Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናበነፃ የተሰናበቱት ጦማሪያን ላይ የቀረበው ይግባኝ ያስቀርባል ተባለ

  በነፃ የተሰናበቱት ጦማሪያን ላይ የቀረበው ይግባኝ ያስቀርባል ተባለ

  ቀን:

  ከተጠረጠሩበት የሽብር ድርጊት ወንጀል መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ ተሰናብተው የነበሩት አራት ጦማሪያንና አንድ ተከላከል የተባለ ጦማሪ፣ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበባቸው የይግባኝ አቤቱታ ‹‹ያስቀርባል›› በመባሉ ለክርክር ተጠሩ፡፡

  ጦማሪያኑ ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላ፣ ሶሊያና ሽመልስ (በሌለችበት)፣ አጥናፉ ብርሃነና በፍቃዱ ኃይሉ ሲሆኑ፣ ከበፍቃዱ በስተቀር ሁሉም በነፃ እንዲሰናበቱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ውሳኔ የሰጠ ቢሆንም፣ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በውሳኔው ቅር በመሰኘት ይግባኝ መጠየቁ ይታወሳል፡፡

  በመሆኑም ይግባኙ የቀረበለት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔን ሲመረምር ከርሞ የዓቃቤ ሕግን ይግባኝ አቤቱታ በመቀበል፣ ጦማሪያኑ ታኀሳስ 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀርበው እንዲከራከሩ የትዕዛዝ ጥሪ እንደደረሳቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ እንዲከላከል የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጥቶበት ለጥር 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ተቀጥሯል፡፡

  የተለያዩ ሥልጠናዎችን በመውሰድ፣ ለሽብር ተግባር መፈጸሚያ የሚሆን ገንዘብ ከውጭ ተባባሪያቸው በመቀበልና ሕዝብን ለአመፅ የሚያነሳሱ ጽሑፎችን በማሰራጨት፣ የሽብር ድርጊት ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በሚያዝያ ወር 2006 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ክስ ተመሥርቶባቸዋል፡፡ ተከሳሾቹ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስና አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ጦማሪያን ናትናኤል ፈለቀ፣ ኤዶም ካሳዬ፣ አቤል ዋበላ፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ሶሊያና ሽመልስ፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ ማህሌት ፋንታሁንና ዘለዓለም ክብረት ነበሩ፡፡

  ክስ ተመሥርቶባቸውና ዓቃቤ ሕግ የሰነድና የሰው ምስክሮቹን አሰምቶ እንደጨረሰ ለብይን ተቀጥረው እያለ፣ ጋዜጠኛ ተስፋለምና አስማማው እንዲሁም ጦማሪያን ዘለዓለም ክብረት፣ ኤዶም ካሳዬና ማህሌት ክሳቸው መቋረጡን ፍትሕ ሚኒስቴር ነግሯቸው ከእስር መፈታታቸው አይዘነጋም፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...