Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከዩኒቨርሲቲ መምህራን 40 በመቶው የዶክትሬት 60 በመቶው የማስተርስ ዲግሪ እንዲኖራቸው እየተሠራ መሆኑ...

ከዩኒቨርሲቲ መምህራን 40 በመቶው የዶክትሬት 60 በመቶው የማስተርስ ዲግሪ እንዲኖራቸው እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

ቀን:

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደረጃ በዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የመምህራን ደረጃ 60 በመቶ የማስተርስ ዲግሪ፣ 40 በመቶ ዶክትሬት ዲግሪ ያላቸው እንዲሆኑ የተወሰነ ሲሆን በቀጣይ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ይህንን አሠራር እንዲከተሉ እንደሚደረግ የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ተናገሩ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ2008 ዓ.ም. እስከ 2012 ዓ.ም. ድረስ የሚተገበረው ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ረቂቅ ዕቅድ ላይ ሐሙስ ታህሳስ 14 ቀን 2008 ዓ.ም. በተወያየበት ወቅት የተገኙት አቶ ሽፈራው፣ በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ኢላይብረሪዎች መቋቋማቸውን፤ በቀጣይ የግል ዩኒቨርሲቲዎች ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመሠረተ ልማት በሚገናኙበት ዙሪያ እንደሚሠራም አክለዋል፡፡

በቀጣዩ አምስት ዓመት የጎልማሶችን ትምህርት 95 በመቶ ለማድረስ እየተሠራ መሆኑንና ቅድመ ትምህርት ማለትም የመዋዕለ ሕፃናት ትምህርትም በሁሉም የመንግሥት ትምህርት ቤቶች እንዲጀመር መወሰኑንም ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ሕፃናት ለሕፃናት ማለትም ቤት ውስጥ የሚውሉ ሕፃናት እርስ በእርሳቸው የሚማማሩበት ፕሮጀክት በአንዳንድ ክልሎች መጀመሩንና በቀጣይም በሁሉም ክልሎች ለማዳረስ እየተሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የትምህርት ሥልጠናን ማፋጠንና ጥራትን በተመለከተ እንዳሰፈረው፣ የመሠረታዊ ትምህርት አገልግሎትን ለሁሉም ለማዳረስ ይሠራል፡፡ ጥራቱን የጠበቀ፣ ፍትሐዊና ተደራሽ የሆነ የቅድመ መደበኛ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን ለሁሉም ለማዳረስ፣ ወጪ ቆጣቢና በኅብረተሰቡ ሙሉ ተሳትፎ የተደገፈ መደበኛና መደበኛ ባልሆኑ ስልቶች ትምህርት እንዲስፋፋ የሚደረግም ይሆናል፡፡

የአጠቃላይ ትምህርት ተሳትፎን በተመለከተ፣ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ጥቅል ተሳትፎን በ2007 ዓ.ም. ከነበረበት 39 በመቶ በ2012 ዓ.ም. ወደ 80 በመቶ፣ የአንደኛ ደረጃ (ከ1‑8) ንጥር ተሳትፎን ከ96.9 በመቶ ወደ 100 በመቶ፣ የሴቶችንና የወንዶችን የትምህርት ተሳትፎ ምጣኔ ልዩነትን በአንደኛ ደረጃ ትምህርት አንደኛ እርከን (1‑4) በ2007 ከነበረበት 0.93፡1 በ2012 ዓ.ም. ወደ 0.99፡1፣ የትምህርት ፍላጎት ያላቸውን ሕፃናት የአንደኛ ደረጃ (1-8) ትምህርት ጥቅል ተሳትፎ ከ4.4 በመቶ ወደ 15 በመቶ ለማድረስ ግቦች ተቀምጠዋል፡፡ በተመሳሳይ የአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተሳትፎን ከ40.5 በመቶ በ2012 ዓ.ም. ወደ 79 በመቶ ለማድረስ የታቀደ ሲሆን፣ በከተማ፣ በገጠርና በክልሎች መካከል ያለውን ትምህርት ተሳትፎ ልዩነትን ለማጥበብና የተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት ተሳትፎ ምጣኔን ወደ 95 በመቶ ለማድረስ ግብ ተቀምጧል፡፡

በትምህርት ጥራትና አግባብነት ረገድ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ሁሉም ትምህርት ቤቶችና የጉድኝት ማዕከላት በደረጃው መሠረት የሙያ ብቃታቸው በተረጋገጠ ርዕሰ መምህራንና ተቆጣጣሪዎች እንዲመሩ የሚደረግ ሲሆን ለየደረጃው ሙያዊ ብቃታቸው የተረጋገጡ መምህራንን ምጣኔ በ2007 በጀት ዓመት ከነበረበት 20 በመቶ በ2012 ወደ 70 በመቶ ለማድረስ ታስቧል፡፡ የማቋረጥና የመድገም ምጣኔዎችን ለመቀነስ ከፍተኛ ርብርብ የሚደረግ ሲሆን ከቅድመ መደበኛ እስከ መሰናዶ ሁለተኛ ደረጃ ያለው ሥርዓተ ትምህርት ከሥራ ፈጠራና ቴክኖሎጂ ጋር ተሳስሮ እንዲከለስ ማድረግና ሁሉም የእርከኑን ትምህርት ያጠናቀቁ ተማሪዎች ከየእርከኑ የሚጠበቀውን የሥነ ዜጋና የሥነ ምግባር ባህሪያትን የተላበሱ ስለመሆናቸው ዳሰሳ የሚደረግም ይሆናል፡፡

የትምህርት ጥራትና አግባብነት ላይ ጥናት የሚያካሂድና የትምህርት ሥርዓቱን የሚደግፍ ከሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት እስከ ትግበራ ተቀናጅቶ የሚሠራ የጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት የሚቋቋም ይሆናል፡፡

የሴት ተማሪዎች ተሳትፎን በተመለከተ፣ በቅድመ ምረቃ ፕሮግራም በ2007 ከነበረበት 32 በመቶ በ2012 ወደ 45 በመቶ በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም በ2007 ከነበረበት 19.5 በመቶ በ2012 ወደ 25 በመቶ እንዲሁም በፒኤችዲ ፕሮግራም ደግሞ በ2007 ከነበረበት 11 በመቶ በ2012 ወደ 20 በመቶ ለማድረስ የሚሠራ ሲሆን፣ የመምህራን ልማትን በማጠናከር ጥራትን ለማሳደግ የመምህር ተማሪ ጥምርታ ወደ 1፡19 ይደርሳል፡፡

የመምህራን ብዛትም ወደ 33,030 ይደርሳል፡፡ ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው የበቁ መምህራን ብዛት በ2007 ከደረሰበት 58 በመቶ በ2012 ወደ 75 በመቶ፣ ሦስተኛ ዲግሪ ያላቸው በመማር ላይ ያሉና ያጠናቀቁ መምህራን ብዛት በ2007 ከደረሰበት 15 በመቶ በ2012 ወደ 25 በመቶ የሚያድግም ይሆናል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...