Saturday, February 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ሥነ ፍጥረትየአፍሪካ አንበሳ ጥበቃ አገኘ

የአፍሪካ አንበሳ ጥበቃ አገኘ

ቀን:

በመጥፋት ላይ የሚገኘው የአፍሪካ አንበሳ (ፓንቴራ ሌዮ)፣ በአሜሪካ ለመጥፋት በተቃረቡ ዝርያዎች ጥበቃ ከለላ ማግኘቱን ሳይንስ አለርት ዘግቧል፡፡

በምዕራብና መካከለኛው አፍሪካ የሚገኘውና ወደጥፋቱ የተቃረበው የአፍሪካ አንበሳ፣ ለመጥፋት የተቃረበ የእንስሳት ዝርያ በሚልም ተመዝግቧል፡፡ 1400 የሚጠጉት የአፍሪካ አንበሳ ወይም ፓንቴራ ሌዮ ዝርያዎች በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች እንዲሁም በእስያ ተበታትነው ይገኛሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ሚላኖቺይታ የተባለውና በምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የአንበሳ ዝርያ እየተመናመነ በመሆኑ በቅርቡ ሊጠፉ ከተቃረቡ እንስሳት ዝርዝር ውስጥ ይካተታል ተብሏል፡፡ ከዚህ ዝርያ ከ17 ሺሕ እስከ 19 ሺሕ ያህል ዝርያዎች ብቻ መቅረታቸውም ተገልጿል፡፡

የአፍሪካ አንበሳ በአሜሪካው ለመጥፋት የተቃረቡ ዝርያዎች ተቆጣጣሪ ጥበቃ ማግኘቱ፣ አንበሳውን ከመሰረቅ፣ ከሕገወጥ አዳኝንና ዝውውር ለመከላከል ያስችላል፡፡

ናሽናል ጂኦግራፊ እንዳሰፈረው፣ ከድመት ዝርያ የሚመደቡት አንበሶች ብቸኛዎቹ በቡድን የሚኖሩ እንስሳት ናቸው፡፡ በአንድ የአንበሳ ቡድን ውስጥ ሶስት ወንዶች፣ ብዙ ሴቶች ሕጻናትና ወጣት አንበሶች ይኖራሉ፡፡ ወንዶቹ በቡድናቸው ውስጥ የሚኖሩ አንበሶችን ከአደጋ ይጠብቃሉ፣ የሚኖሩበትን አካባቢም ይቆጣጠራሉ፡፡ ሴቶቹ ደግሞ የቡድኑ ቀዳሚ አዳኞች ናቸው፡፡ ከወንዶቹ ጋር በመተባበርም የሜዳ አህያ፣ ሳላ፣ ሚዳቆ እንዲሁም ትላልቅ እንስሳትን ያድናሉ፡፡ የመሮጥ አቅምን በተመለከተ አብዛኞቹ የዱር እንስሳት አንበሳን በሩጫ የሚቀድሙ በመሆኑ፣ አንበሶች የሚያድኑት በቡድን ነው፡፡

ከአጥቢ እንስሳት የሚመደቡት አንበሶች ስጋ በሊታ ሲሆኑ፣ የአንዱ አንበሳ ክብደትም ከ120 እስከ 191 ኪሎ ግራም ይመዝናል፡፡ ከጭንቅላቱ እስከ ጅራቱ ከ1.4 ሜትር እስከ 2 ሜትር ድረስ ይረዝማል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከህወሓት የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኙ

የፌዴራል መንግሥትና የህወሓት የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትር...

ማስተካከያ

በሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ዕትም...

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...