Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅየሚጠቀምበትን ዊልቸር ወደ ባጃጅ በራሱ ፈጠራ በመቀየር እየተጠቀመበት ይገኛል

የሚጠቀምበትን ዊልቸር ወደ ባጃጅ በራሱ ፈጠራ በመቀየር እየተጠቀመበት ይገኛል

ቀን:

ነጃ ሞሳ የሚኖረው በስልጤ ዞን ነው፡፡ የአካል ጉዳተኛ ሲሆን ትምህርት የተማረውም እስከ አራተኛ ክፍል ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርቷል፡፡ የዊልቸር ተጠቃሚ መሆኑ በንግድ ሥራው ላይ እንደልቡ ለመንቀሳቀስ አላስቻለውም፡፡ በመሆኑም የሚጠቀምበትን ዊልቸር ወደ ባጃጅ በራሱ ፈጠራ በመቀየር እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡ ፎቶ በመስፍን ሰለሞን

**********

አለፈ

እንዲህ በፀጥታ እንዲህ በማረመም

አንዴ በመታዘብ አንዴ በመገረም

ስንት ቀን አለፈ

ስንት ሐሳብ ከሸፈ

አዎ! ‹‹በ›› … ምናልባት እየተለወጠ

ምናልባት ‹‹ለ›› … ቢቀር እጁን እየሰጠ

 ስ… ን…ት… ቀን አለፈ

ከዕድሜ ላይ ድርሻውን እየሞጨለፈ

ዕልፍ ቀን

ዕልፍ ሌት እያየሁ አለፈ

መንፈሴ ያጣውን
ገላዬ ያለውን አጥብቆ እንዳቀፈ፡፡

*******

  • ብሩክታዊት ጎሳዬ፣ ጾመኛ ፍቅር፣ 2007 ዓ.ም.

ሰው ብርቱ

ይቺ ኑሮ መቼም የትም ታስኖራለች፡፡ ለምሳሌ እዚሁ እኛ አገር እንኳ ድሬዳዋ መቃጠል ነው፣ አሰብ መንደድ ነው፣ ደብረ ብርሃን መንቀጥቀጥ ነው ወዘተ እንላለን፡፡ ብርዱንም ሆነ ሙቀቱንም ግን እየቻለ ሰው ይኖራል፡፡ ዓባይን ያላየ … አይሁንብን እንጂ ሳይቤሪያዎች ከዜሮ በታች 75 ዲግሪ ውስጥ ይኖራሉ፡፡ ሰሃራዎችም ከዜሮ በላይ 125 ዲግሪ ውስጥ ይኖራሉ፡፡ ከ30 እስከ 40 ውስጥ እየኖርን አየሩን እምናማርር ብንኖርም እንዲያም ይኖራል ማለቱ ጥሩ ነው፡፡ አይለመድ ነገር የለ!

*******

ደሃ ነው የሚታጠብ

‹‹ሲሠራ ሲጨማለቅ የሚለው ደሃ ነው፡፡ እኛ ምን በወጣን እንታጠብ?›› እንዲህ የሚሉት የመካከለኛው ዘመን የአውሮፓ ከበርቴዎች ናቸው፡፡ ቱጃርነታቸውን ለማሳወቅ ሲሉም ጨርሶ አይታጠቡም፡፡ በሕይወት ዘመናቸው ውኃ ነክቷቸው እንደማያውቁ በኩራት ያወራሉ፡፡ በ16ኛው ክፍለ ዘመን የነበረችው ንግሥት ኤሳቤጥ ግን ይኼ ነገር አልተዋጠላትም፡፡ ምክንያቱም ቢያንስ በወር አንዴ ትታጠብ ነበርና፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን በዚያን ጊዜ በነገሥታት ዘንድ እንኳ ሳይቀር እንደታላቅ ስጦታ እንሚቆጠር አንድ ውድ ነገር ነበር ሽቶ!

*******

ኮካ ኮላ ምን ማለት ነው?

ምንም ማለት አይደለም፡፡ ያው ኮካ ኮላ ነው፡፡ በየትኛውም አገር ቋንቋ ትርጉም አልነበረም፡፡ ይሄ ተጠንቶና ታውቆ ነው ስያሜው የተሰጠው፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬ መጠጡ የደረሰበት አገር ሁሉ ያውቀዋል ከዚህ ውጭ ኮካ ኮላ ማለት በእገሌ ቋንቋ እንዲህ ማለት ነው የሚል ካለ ይወራረድ፡፡ በተረፈ ግን ፈጠራ ማለት እንዲህ ነው እንበል ይሆን?

******

ባቢሎን

ብዙ ሰዎች እስከ አሥር ቋንቋዎች አሳምረው መናገር ይችላሉ ይባላል፡፡ ጆሴፍ ካስፓርን የሚያክል ግን አልተገኘም፡፡ በ18ኛው ክፍለ ዘመን በኢጣሊያ የተወለደው ካስፓር ወደ 30 ቋንቋዎች እንደሚናገር ይነገርለታል፡፡ የምን 30 ነው እሱ 50 ነው የሚችለው እሚሉም አሉ፡፡ ይቅርታ አድርጉልኝና ባይገርማችሁ 100 ልሳኖችን አሳምሮ ሊረዳ ይችላል ብለው የመሰከሩለትም ያን ያህል ናቸው፡፡ ለማንኛውም ይህን ያህል ይናገራል ማለቱ አስቸጋሪ ቢሆንም በትሹ ከ30 በላይ መናገሩ እርግጥ ነው፡፡ ይህን ሁሉ ቋንቋ ሲለምድ ግን እግሩ ከጣሊያን ምድር ውልፍት አላለችም፡፡ ካስፓርን ያስቸገረው ቋንቋ ቢሮር ቻይንኛ ነው፡፡ ቻይንኛን ለማወቅ ብዙ ደክሟል፡፡ ምን ማለታችሁ ነው? አራት ወር እኮ ነው የፈጀበት!

