Monday, June 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊፀረ ኤችአይቪ መድኃኒት በክትባት መልክ ሊቀርብ ነው

ፀረ ኤችአይቪ መድኃኒት በክትባት መልክ ሊቀርብ ነው

ቀን:

ከሦስት ዓመት በኋላ ፀረ ኤችአይቪ መድኃኒትን በክትባት መልክ ለማቅረብ መታቀዱን የአዲስ አበባ ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ ኤችአይቪ ቫይረስ በደሙ ውስጥ ያለበት ሰው በ1993 ዓ.ም. በቀን ስምንት የፀረ ኤችአይቪ መድኃኒት ይውጥ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ በቀን አንድ ፍሬ እየተወሰደ ይገኛል፡፡

ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ አረጋውያንና ጡረተኞች ብሔራዊ ማኅበር 27ኛው ዓለም አቀፍ የኤድስ ቀንን ምክንያት በማድረግ በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የስብሰባ አዳራሽ ባካሄደው የምክክር መድረክ ላይ በጽሕፈት ቤቱ የሪሶርስ ሞባላይዜሽን ኦፊሰር አቶ ዳዊት ይታገሱ ነበር፡፡

አቶ ዳዊት ይህን የተናገሩት “ዓለም አቀፉ የፀረ ኤድስ ምላሽ ስኬት፣ ፈታኝ ሁኔታና ቀጣይ ሥራዎች” በሚል ርዕስ ባደረጉት ገለጻና ማብራሪያ ነው፡፡ እንደ አቶ ዳዊት ማብራሪያ፣ ክትባቱን ወይም መድኃኒቱን የማቅረቡን ሥራ ለማከናወን በዕቅድ ተይዞ የነበረው በ2022 ዓ.ም. ነበር፡፡ ነገር ግን በክትባቱ ዙሪያ እየተካሄደ ያለው ምርምርና ጥናት በአብዛኛው እየተጠናቀቀ በመምጣቱ ከሦስት ዓመት በኋላ እንደሚቀርብ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባንኪ ሙን በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የፀረ ኤችአይቪ/ኤድስ ማዕከላትን ሲጎበኙ ቃል ከገቡት መካከል አንዱ ክትባቱ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባበት ሁኔታ ይመቻቻል የሚለው ይገኝበታል፡፡

ከዚህም ሌላ በ1993 ዓ.ም. የፀረ ኤችአይቪ መድኃኒት ተጠቃሚዎች አንድ ሚሊዮን አካባቢ እንደነበሩ፣ በ2007 ዓ.ም. የተጠቃሚዎች ቁጥር ወደ 15 ሚሊዮን እንዳደገና በ2022 ዓ.ም. ደግሞ ቫይረሱ ያለበት ሰው ሁሉ መድኃኒት ይጠቀማል ተብሎ እንደሚታሰብ ተናግረዋል፡፡ የመድኃኒት ተጠቃሚዎች ቁጥር ከፍ ማለት የሚያሳየው በዘርፉ ከፍተኛ የሆነ ኢንቨስትመንት መሠራቱን ሲሆን ይህም የቫይረሱ ጫና እንዲቀንስ፤ ቫይረሱንም ለማጥፋት እየተሠራ ያለውን ሥራ እንደሚያበረታታ ተገልጿል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው ባለፈው ዓመት በኤች አይ ቪ የሞቱ ሰዎች ቁጥር በዓለም አቀፍ ደረጃ ሁለት ሚሊዮን ነው፡፡ ይህ አሃዝ በ2022 ዓ.ም. ወደ ዜሮ ይወርዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ለዚህም ተግባራዊነት ሰፊ ሥራ ይጠይቃል፡፡

ከእናት ወደ ልጅ ኤችአይቪ እንዳይተላለፍ ለማድረግ ሲባል እናቶች ሳይመረመሩ እንዳያረግዙ፣ በእርግዝና ወቅት ደግሞ የጤና ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራል፡፡ ቆየት ቢልም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተካሄደ ጥናት እንደሚያሳየው በኤችአይቪ/ኤድስ ዙሪያ የተሟላ ግንዛቤ ያላቸው ወጣቶች 35 ከመቶ ያህል ብቻ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያም ሆነ በአዲስ አበባ የተንፀባረቀውም ይኸው እውነታ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

