት ነገሮች ላይ መክሮ ነበር፡፡ ኮሚቴው በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ በምዕራብ አፍሪካ ያለውን የኢቦላ ሁኔታ በድጋሚ ገምግሞ ሪፖርት እንዲያቀርብም ተጠይቋል፡፡

ኮሚቴው እንዳስታወቀው የመጀመሪያውን የኢቦላ ወረርሽኝ ሰንሰለት በማቋረጥ ረገድ መሻሻሎች ታይተዋል፡፡ ለዚህም ባለፉት ጥቂት ወራት ጊኒ፣ ሴራሊዮንና ላይቤሪያ ሪፖርት ያደረጓቸው የኢቦላ ኬዞች በማስረጃነት ቀርበዋል፡፡ ቢሆንም ግን ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ የታዩ የኢቦላ አዳዲስ ኬዞች እክል ሆነዋል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በላይቤሪያ ሦስት ኬዞች ታይተዋል፡፡

እነዚህን ኬዞች በፍጥነት መቆጣጠር የተቻለ ቢሆንም ይህ የሚያሳየው ዛሬም ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የተቀናጀ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ አስፈላጊ መሆኑን ኮሚቴው አስታውቋል፡፡ ምንም እንኳ የቫይረስ ጥንካሬ በጊዜ የሚወሰን ቢሆንም በኢቦላ ቫይረስ ተፈጥሮ፣ ቆይታውና ተፅዕኖው ላይ ተጨማሪ ጥናት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡

ኮሚቴው ከኢቦላ ቫይረስ ጋር በተያያዘ ተገቢ ያልሆነ የጉዞ ዕገዳ የጣሉ 34 አገሮች ጉዳይ አሳሳቢ እንደሆነ ገልጿል፡፡ የጉዞ ዕገዳው በኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ የተጠቁ አገሮች ከደረሰባቸው ችግር የማገገም ጥረታቸውን በእጅጉ የሚጎዳ በመሆኑ ዕገዳው በአስቸኳይ መነሳት እንደሚገባው አሳስቧል፡፡

በኮሚቴው ኢቦላ ወረርሽኝ ለተቀሰቀሰባቸው አገሮች ከተቀመጡ ምክረ ሐሳቦች መካከል በኢቦላ ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ከሕክምና ጋር የተያያዘ ካልሆነ በቀር ዓለም አቀፍ ጉዞ እንዳያደርጉ፣ በዓለም አቀፍ አየር መንገዶች ተጓዦች አሁንም ተመርምረው እንዲያልፉና አገሮች ስለአጠቃላይ የኢቦላ ሁኔታ በየጊዜው ለሕዝብ መረጃ እንዲሰጡ የሚሉ ይገኙበታል፡፡

ሌሎች ሁሉንም አገሮች በሚመለከት ከተሰጠው ምክረ ሐሳብ መካከል ምንም ዓይነት ዓለም አቀፍ የጉዞ ወይም የንግድ ዕገዳ ማድረግ እንደማያስፈልግ፣ ለተጓዦች በሚሄዱበት ቦታ የኢቦላ አደጋ ካለ ይህን የሚመለከት መረጃ መስጠትና አገሮች የኢቦላ ኬዞችን ለመመርመርና ለመቆጣጠርም ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል የሚሉ ይገኙበታል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...