(ዕፎይታ ታኅሣሥ፣ 1985 ዓ.ም.)

**********

ከ450 ዶላር በላይ የሚያወጣ ጌጣጌጥ ለሚገዙ ሽጉጥ በነፃ የሚሰጥ ሱቅ

የምዕራባውያንን ገና አስመልክቶ በአሜሪካ ፍሎሪዳ የሚገኘው የዳይመንድና የሌሎች ጌጣጌጦች መሸጫ ሱቅ፣ ከ450 ዶላር በላይ የሚያወጣ ጌጣጌጥ ለሚገዙ ሰዎች 12 ጐራሽ ሽጉጥ በነፃ እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡

ዩፒአይ እንደዘገበው፣ እንደዚህ ዓይነቱ ማስታወቂያ ያልተለመደ ቢሆንም፣ በ2015ቱ ገና ግን ለሴት ጓደኞቻቸው ወይም ለሚስቶቻቸው ጌጣጌጥ የሚገዙ፣ 450 ዶላር ብቻ በማውጣት፣ የጌጣጌጥና 270 ዶላር የሚያወጣ ሽጉጥ ባለቤት ይሆናሉ፡፡

‹‹ጐልድስሚዝ ጂውለሪ ኤንድ ኢንግሬቪንግ›› ባለቤት ጄሲ ዢሮክ፣ ‹‹ለሚስት ጌጣጌጥ መግዛት ትንሽ ስጦታ ነው፡፡ ጌጣጌጥ በመግዛት አንድ ሽጉጥ ያግኙ›› ስትል ተናግራለች፡፡

*******************

የአሽከርካሪውን መተኛት ያየ ዝንጀሮ መኪናውን አስነስቶ አጋጨ

ጉዳዩ የተፈጸመው ህንድ ውስጥ ነው፡፡ አሽከርካሪው በሪሊ በተባለው የአውቶቡስ ማቆሚያ መኪናውን አቁሞ ሸለብ አድርጐታል፡፡ አሽከርካሪው አገልግሎ ለመስጠት ተራው እስኪደርስ የ30 ደቂቃ ጊዜ የነበረው ቢሆንም፣ እንዳሰበው 30 ደቂቃውን መተኛት አልቻለም፡፡ ሸለብ እንዳደረገው ያየ ዝንጀሮ በመስኮት በመግባት መኪናውን ያስነሳል፡፡ በድንጋጤ ከእንቅልፉ የነቃው አሽከርካሪ ዝንጀሮውን ከመሪው ላይ መወርወር ቢችልም፣ መኪናውን ግን ማቆም አልቻለም ነበር፡፡ እንደ ዩፒአይ ዘገባ፣ መኪናው በስፍራው የነበሩ ሁለት መኪኖችን ገጭቶ ቆሟል፡፡

***************

ታጃኪስታን በትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች የገና በዓል እንዳይከበር አገደች

በቀድሞዋ ሶቭየት ሪፐብሊክ ሥር የነበረችው ታጃኪስታን፣ ገናን አስመልክቶ በትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች ምንም ዓይነት ዝግጅት እንዳይደረግ አገደች፡፡

ስካይኒውስ እንደዘገበው፣ ለገና ተብለው የሚዘጋጁ ምግቦች፣ ርችቶች እንዲሁም ስጦታ መለዋወጥም ሆነ ገቢ ማሰባሰቢያ ማድረግ ተከልክሏል፡፡ የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ የገና ዛፍ ማድረግም አልተፈቀደም፡፡

ባለፈው ዓመት የሩሲያ ዓይነት የገና አባት እንዳይኖር የከለከለችው ታጃኪስታን፣ በዚህ ዓመት ጠንካራ የተባለ እገዳ መጣሏን ዘገባው ያሳያል፡፡

***************

የአውስትራሊያ አርሶ አደሮች የገና ምኞታቸው የሞባይል ስልክ አገልግሎት እንዲሻሻል መሆኑን ገለጹ

በምዕራብ አውስትራሊያ የሚኖሩ ሁለት ዋና የአርሶ አደር አቀንቃኝ ቡድኖች፣ የገና ቀዳሚው ሞኖቻቸው የሞባይል ስልክ ግንኙነት የተጠናከረ እንዲሆን መሆኑን ገለጹ፡፡

ኤቢሲ እንደሚለው፣ በምዕራብ አውስትራሊያ የኢንተርኔት ኔትወርክ መቆራረጥና ጥራትና ቀጣይነት ያለው የሞባይል ስልክ አገልግሎት ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ በመሆኑም አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮችና የግጦሽ ሣር መሬት ባለቤቶች በ2015 የገና ቀዳሚ ምኞታቸው ያልተቆራረጠ የሞባይል ስልክ አገልግሎት ማግኘት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...