“ለጊዜው ይህንን በሽታ ታሪክ የሚያደርግ ሌላ አዲስ መድኃኒት የለም፡፡ ያለው ማኅበራዊ ክትባት ብቻ ነው፡፡ ይህም ክትባት ማስተማር ብቻ ነው” ያሉት አቶ ዳዊት፣ ግንዛቤ ካላቸው ሰዎች ትክክለኛ ውሳኔ መወሰን ይችላሉ የሚል ዕምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

የኤድስ ሞትም እየቀነሰ መጥቶ በ2022 ዓ.ም. ከ200 ሺሕ በታች ወርዶ ዜሮ እንዲሆን የማድረግ ዕቅድ አለ፡፡ የተመዘገቡ ለውጦች እንደሚያሳዩት ሞቱ እየቀነሰ መጥቷል፡፡ በ2006 ዓ.ም. ወደ 1.5 ሚሊዮን በቫይረሱ ምክንያት መሞታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ያሳያል፡፡ ከዚህ ውስጥ 1,100,000 የሚሆነው አፍሪካ ውስጥ የተመዘገበ ነው፡፡

አቶ ዳዊት የዓለም አቀፍ ሪፖርትን ዋቢ አድርገው እንደገለጹት በሚቀጥሉት 15 ዓመታት ከፍተኛ ገንዘብ ቫይረሱን ለመከላከልና ለመቆጣጠር መመደብ ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ በ1993 ዓ.ም. ኤችአይቪን ለመከላከል የዋለው ገንዘብ 4.9 ቢሊዮን ዶላር እንደነበር፣ በ2007 ዓ.ም. ወደ 21.7 ቢሊዮን ዶላር እንዳደገ፣ በ2022 ዓ.ም ወደ 32 ቢሊዮን ዶላር ማደግ እንዳለበት ነው ያመለከቱት፡፡

ይህም የሆነበት ምክንያት የፀረ ኤችአይቪ መድኃኒት የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር ስለሚጨምር ለመድኃኒት መግዣ እና ለምርመራ ለመሳሰሉት የሚያስፈልገው ወጪ ከፍተኛ ስለሚሆን ነው፡፡ “ስለሆነም ከግለሰብ ጀምሮ ሁላችንም በዚህ ላይ አስተዋጽኦ ካላደረግን መንግሥትና ድርጅቶች ብቻ የሚሸፍኑት ወጪ አይደለም” ብለዋል፡፡

ወይዘሪት ሀብታምነሽ አስፋው የአረጋውያንና ጡረተኞች ብሔራዊ ማኀበር ፕሮጀክት አስተባባሪ የተባበሩት መንግሥታት የኤችአይቪ/ኤድስ ድርጅት በ2004 ዓ.ም. ያወጣውን መረጃ ጠቅሰው እንዳብራሩት በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕድሜያቸው 50 እና ከዛም በላይ የሚሆኑ 3.6 ሚሊዮን አረጋውያን በደማቸው ውስጥ የኤችአይቪ ቫይረስ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ 2.9 የሚሆኑት ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት የሚኖሩ ናቸው፡፡

በእነዚህ አገሮች የሚገኙ ወደ 100 ሺሕ የሚጠጉ አረጋውያን በየዓመቱ በኤችአይቪ/ኤድስ እንደሚያዙ መረጃው ጠቁሟል፡፡ ኽልፕ ኤጅ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ከሌሎች አጋር ድርጅቶች፣ በአዲስ አበባ አስተዳደር፣ በአማራ፣ በኦሮሚያና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች በሚገኙ ከተሞችና ገጠሮች ያካሄደው ጥናት እንደሚያሳየው 35 በመቶ ያህል አረጋውያን ስለኤችአይቪ/ኤድስ ምንም ዓይነት ዕውቀት የላቸውም፡፡

በተለይ አዲስ አበባ ውስጥ የተከናወነ ሌላ ጥናት እንደሚያሳየው ወደ ውጭ አገር ለመጓዝ ሲሉ ምርመራ ካደረጉ አረጋውያን 11.7 በመቶ፣ እንዲሁም ደም ለመለገስ ከቀረቡ መካከል ደግሞ 1.5 በመቶ ያህሉ የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ተገኝቷል፡፡

ታህሳስ 12 ቀን 2008 ዓ.ም. በተካሔደው በዚሁ የምክክር መድረክ፣ ከአሥሩም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ አረጋውያን፣ የመንግሥት ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ተወካዮች የተገኙ ሲሆን፣ በኤችአይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ላይ ያተኮረ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...